Nov. 29, 2016, 12:44 a.m. by EtMDB
አነሰም በዛም ፊልሞቻችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በሀገራችን ተወዳጅነታቸውና ተጽዕኗቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ደስ የሚያሰኝ ነው፣ እንደኔ እንደኔ እንደ ጤዛ ,ረቡኒ, ገዳይ ሲያረፋፍድ እና ሌሎችም ተወዳጅ ፊልሞቻችን የመታየት እድሉን ቢያገኙ በመላው አፍሪካ ተቀባይነትን ሊያገኙ እንደሚችሉ እምነቴ ነው ማን ያውቃል በቅርቡ የነ ሩታ መንግስታብ ፣ ሃናን ታሪክ፣ ግሩም ኤርምያስ አንዲሁም ሌሎች ዝነኞች አርቲስቶቻን በአፍሪካ ሃገራት ዝናን አግኝተው በቲሸርቶች፣ በደብተሮችና በተለያዩ ህትመቶች ላይ እንደ ዛራና ቻንድራ እናያቸው ይሆናል. ለነገሩ ምን ያንሳቸዋል? Call me crazy, but "I have a dream" ህልሜም ፊልሞቻችን በአፍሪካ ሃገራት ተወዳጅነትን አግኝተው በተለያዩ የአፍሪካ መንደሮች ፊልሞቻችን በትርጉም ሲታዩ ማየት ነው ግን ከዛ በፊት የታዘብኩትን ልናገር በቅርቡ የወጡ ፊልሞች subtitle ማካተታቸውን ብወደውም በተወሰኑት ፊልሞች ላይ ያሉት subtitles ከማነሳቸው የተነሳ ለማንበብ ያስቸግራሉ ስለሆነም የሚመለከተው አካል በsubtitle ላይ በትኩረት እንዲሰራበት ለማሳሰብ አወዳለው ታድያ የትኛው ፊልም ኣዘጋጅ (producers) ነው ፋና ወጊ ሆኖ ፊልሞቻችንን ወደተለያዩ የአፍሪካ አህገራት በመላክ ባህላችንን አና የኑሮ ዘይበኣችንን የሚያስተዋውቀው ?