Surafel Kidane (ሱራፌል ኪዳኔ)
ሱራፌል ኪዳኔ መጋቢት በ1978 ዓ.ም ከእናቱ ወ/ሮ አስቴር ደስታ ተወለደ ፡፡ ምስራቅ ታሪኩ እና ሚካኤል ታሪኩ የሚባሉ ወንድምና እህት አለው፡፡ ለአያቱ ወ/ሮ ጣያቱ ተሰማ እና ለአጎቱ ተስፋዬ ደስታ የተለየ ፍቅር እንዳለው የሚገልጸው ሱራፌል ኪዳኔ የማንበብ ልምዱን ያገኘው በሳደገው አጎት ምክንያት ነው፡፡ ሱራፌል የሚኖረው ከባለቤቱ ከአርቲስት ትዕግስት ተስፋ ጋር ሲሆን ትዕግስት ተስፋ በፍቅርና ፖለቲካ ፊልም ዋና ተዋናይት ሆና ሰርታለች በተጨማሪም ወደሀገር ቤት ፊልም ላይ በረዳ ተዋናይነት የሰራች ሲሆን የተለያዩ ስራዎች ላይም ተሳትፋለች ፡፡ ጥንዶቹ በአሁን ሰአት ቅዱስ የተባለ ወንድ ልጅ አፍርተው በፍቅር እየኖሩ ይገኛሉ ፡፡ በልጅነቱ የተለያዩ ክህሎቶችና ችሎታዎች ስለነበረው ከጥበቡ ባሻገር በእግር ኳስ ትልቅ ቦታ ይደርሳሉ ከሚባሉ ወጣቶች መሀከል አንዱ ነበር ፡፡ ሀይኮፍ ለሚባል ቡድንም በመጫወት በአዲስ አበባ እስፖርት ኮሚሽን እድሚቸው ከ18 አመት በታች ለሆኑ ወጣቶች በተዘጋጀው ዋንጫ ቡድኑ አሸናፊ ሲሆኑ የማሸነፍያውን ግብ ያስቆጠረው እሱ ነበር፡፡ ነገር ግን እግሩ ላይ በደረሰበት የመሰበር አደጋ ከእግር ኳስ ለመራቅ ተገዷል፡፡ በትምህርቱም ቢሆን በደረጃ የሚወጣ እስፔሻል ተማሪ ነበር ፡፡ ሱራፌል ኪዳኔ ሲኒማ አውቶግራፊ ፣ ኤዲቲንግ እዲሁም አፍተር ኤፌክትን ሞያዎችን በመማር የተለያዩ ሰራዎችን ሰርቷል በመስራ ላይም ይገኛል ፡፡ በአሁን ሰአት ደግሞ በባህር ዳር ላይ የመጀመርያ የሆነውን አስኳላ የፊልም ማሰልጠኛ ተቋምን ከወንድሙ ኤርሚያስ ፍቅሬ ጋር በመክፈትና እውቅናን በማግኘት በአስተማሪነት ሞያ ስክሪፕት ራይቲንግ ፣ ዳይሬክቲንግ ፣ ትወና ፣ ሲኒማቶግራፊ እና ኤዲቲንግ ኮርሶችን እያስተማረ ይገኛል ፡፡
Born: March 1986 in Addis Ababa
![]() |
Jan. 1, 2015 |
![]() |
Jan. 1, 2015 |