Asansiro ( እንሳሮ (፪፻፻፲፪ ዓም) ፊልም ላይ እሚያብረቀርቅ ድፍረት የተበታተነበት ምስል ስኩነቱን እራስአጥፍቶ አበላሸ፤ ወይም እራስአጥፊ አኗኗርአችን ላይ ተሳለቀ?)

የተዋናይዎች ትትረት፣ እንከኑን ያላሳየ አርዖት፣ ደግ ስክሪብት፣ በምስጋና-ጋባዥ ገጽማያ-(ስክሪን) ቆየ። ያንቆረቆረው የደስታ አሽከርነቱ ቢኖርም፣ በፍፃሜው ግን በግድንግድ ሽንቁርዎች ተቦትርፎ እንዳይሆኑት ሆኖ ምንአልባት የነተበ ፊልም። እሚደነቁ ለመመልከት እሚያገዱ -ገጽታዎች

  • ደግ ደረጃ ስክሪብት፣
  • የትርክቱ ደግ የመንቆርቆር አቅም፣
  • ደህና ሹፈትዎች እና ቀልዶች፣
  • ልባምአዊነት-(ከሬጅ) በትርክቱ አካሄድ እና ገጸባህሪዎች፣
  • ከቶ የጀማሪ ባለሙያ እማይሰኝ ዓርትዖት፣
  • አልፎአልፎ እሚጠፋ ቢሆንም የእራሱ-ለእራሱ እሚስማማ ምንምአይሌ-(ፌር) አዝማችነት-(ዳይሬክቲንግ) ላይ እሚኩራራ
  • ከቶ ከማስቀየም-የራቀ የአብይ ተዋናዮች ካሜራ ፊት ግርግሮች፣
ግን ሁሉ በእዛ እሚያበቃ መዝናኛ ለመሆን አልታደለም። ከእዛ እንከንየለሽነት በጣም እሚያሽቀነጥሩት ምህረትየለሽ መጣባትዎች ሳይከብዱት አልቀረም። የእዛ መሠረት፦ እምቅ-(ፖቴንሻል)፣ በከባዱ-አስጊ፣ ልእለ-ጅሌዎች-(ሱፐር-ጉፍስ)፦ የትርክት ክሽፈት-እና-ሴራ መፈረካከስ፨እኒህ ኮሶዎች በየት ተንጣለሉ ይሆን? ከሙሉ እይት ጋር ተጣብቷል፨

በጠቅላላው ቢቀመጥ አንደኛው ክህደተ-ገሃድ ነው። ሴራው አሩንሲበላ የነበረው ቤተኛ ጭብጥ፦ ጸረ-ደምመላሽ ዓለም፣ ለመዘብዘብ ነው። መቶ እጅ የጓዳአችን ጽልመት! አንገዳደል...ጠብመንጃዎች እና ሰይፍዎች...ማጭድ እና ዶማ ሆነው...ማሣን ይተዋወቁ! ደህና። ጎበዝ። ዳሩ፣ ተራራ ችግርአችን እና ቂል ዝምታአችን እኩል ቢኖሩም፣ መነሾ ብቻ እንጂ መቋጫ አይደሉም። ከቶ። እና ፊልሙ በእዚህ ሊንሳፈፍ ግሉን አስፈነጠረ። በቶሎ ግጭቶች አቆራኝቶ በአልከፋ ስኬት ወደ ደም-መዘወረ-(ትሪለር) ሳይቸገር ተጓዘ። የመልክአምድርአዊ እይትዎች አሰባሰቡ ደግ ሆኖ አገዘው። እስከ ማብቂያ በማይከፉ ምስሎች፣ ምልልስዎች፣ እና ምንምአይሌ ሴራ አላስከፋም። ተገማች ነገሮች ቢኖሩም (አጋች-ወ-ታጋች እንደእሚፋቀሩ-ለምሳሌ)፣ አለት-ተራራው፣ ተዳፋቱ እና እንቁ ተዋናዮቹ እያስደሰቱ ሸበቡ። ያም ግን ማብቂያ አይሆንም። እ! የአላባአዊያኖች ስምጠት። የጠነቆለው