Sept. 7, 2017, 12:50 p.m. by EtMDB
ደራሲ(Writer)፦ የታሪኩ ፈጣሪ ሲሆን የፊልም ስራ ከመሰራቱ ፣ፊልሙ ቡድን ከመሰብሰቡ በፊት ያለ ባለሙያ ነው። በፊልም ሰራው ላይ ቢገኝ ታሪኩ ላይ የሚፈጠሩ ስህተቱችን ለማረም ይረዳል አብዛኛው ጊዜ ደራሲው በቀረፃ ወቅት አይገኝም።የፊልም ፅሁፍ(Screen play)፦ የቀረበለት ድርሰት ወደ ፊልም ፅሁፍ የሚቀይር ባለሙያ ነው። የቀረበለትን ፅሁፍ ቃለ ተውኔት የሚፅፍ ፣ ገፀ ባህርያትን የሚስል ሲፈልግ የሚጨምር እና የሚቀንስ ድርሰቱን በፅሁፍ ፊልም የሚያደርግ ባለሙያ ነው።
የፊልም ፅሁፍ አማካሪ(Script supervisor)፦ ከፊልም ፅሁፍ ከሚፅፈው ባለሙያ ጋራ በጋራ የሚቀነስ እና የሚጨመረውን የሚያማክር አንዳድ ቃለ ተውኔትን የሚፈጥር ባለሙያ ነው። አብዛኛው ጊዜ ከፊልም ቀረፀ ጊዜ አይገኝም።
አዘጋጅ ወይም ዳይሬክተር(Director)፦ ፊልሙ ባለቤት ተብሎ የሚጠራው ዳይሬክተሩ ንው። ፊልሙን በዋናነት የሚያንቀሳቅስ ሲሆን ተዋናዮ የሚያሳየውን ስሜት፣ተዋናዮ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ፣ፊልሙ ታሪክ አካሄድ በአጠቃላይ የፊልሙ ላይ የሚታየው ነገር ሁሉ የዳይሬክተሩ ውጤት ነው። ተዋናይ መልማይ ወይም ካስቲንክ(Casting)፦ ፊልሙ ላይ የሚተውኑ ተዋንያን ካሜራ አድሽን ወስዱ ከዳይሬክተሩ ጋር ለፊልሙ የፈጠራቸውን ገፀ ባህሪያትን በተዋንያን የሚተካ ባለሙያ ነው አብዛኛው ጊዜ በቀረፃ ወቅት መገኝት አይጠበቅበትም።
ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲሰር(Executive producer)፦ በፊልሙ ላይ ትርፍ ለማግኝት ከፍተኛ ወጪ የሚያወጣ ነው። ይሄ ባለሙያ ስለ ፊልም ማወቅ አይጠበቅበትም ዋና አላማው ፊልሙን በገንዘብ ማገዝ ነው። ከፍተኛ የትርፍ ተጋሪ እና የፊልሙ ተደራቢ ባለቤት ነው።
ፕሮዲሰር(Producer)፦ ይሄ ባለሙያ ስለ ፊልም ዕውቀት ያለው ሲሆን ከቀረፃ በፊት ለፊልሙ የተወሰነ ወጪ የሚያወጣ የፊልሙ ባለቤት እና በቀረፃ ወቅት የሚወጡ ወጪዎችን የሚጋራ በተወሰን ረገድ የትርፍ ተጋሪ የፊልም ባለሙያ ነው።
አርት ዳይሬክተር(Art director)፦ ከቀረፃ በፊት ተገኝቱ የሚቀረፅበትን ቦታ ይመርጣል በተጨማሪ በቀረፃው ጊዜ የሚታዮትን ቦታዎችን ከጀርባ ሳቢ እንዲሆኑ ሀላፊነት የሚወስድ ባለሙያ ነው ከፊልም ቀራፃ በፊትም ወቅትም አስፈላጊ ነው።
ፕሮዳክሽን ዲዛይነር(Production design)፦ ከፊልሙ ቀረፃ በፊት የፊልሙን ቀረፃ የሚያቅድ እና የሚወስን ከፊልሙ በፊት የሰራውን ስራ እንዲሰራ የነገሮችን የሚያመቻች ለፊልም ስራ በጣም ቅርብ የሆነ ባላሙያ ነው።
