Aug. 28, 2016, 7:01 p.m. by EtMDB
እንደ መግቢያምንም እንኳ ለአንድ ፊልም ማማር የሁሉም 'ጥበብ' ቅንጅት ጉልህ ድርሻ ቢኖረውም የሁሉም ጥሩ ፊልም መሰረት ማለት ይቻላል 'ጥሩ' ስክሪፕት /የፊልም ፅሁፍ/ ነው ተብሎ ይታመናል።ፕሮዲውሰሩም ገንዘቡን የሚያወጣው ስክሪፕቱ 'ጥሩ' ሲሆን ነው።ለሁሉም ከካሜራ ፊትም ሆነ ከካሜራ ጀርባ ላሉ ሙያተኞች ጥሩ ስራ መሰረት አሁንም ጥሩ ስክሪፕት ነው።ምንም እንኳ በተለያየ ምክንያት ታሪኩን በመተው ሌሎች 'ጥበባት' ላይ ትኩረት የሚደረግበት አጋጣሚ ቢፈጠርም ብዙዎች ይሄ ፊልም ጥሩ ነው የሚሉት ከፊልሙ ታሪክ ተነስተው ነው።ለዚህም ነው እውቁ የፊልም ሙያተኛ (ካልተሳሳትኩ) አልፍሬድ ሂችኮክ ፊልም ለመስራት የሚያስፈልጉ ሶስት ነገሮች
- Script
- Script ና
- Script
በማለት የፊልም ፅሁፍ ምን ያህል ትልቅ ዋጋ እንዳለው የገለፀው።
ወደ እኛ ሃገር አማርኛ ፊልሞችም ስንመጣ(በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ ያሉት ፊልምች...) ምንም እንኳ በድርሰት እረገድ ተጠቃሽ ፊልሞች ቢኖሩንም ይሄን ያህል አንጀት አርስ የሆኑ በርካታ ፊልሞች እንደሌሉን በሙያው አካባቢ ባሉም በሌሉም ሰዎች ይነሳል።
በእርግጥ የአማርኛ ፊልሞቻችን ከታሪክ አንፃር ያለባቸው ችግሮች ምንድነው ናቸው?
ለመሆኑ በእናንተ እይታ ጥሩ የፊልም ድርሰት እንዴት ያለ ነው?...
እስኪ በግልፅና በምክንያታዊነት እንወያይ!!
በኤልያስ ማዳ
ሰኔ 2008