Seyfu Fantahun
(ሰይፉ ፋንታሁን)
Actor
|
Director
|
Producer
|
Writer
ውልደት እና እድገቱ በምስራቅ ኢትዮጲያ ሐረር ነው።
የትወና ህልሙን ከተወለደበት መንደር ትያትሮች በማሳየት ይጀምራል ከእሱም በመቀጠል አዲስ አበባ መጥቱ ከእንግዳ ዘር፣አስረስ በቀለ፣ሱራፌል ወንድሙ ....ጋር ትያትሮችን፣አጫጭር የቲቪ ድራማዎችን መስራት ቀጠሎል ጉንለጉን ሆሊውድ መፅሄት ያዘጋጅ ነበር።
ከትወናው በላይ ይበልጥ የሚታወቀው በጋዜጠኝነት ነው። በኤፍኤም ታሪክ የመጀመርያ የሆነው 97.1 ላይ አዲስ ዜማ ፕሮግራም ጀመረ። ከጓደኞቹ ጋር ከእሱ በኃላ በሸገር 102.1 ላይ ታድያስ አዲስ በሚል ፕርግራም መጠርያ የራሱን ዝግጅት ማቅረብ ቀጠለ በአሁን ሰዓት የራሱን ጣብያ ማለትም ኢትዮ ኤፍኤም 108.4 ላይ እየሰራ ይገኛል።
በቲቪ ደግሞ ETV music በድሮ ኢቲቪ በአሁኑ ኢቢስ ዕሁድ 11 ሰዓት ላይ ከብርሃኔ ንጉሴ እና ሱራፌል ወንድሙ ጋር ያቀርብ ነበር። ከዛም በማስቀጠል በቲቪ ህይወቱ ወደ ኢቢኤስ አቅንቱ እስካሁን ዕሁድ ምሽት 3ት ሰዓት ሰይፋ በ EBS እያቀረበ ነው። በፊልም ደግሙ ይፈለጋልን በድርሰት፣በዝግጅት፣ፕሮዲሰር እንዲሁም ተዋናይ ሆኑ ለተመልካች አቅርቦል።