Blogs & Articles

Eyayu the Fungus-Part 2 ( "እያዩ ፈንገስ- ፌስታሌን" ባለ አንድ ሰው የሙሉ ሰዓት ቴአትር -ክፍል ፪)

....ከክፍል ፩ የቀጠለ

ያለንበት ወቅት ምንም እንኳ በሀገርኛ ፊልሞች እንደ አሸን መፍላት ምክንያት ቴአትራችን የመዋጥ ዕጣ ፈንታ ቢገጥመውም በተለያየ አጋጣሚ ለማንሰራራት እየሞከረ ይታያል፡፡ ባለ አንድ ሰው የሙሉ ሰዓት ተውኔት ፣ ባለ ሁለት ሰዎች ዘመናዊ ቴአትር በአዲስ አቀራረብና ይዘት የቴአትርን ሌላ ገጽታ ማሳየት ጀምረዋል፡፡ ከተለመደው የቴአትር አቀራረብ ወጣ በማለት ማሳያ ቦታውንም ጭምር በመቀየር ከቴአትር ቤት ወደ ፊልም ቤቶችና ሆቴሎች በማሻገር የተመልካቹን ፍላጎት በሌላ አቅጣጫ የማሟላት አካሄድን ዘይደዋል ማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡

የ21ኛው ክፍለዘመን ማብቂያ አዲስ ዕይታ ...