Blogs & Articles

Asansiro ( እንሳሮ (፪፻፻፲፪ ዓም) ፊልም ላይ እሚያብረቀርቅ ድፍረት የተበታተነበት ምስል ስኩነቱን እራስአጥፍቶ አበላሸ፤ ወይም እራስአጥፊ አኗኗርአችን ላይ ተሳለቀ?)

የተዋናይዎች ትትረት፣ እንከኑን ያላሳየ አርዖት፣ ደግ ስክሪብት፣ በምስጋና-ጋባዥ ገጽማያ-(ስክሪን) ቆየ። ያንቆረቆረው የደስታ አሽከርነቱ ቢኖርም፣ በፍፃሜው ግን በግድንግድ ሽንቁርዎች ተቦትርፎ እንዳይሆኑት ሆኖ ምንአልባት የነተበ ፊልም። እሚደነቁ ለመመልከት እሚያገዱ -ገጽታዎች

  • ደግ ደረጃ ስክሪብት፣
  • የትርክቱ ደግ የመንቆርቆር አቅም፣
  • ደህና ሹፈትዎች እና ቀልዶች፣
  • ልባምአዊነት-(ከሬጅ) በትርክቱ አካሄድ እና ገጸባህሪዎች፣
  • ከቶ የጀማሪ ባለሙያ እማይሰኝ ዓርትዖት፣
  • አልፎአልፎ እሚጠፋ ቢሆንም የእራሱ-ለእራሱ እሚስማማ ምንምአይሌ-(ፌር) አዝማችነት-(ዳይሬክቲንግ) ላይ እሚኩራራ
  • ከቶ ከማስቀየም-የራቀ የአብይ ተዋናዮች ካሜራ ፊት ግርግሮች፣
ግን ...

Yegir Esat Drama (የእግር እሳት: እሳት ሀሳቦች)

አንድ ውብ የቴሌቭዥን ተከታታይ ድራማ ወደናል፡፡ ወደን ደግሞ ፍቅራችን ከቴክኒክ ረገድ፣ የድራማውን ልቡ ምኑ ላይ ይሆን የሚለው የሀሳብ አይነት ጋር፣ የተዋናዮቹ የአልባሳት አለባበስ እና ትርጋሜ÷ በቦታዎች ውስጥ ያላቸው አቀመማጥ ትርጋሜን በሰም መንገድ ለማየት እንጥራለን፡፡መማረኬ ነው የሚያስሞነጭረኝ፡፡
በድህረ የስርጭት ዘመን (Post broadcast time) የቴሌቭዥን ተከታታይ ድራማዎች የመገናኛ ብዙኃን አይነተኛ መልክ ናቸው፡፡ በፕሮግራም ድልድል ውስጥ መቼ እና ምን አይነት መሆን እንዳለባቸው ሊሂቃንን የሚጋብዙ ጉዳዮች ሆነዋል፡፡ የቴሌቭዥን ጣቢያዎችም በተመልካቾቻው ላይ የገበያውን ድራሻ ለመውሰድ መፎካከሪያ የፕሮግራም አንቀፃች ናቸው፡፡ (audience and market share)
ለኢትዮጵያ ዘመኑ የቴሌቭዥን መሪነት የሚታይበትም ነው፡፡ ...

CANAL+ with Nolawi Film Production (የፈረንሳዩ ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ የፊልም ቻናል ሊከፍት ነው)

የፈረንሳዩ የቴሌቪዥን ድርጅት ካናል + ኢትዮጵያ ውስጥ የራሱን ቻናል ከፍቶ ፊልሞችን ለማሳየት የሚያስችለውን ስምምነት ከድርጅታቸው ጋር መፈራረሙን የኖላዊ ፊልም ፕሮዳክሽን ሥራ አስኪያጅ ሐኒ ወርቁ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፊልም ፕሮዲውሰሮች ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት ቢንያም አለማየሁ በበኩላቸው፣ ካናል ፕሉስ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የውጪ ድርጅቶችም የኢትዮጵያን ፊልሞች ለማሳየት ፍላጎት ኖሯቸው ወደ ማህበራቸው መምጣታቸውን ይናገራሉ።
የሚከፈተው ቻናል የተመረጡ የኢትዮጵያ ፊልሞች ብቻ የሚታዩበት መሆኑን የሚናገሩት ሥራ አስኪያጇ፤ ለተወሰኑ ወራት አዳዲስ ፊልሞችን በመከራየት ለማሳየት መስማማታቸውን ገልፀዋል። ሥምምነቱ የተለያዩ ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ መሆኑን የገለፁት ሥራ አስኪያጇ፤ ከፕሮዲውሰር ማኅበር ጋር በመሆን የሚታዩ ፊልሞችን የመምረጥ ሥራው...

Our disappointing movie industry (ሞቶ ያልቀበርነው ፊልማችን!)

«ዘውድአለም ታደሠ»
እንዴት አደራችሁ ጎበዛዝት? እኔ አላሁ አክበር ሳይል ከእንቅልፌ ነቅቼ እስኪነጋ ድረስ ዩቲዩብ ላይ የተለቀቀ የአማርኛ ፊልም ከፈትኩ። ጎበዝ! እኛ ኢትዮጵያውያን የፊልም ነገር ምንም አልተዋጣልንም። የፊልሙ ኢንደስትሪያችን (ኢንደስትሪ ከተባለ) ከቀን ወደቀን ተስፋ አስቆራጭ እየሆነ ነው። ድርሰቱ፣ ፕሮዳክሽኑ ምናምን ምንለው አይደለም ባጭሩ ፊልም ኢንደስትሪያችን ሞቷል! ወደድንም ጠላንም ቀብሩ ተራዝሞ ነው እንጂ ፊልማችን ሞቷል!

አሁን አሁን ተስፋ ቆርጬ ተውኩት እንጂ እስከቅርብ ግዜ ድረስ ያለመታከት ደህና ፊልም ፍለጋ የሲኒማ ቤት ደጅ እ...