Must watch movies in 2016/2017 (2009 በፊልም አለም)

2009 በፊልም አለም፦ ከ2008 መጨረሻ ላይ የነበረውን የተመልካች መጥፋት እና የፊልም ምርት መቀዝቀዝ በደንብ 2009 ነበር ማለት ያስደፍራል። ከዚህ በፊት ከነበሩት አመታት አንፃር ብዙ ፊልም ለተመልካች አልቀረበም፣በርካታ ሲኒማ ቤቶች መዘጋታቸውን ቀጥለዋል፣ፊልም ፕሮዲዮስ የሚያደርጉ ባለሀብቶች መሸሽ በይበልጥ ቀጥለዋል፣ በየአመቱ ይካሄዱ ከነበሩ ሽልማቱች አንዱ የሆነው የኢትዮጲያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌሲቲቫል በዚህ አመት አልተካሄደም፣ለተመልካች ከቀረቡ ፊልሞች ውስጥ 25% ብቻ ናቸው ባለሙያን አክብሮ ማስመረቅ የቻሉት... ሌላም መጥቀስ ይቻላል ከምንም በላይ የዘንድሮ አመት ፊልሞች አስደንጋጭ ነገር የነበረው በዚህ አመት የወጡ ፊልሞች ከወጡ እንኳን በትክክል 3ት ወር ሳይሞላቸው የመሰረቅ አደጋ ያጋጠማቸው ከዚህ በፌት ከነበረው በላይ ዘንድሮ ቁጥራቸው በእጁጉ ጨምሮል በአጠቃላይ 2009 አመት ላይ ከ70 የማይበልጡ ፊልሞች በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ውስጥ ለተመልካች እንደ ቀረብ ይታመናል።

በ2009 ከወጡ ፊልሞች በመሪ ተዋናይነት ብዙ ፊልም የተወኑት በሴት ሰላም ተስፋዬ 6ት ፊልም ነው እነሱም፦ የልብ ቋንቁ፣3ትማዕዘን ሁለት፣የተከለከለ፣ያበደች የአራዳ ልጅ 3፣እውነታ እና አፄ ማንዴላ ላይ ነው። በወንዱች ደግሙ በመሪ ተዋናይነት ብዙ ፊልም የተወነው ካሳሁን ፍስሀ ማንዴላ ነው እሱም 6ት ፊልም ላይ ተውኖል እናሱም፦ ወራጅ አለ፣ደስ እንዳለሽ፣ፍቅር ያሸንፋል፣የት ነበርሽ፣ማያ እና ይዳኘኝ ያየ ላይ በመተወን ነው።

