Yemaleda Kokeboch S3 Finale (የማለዳ ኮከቦች ምዕራፍ 3)

የዘንድሮ (ምዕራፍ 3) የማለዳ ኮከቦች የትወና ውድድር አሸናፊ የሚቀጥለው ሳምንት ይታወቃል ሰለዚህ እሰከ ሰኞ እንዲያሸንፍ ለምንፈልገው ተወዳዳሪ ሞቅ አርገን ድምፅ የምንሰጥበት ጊዜ ነው ማለት ነው። የአሁኑ ውድድር እንደ ባለፈው እንደ ካቻአምናው አዝናኝ ነበር! ለአሸናፊነት ስጠበቅ የነበረው ካሳሁን ለመጨረሻ ሳይደርስ መቅረት፣እንደ ራህዋ ሳይጠበቁ ማስደመም፣ ሜላትን የመሰለ ተዋንናይት እንደ ብፁሀን በጣም አዝናኝ ሰው... ብቻ ቡዙ አይተናል እኔ ማለፍ አልፈልግም አሱወድቁኝ ያለው፣"እማ አትበይ" የተባለችውን ጨምሩ ማለት ነው፡፡ ምርጥ 10 ከገቡት ውስጥ በጣም ሁለቱ ይገርሙኛል ዘላለም እና ኤልሳቤት፣ ዘላለም በጉልበቱ እዚ የደረሰ ነው አላቀረብኩም መቼ ሰራው ብለው ተቁጥቱ ያስደመመ ልጅ ነው አንደኛ ይወጣል ብዬ የምጠብቀው ከወንድ እሱ እና አዛርያስን ነው ሌላዋ ኤልሲ ናት የመጀመርያው ዙር ላይ ማህሌት እሱን ለመጣል ሰከንድ እንኳን አለሰበችም አስለቅሳት ነበር ግን መጨረሻ ደረሰች ማሂን ከማሳመን አልፋ ያኔ የተናገረችው እንዲፀፅታት አስደርጋለች በግሌ አንደኛ ከሴት ሊወጡ ይችላሉ ብዬ የምገምታቸው አንዱ ኤልሳቤት አሰፋ እና ሌላው ታምረኛ ሜላት አንዋር ነው። አሳይተዋል የምለውን ከ1-5 ከወንድም ከሴትም የሚከተሉት ናቸው፡፡
ወንድ ተወዳዳሪዎች
  1. ዘላለም ዘማ
  2. ኑርልኝ ብርሀኔ
  3. አዛርያስ ተስፋዬ
  4. አቤል ሀ/ስላሴ
  5. ድማሙ ይታይህ
ሴት ተወዳዳሪዎች
  1. ሜላት አንዋር
  2. ብፁሀን ሽፈራው
  3. እልልታ ያለው
  4. ኤልሳቤት አሰፋ
  5. ራህዋ መብራቱ
የማለዳ ኮከቦች ድህረ ገፅ ላይ አሸናፊ መሆን ይገባቸዋል ላላቹት ድምጽ ስጡ!!! ለእርሶ ምርጥ የነበሩትን ከወንድ ከሴት ብለው ይምረጡ ውጤቱ እና ሽልማቱን ለፋሲካ ሚያዚያ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢቢስ ይከታተሉ ፡፡
Ethiopian acting competition show on EBS Tv, is created by the renown film writer & director Fitsum Asfaw. Yemaleda Kokeboch Season 3 finale award will be hosted on EBS Tv on 16th of April 2017.

Best wishes to all the 10 contestants from EtMDB!


Comments

or to write a comment

Latest News and Articles

Ethiopian movie news and article - Asansiro
read more