Ethiopian Movies (2017-2018) (የኢትዮጵያ ፊልሞች በ2010)

በ2010 የወጡት ስራወች ውስጥ ምርጥ አስር አይደለም አምስት ማውጣት ዳገት የመውጣት ያህል ይከብዳሉ፤ በብዛት የወጡት ስራወች አይቱ መጨረስ እራሱ ከቀን ስራ ብዙም ባልተናነሰ ሁኔታ የሚከብዱ ነበሩ ለዚህ ዓመት መዳረሻ ለህዝብ የቀረቡ ስራወች የተሻሉ ነበር፡፡ በአንፃራዊነት አይቻቸው የወደድኩቸው እና በተመልካች የተሻለ እንደሰሩ የተመሰከራላቸው በገቢም ሻል ያሉ ቢከብድም እነሆ አስር ፊልሞችን መርጫለው፡፡ (እነዚህ ፊልሞች እስከ ነሃሴ ድረስ የወጡት ናቸው) 1 ውሃ እና ወርቅ፡ ደራሲ እና ዳይሬክተር መሀመድ አሊ በዝግጅት ኤርምያስ ንጉሴ አብሮት ነው መሀመድ ከዚህ በፊት በርካታ መጽሐፋትን ፅፎል ከሁለት አመት በላይ በዚህ ፊልም ደክሞል (ድርሰቱን ለመፃፍ የፈጀበት አይደለም) በቀረጻ እና በኤዲቲክ የወሰደበት ነው፡፡ ግሩም ኤርምያስ፣ሸዊት ከበደ፣አበበ ተምትም፣ንግስት ፍቅሬ... ተውነውበታል፡፡ እጅግ ቆንጆ ታሪክ ፊልሙን አይተን ከወጣን በኃላ የምንወያይበት፣ በሚያምር ፍልስፍና የተሞላ፣ ሁሉም ተዋንያን በብቃት የተወጡትበት፣ደስ የሚል ቀረጻ በጣም ቆንጆ ኮስቲዩም ያንበት ከሳለቸን የአማርኛ ፊልም ከፍ ያለ ፊልም ነው፡፡ አሁን ካለንበት የኢትዮጵያዊት ችግር እንደ አንድ የኪነ ጥበብ ውጤት እንደ መፍህቴ የደረሰ ፊልም ነው ያስተላለፈው መልክት የገዘፈ ነው ሀገር ወዳድ ሁሉ ቢያየው የሚያሰኝ ስራ ነው ዉሃ እና ወርቅ፡፡ 2 ወደ ኋላ፡ ደራሲ እና ዳይሬክተሩ ማሀሙድ ዳውድ ነው ከዚህ በፊት ነፃ ትግለ፣ያነገስከኝ፣ምነሼ፣እንደ ሀበሻ.... ፊልሙች ደራሲ እና ዳይሬክተር ነው፤ ሼፉ ፊልም ዳይሬክተር ነው እንዲሁም እቴጌ 2(ዘመቻ ድንግልን ፍለጋ)፣አየውሽ፣አሜን፣ጊዜ ግዙን... ፊልም ደራሲ ነው። ካሳሁን ፍስሃ(ማንዴላ)፣ዳንኤል ተገኝ፣አብራር አብዱ፣ሊዲያ ተስፋዬ.... ተውነውበታል፡፡ ፍልስፍና የያዛ ማንነት ላይ ያተኮረ ካሰለቹን ታሪኮች የወጣ በአቀረረብም ሻል ብሉ የመጣ ፊልም ነው፤ በተለይ ያስተላልፈው መልክት ለሀገርም የሚጠቅም ነው፣የቀረጻ ቦታውም ያማረ ነበር ሜካፕ ስራውንም አለማድነቅ ይከብዳል በጠቅላላ ተደክሞበት የተሰራ መሆኑ ያስታውቃል፡፡ እንደ ተጨማሪ በዚህ ዓመት በልዮ ሁኔታ ፊልም ማስመረቅ የናፈቀን ጊዜ ነበር በማረ ሁኔታ ከስመረቁ እጅግ በጣም ጥቂት ፊልሞች ውስጥ አንዱ ነው ወደ ኃላ፡፡ 3 ትህትና፡ ደራሲዋ ሊዛ ተሾመ ናት ከዚህ በፊት በመንገዴ ላይ ፊልም ደራሲ ናት፡፡ ዳይሬክተሩ ደግሞ ሰይፉ በቀለ ነው የበርካት ዘፈኖች ምስል(ክሊብ) ዳይሬክተር ነው በዳይሬክቲንክ ብቻ ሳይሆን በኤዲተር እና ሲኒማቶግራፈር ነው በኤዲትንህ እና በሲኒማቶግራፈር ፊልሞች ላይ ተሳትፎል፡፡ አዚዛ አህመድ፣አለባቸው መኮንን፣ዳንኤል ገበየው፣ዘነቡ ገስስ... ተውነውበታል፡፡ ታሪኩ ከማህበራዊ ህይወታችን የፈለቀ ነው ደፍሮ እንዲህ አይነት ሀሳብ ማንሳት ሁሉ ያሰመሰግናል ከማስተማር ባለፈ ለውጥ ማምጣት የሚችል ስራ ነው ጹሁፍ ላይ በደንብ እንደተሰራ ያስታውቃል ዳይሬክትንኩም ያማረ ነው ለዚህ ምስክሩ ተዋናቹ ናቸው ሁሉም በብቃት ነው የተወጡት በተለይ ሁኔታ አዚዛ አህመድን መጥራት ግን ይገባል፤ ለሁሉም ትህትና ለተመላካች