ፕሮዳክሽን ማናጀር(Production manger)፦ በቀረፃ ወቅት ሆነ ከቀረፃው በፊት ለፊልሙ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም ነገር የሚያቀርብ እና ነገሮችን የሚያመቻች የፊልሙ የጀርባ አጥንት ባለሙያ ነው።
የፕሮዳክሽን አማካሪ(Production supervisor)፦ በቀረፃ ወቅት የሚደረገውን ማን ምን እደሚሰራ እና በየትኛው ጊዜ ፊልሙ ተጀምሩ ማለቅ እንዳለበት የትኛው ጊዜ ቀረፃ ቢደረግ ስኬታማ እንደሚሆን ከፕሮዳክሽን ማኔጀሩ ጋር የሚመካከር ነው።
ረዳት ዳይሬክተር(Assistant director)፦ በቀረፃ ወቅት ዳይሬተሩ የሚያስፈልገውን ማለት የቀረፃ ባለሙያ እና ተዋንያን በሰዓቱ እንዲገኙ የሚያደርግ ተዋንያን ቃለ ተውኔት በሚጠፋቸው ጊዜ የሚያቀብል በተጨማሪ ዳይሬክተሩ የሚተውንበት ቦታ ካላ እሱን በማዛጋጀት የሚሰራ ባለሙያ ነው።
ሲኒማቶግራፊ(Director photography)፦ በቀረፃ ወቅት ካሜራ ማን ሆና የሚሰራ ባለሙያ ነው በፊልሙ ላይ በካሜራ የሚታዮ ምስሎችን እና አቅጣጫዎችን የሚወሰን የፊልም ዋና የቀረፃ ባለሙያ ነው።
ረዳት ካሜራ ማን(Assistant camera man)፦ በፊልሙ ላይ በቀረፃ ከሲኒማቶግራፈር ጋር በህብረት የሚቀርፅ ባለሙያ ነው። ከሲኒማቶግራፈር የሚለየው ነገር የካሜራ አቅጣጫወችን የሚወስነው እሱ አለመሆኑ ነው።
ፕሮዳክሽን የሚከታተል(Production coordinator)፦ የፊልሙን ፕሮዳክሽን የሚከታተል የፊልም ባለሙያዎችን በጠቅላላ የሚሰሩትን የሚያስተካክል ባለሙያ ነው። ድምፅ(Sound)፦ ፊልሙ ላይ የሚሰሙትን ድምፁች ከተለያየ አቅጣጫ እየሆነ የሚሰራ የድምፅ ባለሙያ ነው።
መብራት(Light)፦ ፊልሙ ላይ የሚታየውን ብርሃን ከተለያየ አቅጣጫ የሚሰራ የመብራት ባለምያ ነው። ተዋንያን(Cast)፦ በፊልሙ የተሳሉትን ገፀ ባህርያትን ወክለው የሚሰሩ ተዋንያን ናቸው።
ከለር ኮሬክሽን(Color correction)፦ ፊልሙ ከተሰራ በኃላ የፊልሙን ቀለም የሚያስተካክል ፊልሙ ተቀርፁ ካለቀ በኃላ የሚቀላቀል ባለሙያ ነው።
ኮንቲኒቲ(Continuity)፦ በቀረፃ ጊዜ አንድ ተዋናይ የነበረውን ገፅታ ማለትም ልብስ፣ፀጉር፣ጫማ。。。 በሌላ ተመሳሳይ ጊዜ እና ቀን ቀረፃ ጊዜ ያን ገፅታ ተመልሱ እንዲኖረው የሚያደርጉ የፕሮዳክሽን አባል ባለሙያ ነው።
ዝግጅት አስተባባሪ(Production line)፦ በቀረፃ ጊዜ የሚያስፈልግ ትብብር ቀረፃው ከመካሄዱ በፊት የሚያመቻች የፕሮዳክሽን አባል ነው።
