Misten Darkuat (ሚስቴን ዳርኳት እንደ እኔ)

(ከብዙ ጊዜ በኃላ ትንሽ ቢሆን ያከራከረ እና የተወራለት አማርኛ ፊልም መምጣቱ እንደ ትጉ ተመልካች እኔም ትንሽ ደስ ብሎኛል። ብዙ ወዳጁቼ ስለ ሚስቴን ዳርኳት ፊልም ጠይቀውኛል ለሁሉም መልስ ለመስጠት የሚሰማኝን ይሀው)
👉 በረከት ወረዳ(ማያ) ከእውነት ሀሰት ፊልሙ አንፃር ይህን ሳየው ከተዋናይ በቀር ወርዶብኛል
👉 አፄ ማንዴላ እና ድንግሉ ፊልም ፕሮዲሰር ይላል ከላይ ሁለቱም ፊልሞች ለእኔ ማዕበራዊ ችግሮችን ከማሳየቱ ብዙም ባልተናነሰ መሆን የሌለባቸውን አይቻለው በዚህ ፊልም ደሞ በጣም ተሰምቱኛል!
👉 የህክምና ስህተቱች የምንሰማበት እና የምናይበት ሀገር ነው ልክ ነው! ግን ሀኪሞችን አትመኑ ማለት ልክ አይደለም ለእኔ ሚስቴን ዳርኳት የህክምና ባለሙያዎች በጥንቃቄ እንዲሰሩ ካስተላለፈው ይልቅ ታካሚኦች ህክምና ቦታ ሄዳቹ የሚነገራቹውን አትመኑ የሚሰሩትን አያውቁም የሚለው ጉልቶብኛል፤ ከዚ በፊት የሚነሱ አሉ አማርኛ ፊልም ላይ ሴቶችን በጅምላ ገንዘብ ይወዳሉ፣ወንዶችን ደሞ የሚፈልጉትን እስኪያገኙ ነው እያሉ ጅምላ ጭፍጨፋ ማካሄድ የለመድነው ነው.... አስቦበትም ይሆን ባላውቅም ሚስቴን ዳርኳት በጅምላ ዶክተሮችን ሰድቦል የገቡት ቃል በተቃራኒው ሁሉም እንደሚሰሩ ነግረውናል!!! ሌላው በግሌ በጣም የማልወደው ገፀ ባህርያት እራሶቸውን መግደል ነው ምን ለማስተላለፍ እንደሆነ ግራ ይገባኛል በተለይ ሴቶችን... ባላይ ደስ ይለኛል ነገሮችን የህይወት መጨረሻ ማድረግ ያስጠላል። ሳልናገር ማለፍ የማልፈልገው ሙሉ ታሪኩን ዝክዝክ አድርጎ መፃፍ ልክ አይደለም!!!

ሚስቴን ዳርኳት (Misten Darkuat) ቀን ተሌት ህይወት ለማትረፍ የሚደክሙ ህክምና ባለሙያዎች ሁላቹንም እናመሰግናለን ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ!!!

By: ከእኔ (Tsion Tamrat)


Comments

or to write a comment

Latest News and Articles

Ethiopian movie news and article - Asansiro
read more