Posted on: Sept. 20, 2018, 7:54 a.m. by EtMDB
Posted on: Sept. 20, 2018, 7:54 a.m. by EtMDB
በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ሁለት ወንድ ልጆች አሉ እነርሱም ደረጄ እና ሰለሞን ይባላሉ: ወንድማማቾቹ በጣም ይዋደዳሉ:ደረጄ ታላቅ
ሲሆን ሰለሞን ደግሞ ታናሽ ወንድሙ ነው: አባታቸው ዘለቀ ይባላል እናታቸው ደግሞ ጥሩዬ ይባላሉ::ዘለቀ የራሳቸው ድርጅት አላቸው ሀብታም ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ናቸው:: ደረጄ በአካውንቲንግ የመጀመሪያድ ግሪውን ይዟል ግን ስራ አላገኘም አባቱ ድርጅት ውስጥ
መግባት አይፈልግም ምክኒያቱም በዕውቀት እና በችሎታ ስለሚያምን ከዛም አልፎ በዘመድ በቤተሰብ ገባ መባሉን ስለሚጠላ ነው::
ታናሽ ወንድሙ ሰለሞን ማትሪክ ሳይመጣለት ቀርቶ መማርን እርግፍ አድርጎ ትቶታል ቤተሰብ መንጃ ፈቃድ አውጥቶለት እንኳን..
የመስራት ፍላጎት የለውም ሱሳም ጓደኞች አሉት አንዳንዴ ከእነርሱ ጋር ነው የሚውለው ጓደኛቹም ወንደሰን እና ዮናስ ይባላሉ:: የደረጄ
ስራ መፍታት ያሳሰባቸው እናትየው ደረጄን ለምነው አባቱ ድርጅት እንዲገባ ይነግሩታል ደረጄም እናቱን ላለማስቀየም አባቱ ድርጅት
ውስጥ ይገባል አብራውም ሰብለ የምትባል አካውንታንት አለች ከሷ ጋር እየተጋገዙ መስራት ይጀምራል::ትንሽ እንደቆ የሰለሞን
የአባቱ ሹፌር ይሆናል:: ሰለሞንም አርፍ እንዲቀመጥ ቢሮ ውስጥ መቀመጫ ይዘጋጅለታል ሄለን ከምትባ ልሴክሬተሪ ፀሀፊ ጋር ቀስ
በቀስ ይግባባል ደረጄም አብራውከምትሰራው ሰብለ ጋርበደን ብይቀራረባሉ::ማታ ዘለቀ: ደረጄ እና ሰለሞን ወደ ቤት
እየተመለሱ የሰለሞን ጓደኞች ዮናስ እና ወንደሰን ያዩና ለዘለቀ መስራት እና መለወጥ እን ደሚፈልጉ ይነግሩታል ዘለቀም በደስታ የራሱ
ድርጅት ውስጥ በፅዳት ስራ ይቀጥራቸዋል:: ሄለንን ሁሌ አፍቃሪሽ ነኝ እያለ ሚያስቸግራት ሀብታም ወጣት አለየ...
ደራሲ-እስማኤል ኤፍሬም
ህጋዊ መብቱ የተጠበቀት