Artists

Mesfin Mekonen (መስፍን መኮንን)

Producer | Writer

We do not have full information about this artist, Please send us your contribution to our Facebook page or by email to [email protected]

Blen Mamo (ብሌን ማሞ)

Actress

ተወልዳ ያደገችው ደብረ ብርሃን ነው የትወና ፍቅሮን ለመወጣት ከልጅነቱ ጀምሮ የምታገኛቸውን አጋጣሚዎች ትጠቀም ነበር በመጨረሻም ወደ ባህርዳር አምርታ ሙሉዓለም አዳረሽ በተወናይነት ተቀጠረች። የተለያዮ መድረኩችን በትወና ሰርታለች ሙሉዓለም አዳራሽ ውስጥ መቼቱ እዛው ባህርዳር የሆኑ ፊልሞችንም ላይም ተውናለች። በጌትነት እንየው የተዘጋጀው የቴዎድሮስ ራዕይ ላይ ከለችበት ሀገር ወጥታ ብሄራዊ ትያትር መድረክ ላይ ተዋበችን ሆና ተውናለች የቲቪ ድራማ ለይ ደግሙ ምንም ትንሽ ፓርት ቢሆንም ገመና ላይ ሰርታ... read more

Dereje Mekonnen (ደረጄ መኮንን)

Director

We do not have full information about this artist, Please send us your contribution to our Facebook page or by email to [email protected]

Yigerem Dejene (ይገረም ደጀኔ)

Actor

በርካቶች መልካም ስነ-ምግባር ያለው ተዋናይ ነው ይሉታል። በ1972 ዓ.ም አሮጌው ቄራ አካባቢ ተወልዶ ያደገው የዛሬው የመዝናኛ አምድ እንግዶችን በፊልም ደረጃ ዕጣ-ፈንታ፣መስዕዋት፣ አዲስሙሽራ፣ 70/30፣ አስክሬኑ፣ ውበት ለፈተና፣ የትሮይ ፈረስን ጨምሮ ከ30 በላይ ፊልሞችን ሰርቷል። የጀግኖች ማህደር፣ ቅድስተ-ካናዳ፣ ሜዳሊያ፣ ምዕራፍ አራት፣ የብዕር ስምን ጨምሮ በቅርቡ በሚከፈተው የደራሲ ውድነህ ክፍሌ “የደመና ዳንኪረኞች” ቴአትሮች ላይ ተውኗል። በቲቪ ድራማዎቹ ከሚጠቀሱለት መካከል ሾፌሩ፣ አን... read more

Selam Ashagre (ሰላም አሻግሬ)

Actress

በቅርብ ጊዜ ያሉ ተዋንያን እንደሚቀላቀሉት እሷም መንገድ ላይ ያያት ዳይሬክተር ነበር የመጀመርያዋን ፊልም ያሰራት:: እያለች ሌላ አንድ ፊልም ጨምራ የቲቪ ድራማ መስራት ጀመረች። ዋና ስራዋ ማርኬቲንግ ነው:: ወደ ትወና የተቀላቀለችው በዚህ መንገድ ነው።

Sinafikish Tesfaye (ስናፍቅሽ ተስፋዬ)

Actress

ውልደት እና እድገቷ አዲስ አበባ ዑራኤል ነው። የትወና ፍቅሯ ህልሞ ብቻ ሳይሆን ስኬቱማ ጭምር ሆኖላታል ከፊልሞች ይልቅ ትያትር በተለይ ብሄራዊ ትያተር ብዙ ሰርታለች፣የሬዲዮ ድራሞችንም፣የቲቪ ድራማውችንም ላይ ተውናለች ስናፍቅሽ ተስፋዬ። በይበልጥ የምትታወቀው ያልተኬደበት መንገድ ላይ ቢጢቆ ሆና ስትሰራ ነው።

Emebet Woldegabriel (እመቤት ወልደገብሬል)

Actress

ተወልዳ ያደገችው አዲስ አበበ ለም ሆቴል ነው ነው። በልጅነቷ ጋዜጠኛ መሆን ትፈልግ ነበር ግን የሆነችው ተዋናይ ነው ተስፋዬ ስሜ ጋር ትምህርትን ወስዳ ወደ ትወናው በትያትር ተቀላቀለች የመጀመርያዋን መድረክ ህፃናት ወጣቶች ተቀጥራለች ቀጥላም በብሄራዊ ትያትር ተቀጥራ እየሰራች ነው በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ የትያትር ምሩቅ ናት በረከታ ትያትሮች፣ሬዲዮ ድራማዎች፣የቲቪ ድራማ እና ፊልሞች ሰርታለች።

