June 15, 2017, 11:59 p.m. by Dave face
ኒው ዞዲያክ መልቲሚዲያ ስላዘጋጀው ኢትዮ ዞድያክ የተሰኘ ልዩ የኪነጥበብ ሽልማት ዛሬ 13/12/09 በሳፋየር አዲስ ሆቴል የተለያዩ ሚዲያ ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ስለ ሽልማቱ አጠቃላይ ይዘት መግለጫ የሰጠ ሲሆን ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በጋዜጣዊ መግለጫው ጊዜ ኒው ዞድያክ መልቲሚዲያ በቀጣይም ሽልማቱን አለም አቀፋዊ በማድረግ ከተለያዩ አካላት ጋር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል እንዲሁም ዳኝነቱን በተመለከተ አድማጭ ተመልካች በስልክ መልእክት ቁጥር መላኪያ መስመር 8251 ላይ በመላክ እጩዎቹን መምረጥ የሚችሉ ሲሆን ታአማኒነት እንዲኖረው በመረጃ ቋት ተመዝግቦ የምርጫ ውጤት ድምፃቸውን ማየት ለሚፈልጉ ሁሉ ክፍት ሲሆን የተቀረው ድምፅ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተወጣጡ ምሁራን የሚደገፍ እንደሚሆን እና ተወዳዳሪዎች መለያ ቁጥራቸውን በመጠቀም የምረጡኝ ቅስቀሳ በማድረግ እራሳቸውን እንዲደግፉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ እጩ የፊልሞች ዝርዝር- Fidelawit (ፊደላዊት)
- Maya (ማያ)
- Triangle 2 (ሶስት-ማዕዘን-፪)
- Atse Mandela (አፄ ማንዴላ)
- 79 (ሠባ ዘጠኝ)
- Yabedech-Yarada Lij 3 (ያበደች-የአራዳ ልጅ 3)
- Yelij Habetam (የልጅ ሐብታም)
- Yetekelekele (የተከለከለ)
- Mieraf Hulet (ምዕራፍ ሁለት)
- Yimechish-Yarada Lij 2 (ይመችሽ-የአራዳ ልጅ)
- Yabetse (ያቤፀ)
- Taza (ታዛ)
- Bale Guday (ባለ ጉዳይ)
- Toxidow (ቶክሲዶው)
- Yearbegnaw Lij (የአርበኛው ልጅ)
- Yet Nebersh (የት ነበርሽ)
- Labtos (ላብጦስ)
- ድምፃዊ ብስራት፣ድምፃዊ ቃቆ፣ድምፃዊ ሙሉቀን በጋራ በመሆን መንገዳኛ የተሰኘ መጠሪያ ያለው አልበም በአመቱ ከአድማጭ ጆሮ ከደረሱ ሙዚቃዎች ውስጥ በምርጥ አልበም ዘርፍ እጩ አድርጎታል፡፡
- ድምፃዊት ማርታ አሻጋሪ የጉድ መውደድ የተሰኘ መጠሪያ ያለው አልበም በአመቱ ከአድማጭ ጆሮ ከደረሱ ሙዚቃዎች ውስጥ በምርጥ አልበም ዘርፍ እጩ አድርጎታል፡፡
- ድምፃዊ ሀይልዬ ታደሰ በዘመኔ የተሰኘ መጠሪያ ያለው አልበም በአመቱ ከአድማጭ ጆሮ ከደረሱ ሙዚቃዎች ውስጥ በምርጥ አልበም ዘርፍ እጩ አድርጎታል፡፡
- በሙዚቃ ዘርፍ የአልበም ዕጩዎች ውስጥ ድምፃዊ ሲያምረኝ ተሾመ ካሳሁን ሲያምረኝ የተሰኘ መጠሪያ ያለው አልበም በአመቱ ከአድማጭ ጆሮ ከደረሱ ሙዚቃዎች ውስጥ በምርጥ አልበም ዘርፍ እጩ አድርጎታል፡፡
- በሙዚቃ ዘርፍ የአልበም ዕጩዎች ውስጥ ድምፃዊ ቴድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ኢትዮጵያ የተሰኘ መጠሪያ ያለው አልበም በአመቱ ከአድማጭ ጆሮ ከደረሱ ሙዚቃዎች ውስጥ በምርጥ አልበም ዘርፍ እጩ አድርጎታል፡፡
- በሙዚቃ ዘርፍ የአልበም ዕጩዎች ውስጥ ድምፃዊት ኤደን ገ/ስላሴ ወስን የተሰኘ መጠሪያ ያለው አልበም በአመቱ ከአድማጭ ጆሮ ከደረሱ ሙዚቃዎች ውስጥ በምርጥ አልበም ዘርፍ እጩ አድርጎታል፡፡
- በሙዚቃ ዘርፍ የአልበም ዕጩዎች ውስጥ ድምፃዊ እዮብ መኮንን ዕሮጣለው የተሰኘ መጠሪያ ያለው አልበም በአመቱ ከአድማጭ ጆሮ ከደረሱ ሙዚቃዎች ውስጥ በምርጥ አልበም ዘርፍ እጩ አድርጎታል፡፡