Dec. 9, 2018, 11:44 a.m. by EtMDB
ደራሲ፣ዳይሬክተር፣ፕሮዲሰር፣ተዋናይ፣የሲኒማ ቤት ባለቤት፣የፕሮግራም አዘጋጅ፣የሾው አቅራቢ ቴዎድሮስ ተሾመ፡፡ ቴዲ በኢትዮጵያ ሲኒማ ከስሙን ጎን ለጎን ሀብት ማፍራት ከቻሉት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እንዲሁም ከራሱ አልፎ በስራቸው ያስደሰቱትን፣ለሚቀርባቸው እና ለወዳዳቸው ተዋንያን መኪና፣የቤት ዕቃ ሸልሟል፤በተጨማሪም ከሀገር እንዲወጡ አድርጎል(ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እንበለው እንዴ)፡፡
ህግ የያዘውን ህግ ይጨርሰው እና ስለ ፊልም ባለሙያው ይህን ማለት፤እነዚን ማስታወስ ፈለኩኝ፡- ሴፓስቶፖል ሲኒማ ዝነኛ ሲኒማ ቤት ነው፤መገኛው ቦታም ስለሆነ ይሆናል ሰው አማርኛ ፊልም ለማየት ትዝ ከሚሉት ቦታዎች ውስጥ ነው፡፡ በዚህ ሲኒማ ቤት ፊልም ያላየ ተመልካች በጣት እንደሚቆጠር ሁሉ በዚው ሲኒማ ቤት ያልተማረረ ያላለቀሰ ፊልም ሰሪ በጣት ነው የሚቆጠረው (ፊልማችንን እዛ አናሳይም እሰከማለት ድረስ)፡፡
አስር ተመልካች ይግባ መቶ ሁለት መቶም ሰው ይግብ ለፊልም ሰሪው ክፍያው መከፈል አለበት ቢቆይ ቢቆይ ከ3ት ወር በታች ሙሉ ገቢውን ለፕሮዲሰሩ መሰጠት አለበት፤ እሱም ፊልም ሰሪ ነው መቼም አንድ ፕሮዲሰር ፊልሙን ሰሩቱ ከጨረሰ በኃላ በሲኒማ ቤት ገቢ የሚከፍለው ብዙ ዕዳ እንደሚጠብቀው አይጠፋውም ያም ባይሆን እንደ ምፅዋት ጥያቀ ብሩ እንዲከፈለው ተመላልሱ መለመን የለበትም(ነገሩ ተለምኑም በሰጠ)፡፡ እናቱ ታማ ማሳካምያ እና መዳህኒት መግዥ ያጣ ፊልም ባለሙያ፣ለልጆቹ ትምህርት ቤት መክፈል ያልቻለ አባት፣ተዋንያኖች ብራችን አምጣ እያሉ ሰላም የሚነሱት ፕሮዲሰር፣እዳዋን እያሰበች ብቻዋን የምታወራ ፕሮዲሰርት... ይሄ በቴዲ የሚመራረው ሴፖስቱፖል የተባለ ሲኒማ ቤት በጊዜ መክፈል ይቅር ጭራሽ ብራቸውን ባለመክፈሉ የመጣ ነው፡፡
ስለዚህ በተጠየቀበት ጊዜ ሁሉም ቤት ኪራይ አለብን እሱን መክፈል ስላልቻልን ነው፣ብዙ ችግሩች ስላሉብን ነው፣በዕዳ የተሞል ቤት ስለሆነ ይላል ለውጥ የሌለው ዕዳውን የማይከፍልበትን ይቅርታ ይጠይቃል ካሜራ ፊት ስህተትን የማይቀይር ለውጥ የማያመጣ ይቅርታ፤ ዕዳ ሊኖርበት ይችላል፣ገቢ ቀዝቅዞ ይሆናል፣ተከራይቶም ይሆናል የሚሰራው ይሄ ሁሉ ግን ሰው የሰራበትን ለመከልከል ምክንያት አይሆንም ራስ ወዳድነት እና ለሙያውም ለባለሙያው ምንም አለማሰብ ካልተደመረበት በቀር፤ እርግጥ ነው ችግሩ የጋራ ነው እሱን የሚያረጋግጠው የሲኒማ ቤቱም የፕሮዲሰሩም ገቢ መቀነስ እንጂ እንደ ቀማኛ ጭራሽ ገቢን መዘረፍ አይደለም።
ከይቅርታም በላይ እስከ ጥቅምት 2011 ድረስ ዕዳውን ከፍሎ እንደሚጨርስ ቃል ገብቱ ነበር እንኳን መጨረስ መጀመሩን እንጃ እስካአሁን በሴፓስቶፖል ገንዘብ ያላቸው ብዙ ናቸው ጥቅምት አልፎል ሌላ ጥቅምት እንጠብቅ እንዴ....ሌለው በተደጋጋሚ እኔንም ያጋጠመኝ ተመልካች ፊልሙን ለማየት መጥቱ ባለቀ ሰአት ፕሮግራም የሚሰረዝበት (ጥሩ ነገር ቢሆን ብቸኛ እል ነበር) ሴፓስቱፖል ነው ምክንያቱ ምንም ሆነ ምንም ይቀየራል፡፡አሁን እሱ አይታይም የሚታየው ይሄ ነው ላድርግልህ ትባላለ ከውጪ ያየውን ፊልም ለማየት ትኬት ለመቁረጥ ብር ስትሰጥ ፊልሙ ይቀየራል በቃ።