ባህልአዊ መቼት፣ ከፍተኛ እማይነቀነቁ አላባዎች በጡብነት የገነቡት ጽኑ-ገሃድ-(ሪያሊቲ) ነው። ትልሙ ወይ ደጉ ኪን፣ ደብቆ አይደብቀውም። ገሃዱ እንዲህ ነው እና። በእጀሰብእ አንድ ዕድለቢስ የሰውዘር ነብሱ ከጮማው ስቶጣ ይለቀስአለ። ወዲያው ወይ መበቀል ወይም በባህል መታረቅ ባህልአዊው ገሃዱ ነው። ከነብስ የተለደፈ ስጋ የተሸከሙት ዘመድዎች የእርቅ ካርድን በሆንብሎንታ-(ኢንቴንሽንአሊ) ከመዘዙ፣ ይህ ጎዳና በትርክቱ ፍፃሜ እንደ ነበረው፣ ተፃራሪዎችን ዳግ-እሚያወዳጅ-(ሪ-ዩኒፋይ) ይሆንአለ። ከታረቁ፣ ጠብመንጃዎች በማዋደድ ፈሊጥ፣ እነሱንም ዘልሎ በመራመድ ታካይ ትርዒተ-ዘይቤ፣ ደሞ በቄሶች ጸሎት-ማሳረግ ሰላም ይፈበርኩአሉ። ጠብመንጃዎች ተቃቀፉ-ክፉ ገጠመኝ ተዘለለ። ሁሉ ያልተከሰተ ያክል ተናቀ። እሺ፨ በዙ ጊዜ በብሔርአዊ ደረጃ በእሚፎከርበት ይህ የአካባቢው ባህል፣ ይቺ እርቅ ከተደረገች ስምምነቷ ሁለት ዣንጥላአማ አንቀጽዎች አሸገች ማለት ነው። አንደኛ፦ ደም-እመልስባይነት የለም። ቀታይ-ወ-ተጠቂ ቤተሰብ ተደርገውአሉ። ስለእዚህ ሁለትኛው ስምምነት-ፍሬ ሠገገ። በህግ ፊት መካሰስም የለም። እርቁን ከማክበርአቸው የተነሳ ህግዘብ-(ፖሊስ) ምንም መረጃው እንዳይደርሰው ይደረግአለ። ወሬው ብርድልብስ ይጣልበትአለ። ህግዘብ ጆሮዎች መገዳደሉ እንደነበረ ድህረ-እርቁ እንኳ ቢደርስ ወይም በምንም ቅድመንቃትአዊ ትትረት-(ፕሮአክቲቭ-ኢፈርት) ቢነፈነፍ መንግስት በህግ እሚይዘው እና ስምምነቱ እሚጠረስ ይሆንአለ። መረሳት የሌለበት ህግ-እና-ባህሉ ሰማይ-እና-ምድር እንጂ ተመጋጋቢ አለመሆንአቸው ነው። ለእዛነው፣ በስምምነቱ ካልዕ-አንቀጹ፣ ማንም አቃጣሪ ላይኖር ተገዛዝተው ሞቱን በሰፈሩ ሊያስቀሩ ተገዛዝተው ይለያዩ የሆነው። ገዳይ እንዲደበቅ። ለምን? አመክዮው በስምምነት ስላለቀ እና በቀል-ሠንሰለት ስለተቆረጠ መንግስት ወንጀሉን እንዳይሰማው እና ያመረቱት ሰላሙን እንዳይረብሽ ነው። አጥፊን ለመንግስት ሊሰጡ እና “ህግ ይበቀል እኛ አንበቀልም” ቢሉበት እርቁ አመክዮአዊ-(ሪዝናብል) ስልጣኔ ነበር። ብቻ ይህ የለም። ዳሩ፣ የጸሃፊው ጉዳይ ያ አይደለም። የኔው ነበር። የትርክቱ-ኩሬ ግን እዚህ ትልቅ ትልምአዊ ዋርካ ላይ ተንዠረገገ። ሰው ከሞተ፣ ምንም ስምምነት ቢደረግ መንግስት ከሰማ፣ የግድ-እና-የግድ፣ ጣልቃ ገቢ ነው። የጨዋታው እምብርት ከመንግስት እንደራሴ ህግዘቡ ጆሮ ስኩ ድብብቆሽ መከወኑ ነው። ይህ የሆነው ሰው እየገደሉ ወዲያቅ ተከትሎ በተራ ደግ መብል ፈንጠዚያ መሳለመሳ እሚያዘጋጅ ስምምነት ተገን አድርጎ የማምለጥ ዕድልንን ለመዝጋት ነው። የሰው ነብስን መንግስት እሚያስከብርበትን ግዴታውን እና በሀገር የመተዳደርአችንን አንዱ መግለጫው እና ህዝብአዊ ደህንነትን በበላይነት መተዋችንን እሚገለጽበት መንገድ ነው፤ ሌላ ምክንያትዎች መሀል። ስለእዚህ በባህል መታረቅ ቢኖርም በአካባቢው ባህል ገሃድአዊ መቼት፣ ሌላው አላባአዊ ደግሞ፣ የህግ መግባትን መከልከል የሆነው ለእዛ ነው። የእንሳሮ ትርክቱ ትልቅ ስህተት ግን ከጡዘቱ መፍቻ ትእይንት በኋላ ንጹህዋ በደረጃ-ነብስ ስትከፍል ሲያስመለክት ይጠነሰስአለ። በሂደቱ ሁሉ ሰነፍ የነበሩት ህግዘብዎች ሟቿን አክስቲት ቀድመው ባያድኑም እጅከፍንጅ ወንጀሉን ግን እሚይዙ ሆነው ማስመልከቱ በንቅዓት ተከወነልን። ወዲያው በወረዳው ህግዘብዎች ጥያቄ እንኳ ሳይደረግልአቸው ከቶ እሚለቀቁ ሆኑብን። ተሿሚ ህግዘብዎቹ፣ አጥፊ አዋኪዎቹን ከእነጠብመንጃዎችአቸው እና ንጹህዋ ዜጋን ደግሚ ሞታ አካሏን አዩ። ያዙ። ጠብመንጃዎች ወርሰው ሰበሰቡ። ሁኔታው በቁጥጥርአቸው ሆነ። ማንም ህግዘብዎችን ደፍሮ እንኳ አልተገታተረም። ገዳይ በሙሉ-ወንጀል እይት-(ሲን) ላይ ከነመረጃዎች ተገኝቶ ታየ። ይህን እንዳልንው እምናውቀው መሳሪያዎች ሲሰበስቡ እና ሰዎቹን ሲከብቡ ስንመለከት ነው። ግን ቀጥሎ ገሃዱ እሚመዝዘው እድገተ-ገሃድ ተካደብን። ምንም አለመደረጉ ከቶ ኢገሃድአዊ-(አንሪያሊስቲክ) ሴራ ጥምዘዛ ነው። ሴራው በቃለመሀላው ጥቅምዎች ወደ እማይታለፍበት፣ ለመንግስት አቅም የመገለጥ ደረጃ በደራሲው እንዲደርስ ተወስኖበት ነበር። እና ከየት አምልጠው፣ የሞተችዋን እንደያዙ ወዲያው ሰቅጣጩን ጭፈራ መጨፈሩ ተፈጠረ?! መቼቱን ገሃድ ያላንጸባረቀ ቀጣፊ አደረገብን። ትልቅ ቂልነት። ማታለል ተሞከረ። ህግዘብዎች የተሯሯጡት እና ቁምስቅል እየበሉ የደከሙት ለሦስት አላማዎች ነበር። እንዳይወፍሩ ለመሯሯጥ፣ ቅደመወንጀል ደርሶ ለማስጣል፣ ከአልሆነ ደግሞ ድህረወንጀል በህግ አጥፊን ለማስቀጣት። ስምምነት ባህል ስለሆነ በገሃዱ እማይመለከታቸው ማህበረሰብአዊ-አላባዊያን ናቸው። ታዲያ ይህ ትርክት ከየት ተራብቶ-(ኮፒድ) ነው?