Haregewoin Assefa (ሐረገወይን አሰፋ)

Actress

ለጥበብ የተፈጠረች መሆኗን ሁሉ ይስማማባታል ብዙ ትያትሮች፣ለመቁጠር ወር የሚወስዱ የቲቪ ድራማውች እና ጥቂት የማይባሉ ፊልሞች ላይ ሳርታለች። ወርቅ በመሰለው ድምጿ በርካታ ትረካዎችን ተርካለች እንዲሁ ብዙ መድረኮችን መርታለች አሁን ቢቆም ዳሩ ዜማ ፍቅር የሚል የሬድዮ ፕሮግራሟ ከወዳጇ ፀደንያ ገ/ማርቆስ ጋር ከ5ት አመት በላይ ሰርታለች ሀረገወይን አሰፋ።

Misgana Atnafu (ምስጋና አጥናፉ)

Actor | Director | Writer

የተወለደው አዲስ አበባ መሳለሚያ (ኳስ ሜዳ) ነው። ከልጅነቱ ነበር የትወና ፍቅር የነበረው: ትምዕርት ቤት እያለ ሚኒሚድያ ላይ ብዙ ተሳትፎ ያደርግ ነበር ሲያድግም አየር ጤና የኪነጥበብ ክበብ እያለም በግሩፕ ፑሽኪን አደራሽ ትያትሮችን ማቅረብ ቀጠለ ያኔም የሚያቀርባቸው ስራዎች ላይ በግሩፑ በትወናም፣በድርሰትም እንዲሁም በዝግጅት ይሳተፍ ነበር።

Addisalem Getaneh (አዲስዓለም ጌታነህ)

Actress

መስከረም 1 ተወለደች ትውልድና እድገቷ ወሊሶ ነው፡፡አዱ፣አዱኮ፣ሚሚሹ እንዲሁም ፔንኪለር የተሰኙ ቅፅል ስሞች አሏት፡፡እስካሁን 14በላይ ፊልሞችን ሰርታለች የባል ጋብቻ የመጀመሪያ ፊልሟ ሲሆን አሁን በቅርቡ የሰራቸው ሀ እና ለ2 ነው፡፡ለመጀመሪያ ክፍያዋ 8000 ብር ነበር ከትወና ሌላ መደነስ፣መዝፈን ትወዳለች፡፡ ባህሪዋ ተጫዋች፣አይናፋር ናት አይናፋርንቷ ግን ስራ ላይ እንዳልሆነ ተናግራለች ስትደሰት ደስታዋን ምትገልው በመጮህ ሲሆን ስታዝን ደሞ አብዝታ ትፀልያለች፡፡በሀበሻነቷ ከምትኮራበት ነገሮች ባ... read more

Tilahun Gugsa (ጥላሁን ጉግሳ)

አንጋፋ የኪነ ጥበብ ሰው ተብሎ ከሚጠሩት ውስጥ ውልደቱ እና ዕድገቱ አዲስ አበባ መርካቶ ነው እድገቱ ላይ ካለበት ራስ ትያትር ለረዥም አመት አገልግሏል ብዙ ትያትር ላይ ተውኖል፣ፅፏል በተጨማሪም አዘጋጅቷል። አሁን ላይ ለ4ት አመት በተከታታይ ሲታይ አሁንም እየታያ ያለው ቤቶች ላይ በድርሰትም አልፎ አልፎ በዝግጅትም ይሰራል ከትወና እና ከፕሮዲሰርነት በተጨማሪ ይሰራል። በይበልጥ የሚታወቀው በትያትር ጀምሮ ወደ ፊልም የቀየረው መንጠቆ ላይ መንጠቆን ሆኖ ሲሰራ ነው። ከፊልም ባለሙያ ... read more

Tewodros Fekadu (ቴዎድሮስ ፈቃዱ)

Actor | Director | Writer

ውልደት እና እድገቱ አዲስ አበባ ነው የጥበብ መንገዱን አንድ ብሎ በቤሄራዊ ትያትር ክረምት ኮርስ ተማሪ እያለ ወስዷል ቀጥሎ የብዙ ጥበብ መፍለቅያ የሆነው ፋዘር(ዶ/ር ተስፋዬ አበበ)ቤት ተማረ, .. እያለ እያለ ከአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ በትያትር ጥበብ ተምሮ ጨርሶል::ብዙ ሳምንት አሌደም እንጂ ናሁ ቲቪ ላይ ኑሮ በዘዴ የቲቪ ስትኮም ድራማ ደራሲ እና አዘጋጅ ነበር።