ፍቃዱ ተክለማርያም
ጋሽ ፍቄ መታመሙ ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በደንብ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ከምናቃቸቀው መካከል አንዱ ቴዎድሮስ ተሾመ ነው፡ ጎፈንዲሚ አካውንት ከፍቶ ብር እንዲሰባሰብ አድርጎል 76ሺ አሜሪካ ዶላር እሱ በከፈተው በጎ ፈንድሚ አካውንት ተሰብስቦል።
አልሆነም ፍቃዱ ተ/ማርያም በህይወቱም በሞቱም አስተምሩን የተሰበሰበውንም ብር ሳይታከምበት አለፈ፡፡ በደግነት እጁን ዘርግቱ ለፈጣሪ ቀርቦ ያለፈው ትልቅ ክብር ያለውን አንጋፋ ባለሙያ በፍፁም የእሱን ስም የማይመጥን ህዝብ አምኑ ፍቃዱ ይታከም ብሎ በሰጣቸው ብር ኮሚቴው አለመግባባት ተፈጠረ፤ ሁለት ቦታ ተከፈሉ አንድ ቴዎድሮስ ብቻውን እና ሌሎቹ አንድላይ፤ ሌሎቹ በባንክ የተሰበሰበውን አስገብተናል በጎፈንድሚ አካውንት ያለው ሲቀር እሱ ያልገባበት ምክንያት ፊልም ባለሙያ ቴዎድሮስ ብሩን በአካውንት ውስጥ አላስገባም አለ ይህ ነው ጥቅምት 23 በካዛንቺስ የሚገኝው አፍሮዳይት ሆቴል የነበረው መግለጫ ምክንያት፡፡
አንድ ነገር አምናለው ሌሎቹ በህብረት ሆነው ቴዲን አሳጥተውታል እሱን ለማሳጣት እስኪመስል ድረስ ቴዎድሮስም በተፈጠረው ነገር ደንግጦ ነው መሰለኝ ንቀት እና እሱ የፍቃዱ ህክምና የጀርባ አጥንት እንደሆነ አስመሰሉ ነው ያወራው። ካወራቸው ውስጥ
- ሰው የእኔን ስም አይቶ ነው ብር የሰጠው
- የፍቃዱ አደራ አለብኝ
- በኮሚቴው ስራ አላምንበትም
- ብሩን ለሚለከተው አካል እንጂ አካውንት ውስጥ አላስገባም
- ከብሩ ለቀብር ማስፈጸምያ ብር አውጥቻለው
ሌሎችም እርስ በእርስ የሚገጩ ሀሳቦችን ተናግሮል እዛው ቦታ ላይ ከነዚህ ነገሮቹ ውስጥ ሁለት ዋና ነሮችን ላንሳ የፍቃዱ አደራ አለብኝ ለፍቃዱ ወንድም ቤት እህት ደሞ ስራ እንደምያስቀጥራት ቃል አለኝ ለማይመለከተው እዛ ለተሰበሰበ ሰው ብሎል፤ ሲጀመር እዛ ቦታ ላይ ይህ ቃል አያስፈልግም ዘመቻ አካሂደውበት ስለነበር ደንግጦ ነው ብለን እንለፍ ከዚ መግለጫ በኃላ ኪነ ብስራት ላይ የዋላሸት ዘሪሁን ጋር የፍቃዱ ተ/ማርያም ታናሽ ወንድም ግርማ ተ/ማርያም ጋር በነበረው ቆይታ ስለ ቤት ጉዳይ እዛ ቦታ ላይ መስማቱ ከዛ በፊትም ከመግላጫ በኃላም ምንም እናዳልሰማ ተናግሩል፤ እህቱም ቢሆን ከፍቃዱ ህልፈት በፊት ሴፓስቶፖል እንደምትሰራ ተናግሮል፡፡ (ይህንን ምን እንበለው)