ሌላው የሴራ መሠረት መናጋቱ በላጭ ስህተቱ ነው፤ በእርግጥ ምንአልባት እምቅ ብቻ። ግን ይታይ። ገጸባህሪዎቹ አመክዮአማ-(ሪዝነብል) ፍጥረት ናቸው። የሹፈት ካልሆኑ በቀረ። እኛን፦ ሰዎች ናቸው እና። ግን የገጸባህሪዎቹ ማብቂያ ዉሳኔዎች፣ እይታም ሆነ አመለካከት ሁሉ ቂላቂል ሆነ። ሴራው ተጎንጉኖ ተጎንጉኖ ሲያበቃ መነሻው ላይ የነበረ ቀዳዳ ላይ ተጠልፎ እሚዘረፈጥ እና አብሮ እሚጠልፍአቸው ሆነ። ምክንያቱም ለመታረቅ ከበቁ እና ምክንያቱ ደግሞ አለሀፍረት እንደታወጀው የአንድ ሞት አነሳሽነት ከነበረ፣ ሲጀመርም የሴራው ጥንስስ የሰው ሞት ይዞ የተነሳ ነበር። ወዲያው መታረቁ እና የሽማግሌዎቹ መብቃት ያኔም ወዲያው መታየት እሚችል ነበር። ፊልሙ ሳይሠራ ማለቅ ይችል ነበር ማለት ነው። ግን ሴራው በትርክቱ ተወልዶ ከሮጠ በኋላ ማራቶኑ ሲቋጭ የመነሻው ኋኝነትአዊ-(ፖሲብል) ክፍት ሴራ በር፦ እርቁ፣ ተደግሞ እሚከፈት ሆነ። ይህ ሁሉ ሴራ ጎንቁሎ በዳገት የሮጠው እና እየሳበ ያደከመን ሊጥለን ሆነ። የሴራ ተዳፋቱ በእዚህ መግነጢስአዊ ህጸጽ ተመልሶ ተስቦ ሊንከባለልበት እና አለሴራአዊ ድል ሊቋጭ ሆነ። ለተራ መጨፈር፣ ለተራ እርቅ፣ ደጉ የተዋናዮች ክወና፣ ደጉ ዓርትዖት፣ እና ምንምአይሌነት እሚዘልለው አዝማችነት ሙከራው ተሸነፈ። ምንም የአዲስ ነገር ምንም አዲስ አመክዮ ሲገነባ አልታየም። አለምክንያት መቋጨት ይደራር ሆነ። ቀዝቃዛ የሆነ ኢዐዋቂአዊ ስብከት እና ትእይንት ሮጠው ፊልሙን እራሱን ቀደሙ። የአፈፃጸሙም ትእይንት ከፊልሙ ደግ ሩጫው ሁሉ እማይስማማ ሰነፍ-ድራማ ነበር። ልክ ኃይሌ ገብረሥላሴ ዮስፋት ማቹካን ድንገት ሲጨርስ ሲቀድመው ማጅራቱን ማቹካ ተናድዶ እንደዠለጠው ትርክት አፈፃጸሙ የኃይሌ ማጅራት ያስተናገደውን እልህ በአስር ተባዝቶ እሚገባው ነው። በዚህኛው ምት ግን፣ ሮጦ የቀደመው እማይጣፍጥ መፍታቶት-(ሪዞሉሽን) ስለሆነ እንደ ባለጥንቸል እግሮቹ ብርቅ ማጅራት ተመትቶ እሚስቅ ልእለድለኛ አይደለም። ከቶ የወደቀበት የሴራ ተዳፋቱ ሸለቆ እሚገነባው የነበረ እና ወደእዛ ሸለቆ የለቀቀው ነው እና። ምን አልባት አንድ አማራጭ የሴራው ጥረትን ትርጉም ቀዳዳ ሊተውለት ይችል ግን አለ። ይህም ወቀሳ ሆኖ የታሰበ ሴራ ፍፃሜ ከነበረ ነው። አለምክንያት እምንገዳደል መሆንአችንን እና ለመታረቅ ተጨማሪ ደም መፍሰስ የለበትም ለማለት ከሆነ ደግ ስላቅ ሊሰኝ ይችልአለ። ማለትም ሲጀመር መታረቅ ሲችሉ ፊልም ሰርተው ሲያበቁ መታረቅአቸው አለምክንያት እንደ እምንገዳደል ለመስበክ ከሆነ ደግ ነው። ምክንያቱም፣ በመጨረሻ የተናገረው፣ አባትየው፣ ሽሙጥ ነው። ጽልም ቀልድ-(ብላክኮሜዲ) ነገር። በልጄ ደም እንታረቅ እሚል እና እሚያሾፍ ነው። ማለትም ቀድመን መታረቅም እንችል ነበር። ግን ያን አልከወንንም...አንከውንም...