Ethiopia got film policy (የምስራች ኢትዮጵያ የፊልም ፖሊሲ ኖራት)

ለብዙ ዓመታት የለፋንበት የኢትዮጵያ የፊልም ፖሊሲ ከብዙ ድካምና ጥረት በኃላ በኢፌዴሪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እነሆ ዛሬ ዓርብ ጥቅምት 24, 2010 ዓም ጸደቀ።
እናም ከዛሬ ጀምሮ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ የፊልም ዘርፋችን የሚመራበት ፖሊሲ ከነማስፈጸሚያ ስትራቴጂው ኖረን። ይህ በህይወቴ እጅግ በጣም ስለፋበት ስጠብቀውና ስጓጓለት የነበረው የኢትዮጵያ ፊልም ፖሊሲ በመፅደቁ የተሰማኝ ደስታ ወደር የለውም ብሎ ተናግሯል አርቲስት ደሳለኝ ሐይሉ

ይህ የፊልም ፖሊሲ ከጥንስሱ ጀምር እዚህ እስኪደርስ ድረስ ሁሉንም ዓየነት አስተዋፆ ላደረጋቹ ግለሰቦች፣ የማህበራት አመራሮችና አባላቶች፣ ሚኒስትሮች፣ ሚኒስተር ዴኤታውች፣ ዳይሬክተሮች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆናቹ ተቋማቶችና ድርጅቶች ሰላደረጋሁት ነገር ሁሉ በራሴ፣ በማህበሬ በኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎች ማህበር አመራርና አባላት እንዱሁም፣ በቀድሞዎቹ፣ አሁን ባለነውና ወደፊት በሚፈጠሩት በኢትዮጵያ አንጋፋና ወጣት ፊልም ሰሪዎችና የፊልም ዘርፍ ባለሙያዎች ስም እጅግ የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብሏል።

ወደፊትም ይህን የፊልም ፖሊሲ ወደተግባር በመለወጥና ዘርፉን በማሳደግ ራሳችንን፣ ሃገራችንን፣ ወገናኅንን እና የሰው ልጆችን ሁሉ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን በጋር እና በየግላችን እንድንሰራ በታላቅ እክብሮትና ትህትና እንጠይቃለን ብሆ ፅሁፉን ቋጭቷል አርቲስት ደሳለኝ ሐይሉ

Source: Artist Desalegne Hailu Mazengia


Comments

or to write a comment

Latest News and Articles

Ethiopian movie news and article - Asansiro
read more