Blogs & Articles

Meba (መባ ፊልም ኪሳራችን በጊዜና በገንዘብ ብቻ የሚለካ አይደለም )

ትላንት እንደው በስህተት ልበለው መሰል እግሬ እንዳመራኝ በቅርቡ የተመረቀውን ‘መባ’ ፊልም ለማየት ወደ አንዱ ሲኒማ ቤት ጎራ ማለት….ምክንያት ነበረኝ፡፡ ‘ረቡኒ’ የተባለውን ፊልም ካየሁ በኋላ ሀገርኛው ስሜት ይበልጥ ያየለበት ፊልም ከመሆኑ አንጻር በተለይም እንደ ፊልም አብዛኛውን element የያዘ በመሆኑ በነካ እጅ ብዬ የዚሁ የረቡኒ ደራሲ የደረሰችውን መባ ፊልም ማየት … ውስጤ የቀረ ነገር በመኖሩና በረቡኒ የትዝታ ቀዳዳ ውስጥ እንደማጮለቅ መስሎ ስለታየኝም ጭምር ነበር፡፡

በህይወታችን እንደዚህ አይነት የስሜት ግጭቶች ፈትነውን ያውቁ ይሆናል፡፡ ልክ ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ከፍቅር እስከ መቃብር...

Short film competition (የአጭር ፊልሞች ውድድር ሊካሔድ ነው)

የአጭር ፊልሞች ውድድር በሰባት ዘርፎች የሚካሄድበት የቴሌቪዥን መርሐ ግብር በቅርቡ ይጀመራል፡፡ ከአዲስ አበባ የተውጣጡ ወደ አንድ ሺሕ የሚጠጉ ወጣቶች የሚሳተፉበት ውድድሩ፣ በምርጥ አጭር ፊልም፣ ተዋናይ፣ አዘጋጅ፣ አርታኢ፣ የካሜራ ባለሙያና ማጀቢያ ሙዚቃ ዘርፎች ይካሄዳል፡፡ ተወዳዳሪዎች በቡድን ተከፋፍለው የሦስት ደቂቃ ፊልም ያዘጋጁና በሦስት ዙር ለዓመት ይወዳደራሉ፡፡ በአሸናፊው ቡድን የተሠራው አጭር ፊልም ወደ ፊቸር ፊልም እንደሚቀየር የውድድሩ አዘጋጆች ቲሀርቅ ኢንተርቴመንትና የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በጋራ ቅዳሜ ኅዳር 3 ቀን 2009 ዓ.ም. በፓኖራማ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል፡፡

የቲሀ...

Our Movies in Africa (ፊልሞቻችን በአፍሪካ መንደር)

አነሰም በዛም ፊልሞቻችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በሀገራችን ተወዳጅነታቸውና ተጽዕኗቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ደስ የሚያሰኝ ነው፣ እንደኔ እንደኔ እንደ ጤዛ ,ረቡኒ, ገዳይ ሲያረፋፍድ እና ሌሎችም ተወዳጅ ፊልሞቻችን የመታየት እድሉን ቢያገኙ በመላው አፍሪካ ተቀባይነትን ሊያገኙ እንደሚችሉ እምነቴ ነው ማን ያውቃል በቅርቡ የነ ሩታ መንግስታብ ፣ ሃናን ታሪክ፣ ግሩም ኤርምያስ አንዲሁም ሌሎች ዝነኞች አርቲስቶቻን በአፍሪካ ሃገራት ዝናን አግኝተው በቲሸርቶች፣ በደብተሮችና በተለያዩ ህትመቶች ላይ እንደ ዛራና ቻንድ...

Acting is believing (ትወና ማመን ነው)

መነሻ ሃሳብ- በግድ ሊያሳምኑን ከሚጥሩ ተዋንያን ትወና
ምንም አይነት የትወና ቴክኒክም ይሁን ስታይል ተከታይ ይኮን ትወና በ"ማመን" ላይ የተመሰረተ ጥበብ ነው።...በትወና ስራ ውስጥ የአንድ ተዋናይ የመጨረሻ ግብ የተሰጠውን (የሚወክለውን) ገፀባህሪ በአሳማኝ ሁኔታ ለተመልካች ማቅረብ ነው።...ትወና ባመዛኙ ያልሆኑትን ሆኛለው ሆኖብኛል ብሎ ተመልካችን የማሳመን ጥበብ ነው።በአጭር ቋንቋ ተዋንያን ተመልካችን ሲኒማ ቤት 'የሚጠሩት' "ና ላሳምንህ" ሊሉት ነው።...ታድያ በዚህ የማሳመን ጥበብ ውስጥ ቀዳሚው ነገር ተዋናዩ በገፀባህሪው ማመን አለበት።ለማሳመን ማመን ይቀድማልና።..."ውስጥህ ያላመነበትንና ስሜት ያልሰጠህን ነገር ለሌሎች ለማሳየት ፈፅሞ አትሞክር!"...ይላል የዘመናዊ ትወና ፈር ቀዳጅ እንደሆነ የሚታመነው ሩሲያዊው የትወና ምሁር ስታንስላቭስኪ።
ወ...