መሀይም ነን። ንጹህ ልጅዎች አክለን-ገድለን ሳናበቃትማ አንታረቃትም! ለመታረቅ እየፈለግን-ባህሉም እያለ እየፎከርንበትም፣ እሚሰራው ግን ተጨማሪ ደም ከማፍሰስ ጀርባ ነው። እና ይህንን ሽሙጥ ስለከወንንው እንኳን ደስአለን¡ ብሎ ጽልም-ቀልድ እሚያሽሟጥጥ ይመስልአለ። ይህም እቅጭ የፊልም ስኬት ሊያሰኘው ይችልአለ። ነገሩ ያው ነው እና። ቀድሞ መታረቅ ሲቻል ዙሪያጥምጥም ማለቱ እና ንጹህ መሰዋቱ፣ በመጨረሻው በዳንስ እና የከረፋ ድግስ መከተሉ፣ የገሃድ ሽሙጥአዊ አኗኗርአችንን እሚያስመለክት ሊሆን ይችል አለ። ይህ ደግሞ ምርጡ የትርክቱ አቅም ሆኖ ገሃዱን ሊያስመለክት እሚችል ነው። ለእዚህ አረዳድ ሌላ ደጋፊ ደግሞ የስክሪፕቱ አመጣጥ ሁሉ በቀልዶች መከበቡ እና ሹፈት ቀለሙ የነበረ መሂኑ ሊሆን ይችልአለ። ማሾፍ እሚያቅተው ስክሪብት አልነበረም እና። እንደ ቀላጅ አመጣጡ ስለእዚህ ሹፈቱ በፍፃሜው በዝቶ ተዉለበለበ። ትልቅ ስላቅ መፍታቶቱን አድርጎ ተፈጸመ። ይህ ከፍተኛ የትርክቱ አቅም ነው። የፊልሙ ብስለት እና ትልቅነት። ግን ምንአልባት ወይም አንድ መላምት ብቻ እንጂ ግድ እሙን አያያዙ አልነበረም። ስለእዚህ አሁንም ክርክርቴ-(አርጊመንት) ጋባዥ ነው። በእዚህ ቢጸናለት ግን በእርግጥ አኗኗአችንን የነቀሰው እንደ ህይወትአዊ አዙሪት ነው። አዙሪት ቅጠል የነካው። የሰነፍ መንገድ። ስንነሳ ማድረግ የተገባንን አዙሪት ቅጠሏ ነክታን ብዙ ዞረንዞረን ተሽከርክረን ስንደክም በነበርንበት እምንወድቅበት ስንፍና። ስቶይክስ እሚሳለቁበት አለመሰልጠን፣ ነገን አስልቶ ዛሬ አለመጓዝአችን። ይህ በሆንብሎንታ ወይም በአጋጣሚ በልእለቅዠት-(ሰርሪል) አረዳድ በፊልሙ ከተቀረጸ፣ ደህና፣ ጣፋጭ ጨለማ ሽሙጥ። አሁንም ሌላ ደፈጣ ዉጊያ በእዚህ ተፃርሮበትአለ። ሲያበቃ የተቀመጠው የኢሳ-ትንቢት (፪፥፬) ከምር የተፃፈልን ከሆነ እና ከሽሙጡ ዉጭ እንደሆነ አይታወቅም። ከምር ይመስል ዘንድ ይዳዳአለ። ድህረ ሞት ሰው በእርቅ ሲደሰት ኑሮ ሲለውጥ ማሳበቁ ነው። ማለትም አያያዙ ከምር ነበር ማለት ነው? ያስብልአለ። ሆኖ ሽሙጥ ካልሆነ ደግሞ በተነሳንበት ፍርክስክስ ያለበት አፈፃጸም ዉይይት መሠረት፣ እራሱን የእሚያጠፋ ነው ማለት ነው። አሊያም፣ በሀገርአችን ስነዉሳኔ-(ፖለቲክስ) ሽባነት የሞቱትን ዘንግተን እንታረቅ ከንግዲህ ከሆነም እማይተናነስ ቂልነት ነው። ህግ እና የሰው ፍጥረት ክቡራን ናቸው። ማምለጡን በምኑም ትርክት ደግፈን መቆም ቀኑ ቢገባው-ባይገባውም ህሊናአዊነትን መሸጥ ነው። እና፣ ይህ ልበሙሉ ዉሳኔን ከተመልካቾች እሚነጥቅ ነው። ምርጡ ክወና እና እሩጫ ጥራዝነጠቅ ፍፃሜ ላይ ተዘረፈጠ ወይስ በድንቅ ስላቅ ኮረኮመን እና አሳፈረን?


Source: ቢንያም ኃይለመስቀል ኪዳኔ፣ ወልቂጤ


Comments

or to write a comment

Latest News and Articles