ሌላው ደሞ ቀብር ማስፈጸምያ ነው ኪነ ብስራት ላይ የፍቃዱ ቤተሰብ ወጪ የሆነው 70ሺ ነው ይላል ቴዎድሮስ 300ሺ ነው ይላል፤ ደረሰኙን ማህበራዊ ድረገፅ ላይ እንደሚያወጣ ተናግሮል (እስካሁን አላየንም)፤ እንዴት ከ4 እጥፍ በላይ ልዩነት ተፈጠረ ደረሰኙስ የት ነው እርግጥ ነው መግለጫው ላይ ለምን ይዞ አልመጣም አልልም እንዲህ እንደሚፈጠር አያውቅ ይሆናል እንዳለው ግን ለምን ማህበራዊ ድረገጽ ላይ አያሳየንም፡፡በተጨማሪም 3ት ማዕዘን ሁለት ለፍቃዱ ተ/ማርያም ገቢ ማሰባሰብያ አውሮፓ ታይቱ ነበር ገቢው ምን ያህል እንደሆነ ምንቀው ነገር የለም በሱሙ የተፈጸመ ንግድ ነው እንድንል ያደርገናል ገቢውን አለማወቃችን እንደዛ እንዳንል ቢነግረን ጥሩ ነው፡፡
አንዳንድ ነገሮች
ቃል ይገባል ቴዲ ምንአልባት ስሜታዊነት ሆኖ ሊሆን ይችላል እስቲ 3ተኛው እና 4ተኛው የማለዳ ኮከቦችን እንስታውስ ለሜላት አንዋር ፊልም አሰራሻኣለው ብሎል እሱን ወደፊት አይተን እንወስን ብንል የጅማው ታሪኩ አለ የአዳራሽ ቁልፍ እሰጥአለው ብሉ ነበር ወፍ እንደሌለ እራሱ ታሪኩን ጠይቄ አጣርቻላው ሌሎችም ቃሎች ገደል ሆነ በሀይቅ ውስጥ ገብተዋል መሰል፡፡
3ት ማዕዘን 2ት ፊልም በሚታይበት ወቅት ለተመልካች በዕጣ ሲኖትራክ እንደሚሸልም ማስታወቅያ ላይ ተናግሮል፤ ፊልሙ መታየት ካቆመ ቆይቶል ሲኖትራክ ከማስታወቅያ ውጪ እንኳን ልናየው ስሙንም ሁሉ አልሰማንም እና በፖለቲካ አነጋገር የምርጫ ቅስቀሳ ነው እንበል፡፡ ብዙ ፊልም ባለሙያ መሆን የሚፈልጉ እና የፊልም ጽሁፍ ያለቸው ቴዲን አክብረው ፅሁፋቸውን አንብቦ አስታየት እንዲሰጣቸው ይሰጡቱል ከዛ ስክሪፕቱም አስታየቱም የለም በዚህ የተጉዱ ብዙ ሰዎች አሉ ጽሁፋቸው ውሃ ሽታ የሆነባቸው፡፡
መጀመርያ ላይ እንደገለጽኩት ብዙ ባለሙያወችን እና ግለሰቦችን ከሀገር እንዲወጡ አድርጉል በቅርብ እንኳን3ት ማዕዘን ሁለትን አውሮፓ ይዘው የሄዱት አልተመለሱም በዝግጅቱች ምክንያት አሜሪካ የቀሩ የምናቃቸው ተዋንያን አሉ፤ በተለያዩ ምክንያቶች ፊልም ለማሳየት በሚል ለእሱ ብር እየከፈሉ ከሀገር የወጡ ትንሽ አይደሉም፡፡
ከኤል ቲቪ ሾው ጋር የነበረው ቆይታ
ስልኩን አጥፍቶ የነበረ በርካታ ጋዜጠኞች እሱን ለማጠየቅ የማያባራ ጥያቄ የሚያቀርቡለት ቴዲ፤ ፖለቲካ ሰዎችን በማቅረብ የምናቀው የምናቃት ቤቲ እንግዳዬ ቴዎድሮስ ተሾመ ነው አለችን፡፡ ቃለ መጠይቁ ካልማረካቸው ውስጥ አንዱ ነኛ! ፖለቲካ መጠየቅ ከእኔ ውጪ ላሳር ብላ ነው መሰል እሱን አስቀምጣ መጠየቅ የፈለገችው ስለ ጠቅላይ ሚንስትራችን ነው ስራውን በግድ ከፖለቲካ ጋር ማገናኛት ነው ዕቅዷ፤ ያም ሆነ ይሄ እሷም ጠየቀች እሱም መለሰ እኔም ይህን ልል በጣም ፈለኩ፡ የጥበብ ስራ የግድ አሽሙር መናገር የለበትም የህዝብን ሀሳብ ቢናገር ጭወታችን ቢጮው ጥሩ ነው፤ ይሄን ለማለት እኮ ነው ብሉ ግን ጥበብ የለም እኛ ቴዲ አፍሮ ያስተሰርያል ነግሮን አይደለም ትዕንቢት ነው ያልነው የናቲ ማን እመነኝ ይህንን ልል እኮ ነው ብሎ አይደለም ይወክለናል ያልነው የባህር በር ፊልም ይህን ልሰራ ሀስቤ ነው ብሎ አይደለም የታገደው እና የፊልም ባለሙያው ሀሳብ ግልጽ አድርገ መስራት ስላልቻልክ ከአንተ ውጪ የገባው ስለሌለ ሰብ ታይትል ተጠቀም የሚል ምክር ጣል አደርጋለው፡፡
ነጋዴነቱ በጣም ጉልቱ የወጣበት ቮው መሆኑን ሳልናገር ማለፍ አለፈልግም እንዴት ካላቹኝ ያወራውን ስሙልኝ፡፡
ምስጢራዊ ምንጭ