Dec. 19, 2016, 11:21 p.m. by EtMDB
"አጥር ሳናጥር ሳንከልል ድንበር እንዋደድ እንከባበር!!!! ለመወደድ ለመከባበር ምክንያት አንፍጠር በአምሳሉ መፈጠራችን ይበቃል ሰው መሆናችን!!!!" በነቁራ ልጀምር እንዴ...በእውቀቱ ስዮም እንዲህ ብሉ ነበር "እኛ ኢትዮጲያዊያን የመጀመርያ መሆን እንወዳለን የሁሌም ጀማሪ መሆን እንፈልጋለን በጣም ስለምንወድ ቤት ውስጥ ሁለተኛ ልጅ በመሆን የመጀመርያ ነን እንላለን።" ብሉ ነበር እና እና ፫ት ማዕዘን 2ት ማስታወቂያው ላይ ሰራዊት ፍቅሬ "ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጲያ በ5ት ቋንቋ Sound Track የተሰራለት ፊልም" ይላል ቴዲ የብዙ ነገር ጀማሪ ነው ፊልም በሲኒማ ቤት ማሳየት አሁን ቁሚ የሆነው በሁሉም ሲኒማ ቤት ማስመረቅ በአባይ ወይስ ቬጋስ ነው የተጀመረው፣ መኪና ለተዋናይ መሸለም እንደዛው አሁን ደግሞ በቋንቋ መምጣቱ መጀመርያ የሚለውን ቃል ለማስጠበቅ ይመስላል... ወደ ገደለው ስገባ አሁን ፊልማችን ቀዝቅዙል ብዙ ሲኒማ ቤት እየተዘጋ ነው ፊልም ፕሮዲሰርም እንደ ፑሊዮ እየሸሸ ነው። በዚህ መሀል ታድያ የብዙ ነገር የመጀመርያ ጀማሪ የሆነሆ ቴድሮስ ተሻመ በአንዴ 5ት ሲኒማ ቤት ዋናውን መስቀል አደባባይ ያለው ጨምሩ ከፈተ፣ በተመሳሳይ ሳምንት ደግሞ ደራሲ ዳይሬክተር ትንሽ Part ቢሆንም ተዋናይ የሆነበትን 3ት ማዕዘን ፪ትን አስመረቀ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሙ የአንተነህ ሀይሌ ፊልም እሱ በኤክስኩቲቭ ፕሮዲሰር የሆነበትን ሌላው አሪፍ ፊልም የእግዜር ድልድይን አሰመረቀ ከምር ጅግና ነው። 3ት ማዕዘን ሁለት ጊዜውን ጠብቁ የመጣ በጣም አሪፍ ጥራቱ ከ3ት አመት በፊት የተሰራ ያማይመስል ታሪኩ ፍቅርን ከአበድኩልሽ ውጪ አብሮነትን በሚያጠናክር ሁኔታ የመጣ ከምር ደረጃውን የጠበቀ ፊልም ነው።ሳልፅፍ ማለፍ የማልፈልገው ነገር ሁሉም ተዋንያን ከአበበ ባልቻ እሰከ ሰላም ተስፋዬ ሁሉም ከልብ ምርጥ አርገው ነው የሰሩት አንድ ሰው ግን በጣም አስደምሞኛል እሱም ጀማል ወክሉ ሳይሆን ሆኖ የሰራው ሙሉቀን ተሻመ ነው ጀማልን ለመሆን ኪሎ ከመቀነስ ጀምሮ ብዙ እንደሞከረ እሱ ነግሮኝል እኔ ደግሙ ለእናነተና ለእሱ ደግሜ ልናገር በጣም ከልቡ ከውስጡ ተውኖል ሙሌ!!!! (እንደ ጥቆማ ሱስት ማዕዘን 1 ካየነው ስለቁየ መቼም ለቴዲ በሲዲ አውጣው ማለት ይከብዳል ምክንያቱም ስለማያውጣው እንደው ታሪኩን በደንብ ለማስታወስ ወደ ሲኒማ ቤት ቢመለስው ሁሉም ጋር ባይሆን እንኳን ሴባስቶፖል ሲኒማ ቤቶች ጋር ቢመለስ ሸጋ ይመስለኛል)
By Tsion Tamrat