Artist Mulualem Getachew Picture
26 2 0

Actor | Director | Producer | Writer

የተወለደው ሚዛን ተፈሪ ነዉ ከሁለት አመቱ በኋላ አዲስ አበባ ኮተቤ ሰፈር ነው ያደገው፡፡ከ1-4 ኪዳነምህረት ከ5-12 ደጃዝማች ወንድራድ ተምሯል፡፡ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቲያትሪካል አርት እንዲሁም የሙዚቃ ትምህርቶችን ወስዷል፡፡በትምህርት ቤት ቆይታውም በተለያዩ ክበባት ተሳታፊ ነበር፡፡
የኪነ ጥበብ ፍቅሩ አድጉ አሁን ላይ ተዋናይ፣ደራሲ እና ዳይሬክተር አድርጎታል:: ከፊልም ስራው በፊት ጎበዝ ድምፃዊ እና የሙዚቃ መሳራያ ተጫዋች የሚሆን ይመስል ነበር የፊልም ስራው አመዘነና በርካታ ፊልሞችን በወጣትነቱ በማቅረብ ከፊት አለ። በይበልጥ የታወቀው 300ሺ ላይ በረከትን ሆኑ ሲተውን ነው።
አማተሮቹ፣አንድዜ የተሰኙ የመድረክ ስራዎችን ሰርቷል እስካሁን ከ20 በላይ ፊልሞች ላይ በትወና እንዲሁም 10 የሚሆኑ ፊልሞችን ዳይሬክት አድርጓል፡፡
የተወለደው ሚዛን ከተማ ቢሆንም እድገቱ ግን አዲስ አባ ኮተቤ አካባቢ ነው ። የ 9ኛ ክፍል ተማሪ እስከነበረበት ጊዜ የወደፊት እጣውን ገና በውል አልተመነም ነበር። ከዚያ በኅላ ግን በትምህርት ቤታቸው በተለያዩ ክበባት መሳተፍ ጀመረ።በእርግጥ በወቅቱ አዚህ ደረጃ ላይ አደርሳለው ብዬ ባልገምትም ዛሬ በስራዎቼ ሰዎች ተቀብለውኝ ሳገኝ ለካ ለኔ መክሊት ይህ ነበር ብያለሁ ይላል። ወጣቱ የፊልም ደራሲ፣አዘጋጅና ተዋናይ ሙሉአለም ጌታቸው።ትወናውን አስቀድሞ ወደ ጥበቡ የገባው ሙሉአለም አየቆዬ ከትወናው አስበልጦ ትኩረት እና ስኬትን ያገኘባቸው የፊልም ደርሰትና ዝግጅት ስራዎችን አጠናከረ። በትወና ደረጃ የመጀመሪያ ፊልሙ ያለሴት ሲሆን ከዚያ በኅላ አማን ፣ሩጫዬን ጨርሻለው ፣ ቺኮሎጂ ፣ 3+1 ፣ ጀግኖቹ፣ አንላቀቅም ፣ ተወዳጅ ፣ የሰማይ ረፈግታ ፣ ሰምታ ይሆን እንዴ? ፣ ወ/ት ድንግል ፣ ጥለፈኝ ፣ ሃለም በቃኝ ፣ ሁለት አረንጎዴ ጠርሙሶች ፣ያየ አለ ፣እውነት ሀሰት አና የልጅ ሀብታም ላይ ተውኗል። በአዘጋጅነትና በድርሰት ደግሞ 300ሺ አገርሽ አገሬ ፣ አዲስ እንግዳ ፣ አፄ ማንዴላ ፣ ሩጫዬን ጨርሻለው ፣ ሚስቴን ቀሙኝ ፣ ጥለፈኝ ፣ አለም በቃኝ ፣ ሀገርሽ ሀገሬ እና እንደ እናት የሰራቸው ናቸው። የቻርዳ ፊልም ኘሮዳክሽን መስራችና ባለቤትም ነው

Nick name: Mule

Photos & Videos

Recommended Artists