በዚህ አመት ከወጡ ፊልሞች ውስጥ መታየት ያለባቸው 15ት ፊልሞች

  1. አፄ ማንዴላ፦ ከዚ በፊት ብዙ ፊልም በሰጠን በሙሉዓለም ጌታቸው የተሰራ ነው በኢትዮጲያ የመንግስት ሲኒማቤት ታሪክ ከ6አመት በፊት በተመልካች ብዛት የተያዘ ሪከርድ መሰበር ያቻለ ፊልም ነው፤ ታሪኩ መርካቶ ላይ ተጀምሮ መርካቶ ላይ የሚያልቅ ነው ጉልበት እና ፍቅር ያለቸውንም ሀይል ያሳያል። ይሄ ፊልም ታሪኩ ለሁላችንም እጅግ ቅርብ ታሪክ ነው የታሪኩ አካሄድ፣መቼቱ፣ተዋንያኖቹ፣ቀረፃው በአጠቃላይ ፊልሙ ፕሮዳክሽኑ ቻርዳ ሆነ ዳይሬክተሩ ሙሉዓለም ከዚ በፊት ከሰሩት ከፍ ብሎ ይታያል። በተመልካች ብዛትም በአጭር ጊዜ ከሁሉም ፊልሞች በልጡል።
  2. ሶስት ማዕዘን ሁለት፦ በኢትዮጲያ ፊልም ትልቅ ቦታ ያለው አሁን ሎሬት የሚል ማዕረግ ያገኛው ቴዎድሮስ ተሾመ ፊልም ነው መቼቱን አዲስ አበባ እና አሜሪካ ዲሲ ውስጥ ያደረገ ሲሆን ታሪኩ ደግሙ ከአንድ የቀጠለ ሲሆን በይበልጥ የአብሮነትን ጥግ የሚያሳይ ፊልም ነው። ለሀገሩ ውስጥ ገብያ ብቻ ሳይሆን ለአጉራዊ እና አለም አቀፍ ውድድሮች ታስቦ የተሰራ ፊልም ነው፤ ታሪኩ ከምንም ጊዜውም በላይ በሚያስፈልገን ጊዜ የመጣ ነው፣ቀረፃውም በሚያምር ሁኔታ የተሰራ ነው፣ተዋንያኑም በተለይ ሙሉቀን ተሾመ የሚያስገርም ትወና ያሳየበት ነው በብዙ መስፈርት ምርጥ ብለን መጥራት የምንችለው ፊልም ነው እንዲሁም ብዙ ተመልካችም የነበረው ነው።
  3. ታዛ፦ የንስር ዓይን እናዳላት በሚታመነው ቅድስት ይልማ ተፅፎ የተዘጋጀ ፊልም ነው፡ ታሪኩ የደርግ ወታደር የሆነው ወግ አጥባቂ ሰው ወደ ቤቱ ሲመለስ ከምታጋጥመው ከኩባ ተመላሽ የሆነች ተማሪ ጋራ ያለውን ያሳያል። ፊልሙ ለዓይን በማይከብድ ሁኔታ ማስተላለፍ የፈለገውን ሀሳብ ባልሳተ ሁኔታ የተሰራ ነው፤ የቀረፃ ቦታው በዚህ አመት ካየናቸው ፊልሞች ሁሉ ያማረ ነው፣የታሪኩ የሚያስፈልገውን ሜካፕ እና አልባሳት በሚገባ አሳክቱል፣ቀረፃውም እጅግ ያማረ ነው፣ተዋንያኖችም (በተለየ ደግሙ ዘሪቱ) በሚገባ ተወጥተዋል።
  4. ማያ፦ ከዚህ በፊት በድርሰትም በዝግጅትም 3ት ፊልም ያቀረበው የልዑል ሰፈፈ(ቢኒ) ፊልም ነው። በትራፊክ አደጋ ላይ በዋናነት አተኩሮ የተሰራ ፊልም ነው ታሪኩም ካለመጠንቀቅ ሆነ በአደጋ የሚከሰቱ የመኪና አደጋዎች የምንያህል ነገሮችን እንደ ሚያመሰቃቅሉ ያሳያል። ታሪኩ እጅግ በጣም አስተማሪ ከመሆኑ በላይ ችግራችንን መቀነስ የሚችል ነው፣ተዋንያኖቹ ሁሉም ማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ምርጥ ነበሩ፣አንዳንድ የኮንቲኒት ችግሩች ውጪ ፕሮዳክሽኑም ጥሩ ነበር፣ታሪኩን እንድናይ የተደረግንበት ሁኔታ ቆንጆ ነው።
  5. እንቆጳ፦ በኢትዮጲያ ትያትር ሆነ ፊልም ትልቅ ቦታ ያላት አለምፀሀይ በቀለ ያዘጋጀችው ፊልም ነው፤ ታሪኩ ህገወጥ ስደት ውስጥ የሚፈጠሩትን እና ከሀገር ተወጥቱ ሁሉ የሚያጋጥመውን ነገር በሰፋ ሁኔታ የሚያሳይ ፊልም ነው። መቼቱ ሰፊ ነው ታሪኩ መርገጥ ያለበትን ቦታ ሁሉ ከሀገር ውጪ እየሄዱ አሳይተውናል፣ እንድ ከዚ በፊት እንደጠራናቸው ሁሉ ታሪኩ ቆንጆ ነው ስደት ላይ ያለውን ነገር ከዚ በፊት ያላየናቸውን አሳይቱናል፣ በፕሮዳክሽን ስራውም እጅግ የተሳካ ነው እንደ ሱስት ማዕዘን ሁሉ ለአለም አቀፍ ውድድሮች በቂ ነው።
  6. ቀሪ 10 ፊልሞች
  7. ስስት ሁለት
  8. ያበደች የአራዳ ልጅ ሶስት
  9. ባለ ጉዳይ
  10. እንደ እናት
  11. ላብጦስ
  12. የእግዜር ድልድይ
  13. የልጅ ሀብታም
  14. ያልተሾፈ
  15. ቶክሲዶው
  16. የተከለከለ

ተስፋ የተጣለባቸው ተዋንያን ከሴት እና ከወንድ
ከሴት ማራማዊት ፍፁም በማያ ፊልም፦ ማራማዊት ከዚህ በፊት እንደ ዋና ተዋናይ ሆና ባትተውንም ከእናቱ አዚዛ አህመድ ጋር አንዳንድ ፊልሞች ላይ እንደ ማያ ብዙ ፓርት ባይኖራትም ተውናለች። ለመጀመርያ ጊዜ ከእናቱ ተለይታ በርካታ ፓርት ይዛ የተወነችበት ፊልም ነው ካራክተሮ በእሱ እድሜ ላለ ታዳጊ ህፃን እጅግ ከባድ ነው ግን ከመጠን በላይ ተውጥታዋለች ማለት ያስደፍራል እኛም ምንም እንኳን ኑሮዋን በአሜሪካ ብትደርግም ከትወናው የመራቅ እድሉ ሰፋ ቢልም ተስፋ ጥለንባታል።
ከወንድ ዘላለም ብርሀኑ(ማንዴላ) በአፄ ማንዴላ፦ ዘላለም ከትወና በፊት ፊልሞች ላይ ፕሮዳክሽን ስራ የሚሰራ ባለሙያ ነው ወደ ትወና የተቀላቀለው በዚህው አመት ከወጡ ፊልሞች ውስጥ አንዱ በሆነው በትንሽ ገፀ ባህሪ ወራጃ አለ ላይ ነው። መሪ ተዋናይ ሆኑ መጀመርያ የሰራው ፊልም ይሄው አፄ ማንዴላ ነው ትወናውንም በሚገባ ተወጥቱታል ማለት ያስደፍራል በመጀመርያው ስራው ቆመን እንድናጨበጭብ አድሮጉናል እና በቀጣይ ስራው ለማየት እኛም ተስፋ ጥለንበታል።

Tsion Tamrat


Comments

or to write a comment

Latest News and Articles

Ethiopian movie news and article - Asansiro
read more