አልባሳት(Costume)፦ ገፀ ባህሪው የሚያስፈልገውን እድሜ እና የታሪክ ዘመን ባገናዘበ ሁኔታ አልባሳትን የሚያዘጋጅ የፕሮዳክሽን አባል ነው።
ቤስት ቦይ(Best boy)፦ በቀረፃ ወቅት ማንኛውም ስራ ላይ በጉልበት የሚያግዝ ረዳት የፕሮዳክሽን አባል ነው።
ስታንድ ባይ(Stand by)፦ ያ ተዋናይ ሊሰራው የማይችለው አስቸገራ እና አደገኛ የሆኑ ድርጊቶችን ማለትም ከፎቅ መውደቅ፣ድብድብ(ካራቲ)。。。 ሌሎችንም ለተዋናዮ ከባድ የሆኑ ነገሮችን ተዋንያን ወክሎ የሚሰራ ነው።
አጃቢ ተዋናይ አቅራቢ(Cast agent)፦ በፊልሙ ላይ ትንሽ ተሳትፎ ያላቸውን ተዋንያን የሚቀርብ ባለሙያ ወይም ተቋም ነው።
ጋፈር(Gaffer)፦ በቀረፃ ወቅት ያለውን ኤሌክትሪክ ነክ ነገር የሚቆጣጠር ኤሌክትሪሺያን ባለሙያ የሆነ የፕሮዳክሽን አባል ነው።
ኤዲተር(Editor)፦ ፊልሙ ተሰርቱ ሲያልቅ ድምፅ እና ምስልን የሚያቀናጅ ለፊልም አስፈላጊ ያልሆኑ ቦታሆችን ሰዓት ለማሳጠር ካዳይሬክተሩ ጋር በህብረት የሚቀንስ የፊልሙ የመጨረሻ ገፅታ የሚያሳይ ባለሙያ ነው።
ገፅ ቅብ ወይም ሜካፐር(Make up)፦ ገፀ ባህርያት የሚያስፈልጋቸውን የጉዳት እና የዕድሜ ሁኔታ ተዋናዮ ላይ እንዲታይ የሚያደርግ የፕሮዳክሽን አባል ባለሙያ ነው።
አኒሜሽን(Animation)፦ በቀረፃ ሊሰራ የማይችል ማለትም እንደ ቤት ማቃጠል፣ጦርነት፣እሳት አደጋ。。。በቀረፃ ማሳያት ያልቻሉትን በኮሚፒተር ጥበብ የሚያሳይ ባለሙያ ነው።
የሙዚቃ ቅንብር(Sound score)፦ ፊልሙ በተለያየ ትዕይንት ውስጥ የሚያስፈልገው ሙዚቃ የሚሰራ የ ሙዚቃ ባለሙያ ነው።
ማጀብያ ሙዚቃ(Soundtrack)፦ የፊልሙ ታሪክ ጋር የተገናኝ ለፊልሙ ሲባል የተሰራ ዘፈን የሚያዜም ድምፃዊ ነው።
ሰብታይትል ፀሃፊ(Sub-title writer)፦ የፊልሙ ካለቀ በኃላ የሚመጣ ባለሙያ ሲሆን ቃለ ተውኔቱችን በኢንግሊዘኛ የሚፅፍ እንግሊዘኛ ከሆነ ደግሞ ወደ አማርኝ እየቀየር የሚፅፍ የቋንቋ ባለሙያ ነው።
ፖስቸር ዲዛይነር(Poster designer)፦ ፊልሙ ተሰርቱ ሲያልቅ የሚመጣ ባለሙያ ሲሆን ከፊልሙ ጋር የሚገናኝ ፖስቸር የሚሰራ ነው።
ፕሮሞተር(Promoter)፦ ይሄም ፊልሙ ካለቀ በኃላ የሚመጣ ባለሙያ ሲሆን ፊልሙ እንዲታይ የማስተዋወቅ ስራ የሚሰራ ባለሙያ ነው በተጨማሪም ፊልሙ የሚመረቅ ከሆነ ነገሮችን የሚያስተባብር እና የምርቃት ለት የሚከሰቱ ነገሮችን የሚከታተል ነው።
የፊልሙ ክሩ(Film crew)፦ከላይ የዘረዘርኮቸው በጋራ ሁሉም በህብረት ሲሰሩ መጠርያቸው የፊልም ክሩ ነው።