Artist Yigerem  Dejene Picture
5 0 0

Actor

በርካቶች መልካም ስነ-ምግባር ያለው ተዋናይ ነው ይሉታል። በ1972 ዓ.ም አሮጌው ቄራ አካባቢ ተወልዶ ያደገው የዛሬው የመዝናኛ አምድ እንግዶችን በፊልም ደረጃ ዕጣ-ፈንታ፣መስዕዋት፣ አዲስሙሽራ፣ 70/30፣ አስክሬኑ፣ ውበት ለፈተና፣ የትሮይ ፈረስን ጨምሮ ከ30 በላይ ፊልሞችን ሰርቷል። የጀግኖች ማህደር፣ ቅድስተ-ካናዳ፣ ሜዳሊያ፣ ምዕራፍ አራት፣ የብዕር ስምን ጨምሮ በቅርቡ በሚከፈተው የደራሲ ውድነህ ክፍሌ “የደመና ዳንኪረኞች” ቴአትሮች ላይ ተውኗል። በቲቪ ድራማዎቹ ከሚጠቀሱለት መካከል ሾፌሩ፣ አንድ ዕድል፣ ያልተሄደበት መንገድ፣ ሰው ለሰው እና አሁን በቅርቡ በኢቤኤስ ቲቪ በመታየት ላይ በሚገኘው “ሞጋቾቹ” ላይ ተጫውቷል። ይህ ሲባል ግን ከ40 በላይ የሚሆኑ አጫጭር የቴቪ ድራማዎችን ሳይጨምር ነው። ይህ ሰው በሬዲዮም አለ፤ አሁን ድረስ የሚታወስባቸውን ጨምሮ ግራረ አምባ፣ የደወል ድምፆችና በሸገር ኤፍ ኤም እየተላለፈ በሚገኘው የኛ ድራማ ላይ በብቃት እየሰራ ይገኛል።

Born: January 1979 in Addis Ababa

Nick name: Aster

Recommended Artists