24min | Drama
Tewodros Hunde; Berhanu Digaffe; Meskerem Abera; Abraham Gezahagne አንድ ውብ የቴሌቭዥን ተከታታይ ድራማ ወደናል፡፡ ወደን ደግሞ ፍቅራችን ከቴክኒክ ረገድ፣ የድራማውን ልቡ ምኑ ላይ ይሆን የሚለው የሀሳብ አይነት ጋር፣ የተዋናዮቹ የአልባሳት አለባበስ እና ትርጋሜ÷ በቦታዎች ውስጥ ያላቸው አቀመማጥ ትርጋሜን በሰም መንገድ ለማየት እንጥራለን፡፡መማረኬ ነው የሚያስሞነጭረኝ፡፡ በድህረ የስርጭት ዘመን (Post broadcast time) የቴሌቭዥን ተከታታይ ድራማዎች የመገናኛ ብዙኃን አይነተኛ መልክ ናቸው፡፡ በፕሮግራም ድልድል ውስጥ መቼ እና ምን አይነት መሆን እንዳለባቸው ሊሂቃንን የሚጋብዙ ጉዳዮች ሆነዋል፡፡ የቴሌቭዥን ጣቢያዎችም በተመልካቾቻው ላይ የገበያውን ድራሻ ለመውሰድ መፎካከሪያ የፕሮግራም አንቀፃች ናቸው፡፡ (audience and market share) ለኢትዮጵያ ዘመኑ የቴሌቭዥን መሪነት የሚታይበትም ነው፡፡ በአይነት÷ በአላማም የተሰለፈው የቴሌቭዥን አይነት አየሩን ይዞታል፡፡ ዜናው፣ ፕሮግራሙ፣ ውይይቱ፣ ድራማው ይመረታል፡፡ (Daily production of the media houses) የቴሌቭዥን ተከታታይ ድራማዎች ደግሞ ተወዳጅ የቴሌቭዥን ሀሳብ ማቅረቢያ መሰፈሪያ ሁነዋል፡፡ (favorable television format for audience)
Directed by:
Actor(s) & Actress(s):
Produced by:
Written by:
Age restriction: G (General Audiences)