Abegasu Shiota (አበጋዝ ክብረውርቅ ሸወታ)
ግማሽ ኢትዮጲያዊ ግማሽ ጃፓናዊ ነው የተወለደው ጃፓን ነው ያደገው ግን ኢትዮጲያ ነው። የሙዚቃ ትምህርቱን የተከታተለው በአሜሪካ ነው ከ100 በላይ አልበሞችን አቀናብሩል ጥላሁን ገሰሰ፣ማህሙድ አህመድ፣አስቴር አወቀ፣አሊ ቢራ፣ቴዋድሮስ ታደሰ፣ኤፍሬም ታምሩ፣ንዋይ ደበበ፣ፀሀዬ ዮዋሀንስ፣አረጋኝ ወራሽ፣ሀመልማል አባተ፣ኩኩ ሰብስቤ፣ነፃነት መለሰ。。。 ከአሁኑ ድምፃውያን ደግሞ ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ጎሳዬ ተስፋዬ፣ህብስት ጥሩነህ፣ሚካሄል በላይነህ፣ታምራት ደስታ፣ዳዊት መለሰ፣ግርማ ተፈራ፣ሀይልዬ ታደሰ፣ሸዋንዳኝ ሀይሉ፣ሄለን በርሄ፣የኛ。。。እሱ ከሰራላቸው ሙዚቀኞች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። በፊልም የተሳተፈበት ቀሚስ የለበስኩለት ነው በ2ተኛው ጉማ አዋርድ ምርጥ ስኮር አሸናፊ ነበር አበጋዝ ክብረወርቅ ሸወታ።