የሚመጥን ስራ ሆኖ አግኝቼዋለው፡፡ 4 ጀማሪ ሌባ፡ ደራሲ እና ዳይሬክተሩ አብዲሳ ምትኩ ነው በድራስት አሚሪ በዲው አብሮት አለ አብዲሳ ከዚህ በፊት ታሽጉል፣አይገባንም፣ፍቅር ተራ፣የልጅ ሀብታም ፊልም ደራሲ እና ዳይሬክተር ነው እንዲሁ የጊዜ ቤት ዳይሬክተር ነው፡፡ ቃልኪዳን ታምሩ፣ሰሚር በዲው፣አንዱዓለም ተስፋዬ፣ሳምሱን አጅጉ(ጃፋር).... ሌሎችም ተውነውበታል፡፡ ቀለል ያለ ታሪክ ባማረ መንገድ የቀርበ፣ከእኛ ህይወት የተቀዳ አንድም የተጋነነ ነገር ያለሳየን ፊልም ነው፡፡ የተቀረጸበት ቦታም የአዲስ አበባን በቲቪ እና በብዛት ፊልሞቻችን ላይ ያማናየው የምናቀው የሚያመረው ገጽታ ላይ ነው፡፡ አዳዲስ ተዋንያችን በሚገርም ብቃት እንድናይ ያደረገን ፊልም ነው ፊልሙ ላይ ሁሉ የተሳተፉት ተዋናዮች ሆነው ነው የተወኑት፡፡ አስተማሪነቱም እንደተጠበቀ ነው ጀማሪ ሌባ፡፡ 5 የእናት መንገድ፡ ደራሲ እና ዳይሬክተሩ በሀይሉ ዋሴ(ዋጄ) ነው ከዚሀ በፊት ያ_ልጅ፣በልደቴ ቀን እና ዮቶጲያ ፊልም ደራሲ እና ዳይሬክተር ነው፤ አይራቅ እና ሰኔ30 ፊልም ደግሞ ዳይሬክተር ነው እንዲሁም የምን ልታዘዝ?ሲትኮም ደራሲ እና አዘጋጅ ነው። ሜላት ሰለሞን፣ደሞዝ ጎሽሜ፣ብርሃኔ ገብሩ፣መስፍን ሀይለእየሱስ... ተውነውበታል፡፡ ታሪኩን በሚያምር ዳይሬክቲንክ ነው የቀረበው ኢትጵያን ለማሳየት ብቻም ሳይሆን ለታሪኩም ጭምር የተቀረጸበት ቦታ ደስ ይላል ተዋንያችም ለተሰጠቸው ገጸ ባህሪ ብቁ ነበር፡፡ ዋጄን በድርሰት አለማድነቅ አይቻልም እንደ ሁሌው የእናት መንገድ ታሪኩም ከተለመደው የአማርኛ ፊልም ነጻ የወጣ ነው፡፡
6 ዋሻው
7 አንድ እኩል
8 ጉዳዬ
9 አስመላሽ
10ድንግሉ
ይህን ይመስላል (ከዚ ቀጥሎ የሚቀርቡት መተካወች ደሞ እስከ ጶጎሜ ናቸው በዚህ አመት(2010) ዕረፍት ለምኔ፣የሲኒማ ቤት ባንዲራ ነው ያስባለለን ካሳሁን ፍስሃ (ማንዴላ) በጣም ብዙ ደስ የማይሉ ፊልሞች ጥቂት ሻል ያሉ ፊልሞች ላይ ተውኖል በጥቂቱ ከሰራበቻው ወደ ኃላ፣ወርያ፣የኔማ፣ሰርቄሽ ልሂድ፣ጉዳዬ፣ዘናጭ፣አደረች አራዳ፣ጉራ ብቻ፣የወፍ ቋንቋ፣አስመላሽ፣መዳ፣ጃሎ... ይጠቀሳሉ ሌሎችም አሉ፡፡ በ2010 ሴቶች እንኩን ተከፋፍለው ነው የሰሩት የበዛ ሴት ተዋናይት የለም ሁለት ወይም ሶስት ስራ ነው የሰሩት አራት ፊልም በመስራት የበለጠቻቸው ማርታ ጎይቶም ናት፡፡ ሰራችልኝ፣አስመላሽ፣ፊያሜታ እና የወፍ ቁንቁ ላይ ሰርታለች፡፡ ሁለት ፊልም የቀረቡ ባለሙያዎች ደሞ ይሄው ከዚህ ቀጥሉ
1 ቡዙአየው አለሙ፡ ሰራችልኝ እና የወፍ ቋንቋ (ደራሲ እና ዳይሬክተር)
2 አቤል ሀጉስ፡ እንደ ባል እና ሚስት እና ዋሻው(ዳይሬክተር)
3 ነብዩ ተሾመ፡ አደረች አራዳ እና ጉራ ብቻ(ዳይሬክተር)
4 ሳሙኤል ተሻገር(የእምዬ ልጅ)፡ መዳ እና አንድ እኩል (ዳይሬክተር)
5 ኑር ሁሴን፡ አቶ እና ወይዘሮ እና ባለቤት (ደራሲም ዳይሬክተርም ነው)
6 እስማሄል ሀሰን(ኢሳም ሀበሻ)፡ ጎሚስታው እና የሰው ለህ (በድርሰት በቻ)
7 ውብሸት ስዩም፡ ድንግሉ እና ሚስቴን ዳርኳት(ድርሰት)
ጺዮን ታምራት


Comments

or to write a comment

Latest News and Articles

Ethiopian movie news and article - Asansiro
read more