Zemen Drama From my Point of View (ዘመን እንደ እኔ እይታ)

በኢትዮጵያ ተከታታይ ድራማ ታሪክ በሳምንት ሁለት ቀን በመታየት ቀዳሚ የሆነው ዘመን ድራማ በርዝመት ከዚህ በፊት የሰሩትን ሰውለሰው በቅርብ ያለቀውን ዳና በልጦ አሁን ባለበት ክፍል ብቻ ረዥም ክፍል በማሳያት(አሁንም እየታየ ነው) ከፊት ይገኛል ዘመን፤ ከአንጋፋዎቹ አበባ ባልቻ፣ስዩም ተፈራ፣ዘውዱ አበጋዝ፣አብራር አብዱ... መሃል ላይ ካሉት ሀና ዮዋሀንስ፣ሳምሶን ታደሰ(ቤቢ)፣ሰለሞን ቦጋለ፣ኤልያስ ሻፊ... የማለደ ከከቦች ተወዳዳሪ እና አሸናፊ የነበሩት እነ አዩ ግርማ፣ጸደይ ፋንታሁን፣ሙሉጌታ ዘሚካሄል፣ቤቴልሄም ኢሳያስ... በዘመን ዝና ያተረፉት ወጣቱችን ማስተዋል ወንደወሰን፣እስክንድር ታምሩ፣ትንሳሄ ብርሃኑ፣ቁመነገር ደረጀ... ከአሜሪካ እየተመላለሰች የምትሰራውን ፍሬህይወት ታምራት ጨምሮ በርካታ ተዋንያንን አሳትፎል ደራሲው መስፍን ጌታቸው ዳይሬክተሩ ሰለሞን አለሙ ፈለቀ ነው ደራሲ እና ዳይሮክተሮችን ጨምሮ አንጋፋው ተወናይ አበበ ባልቻ እና ሌላዋ ተወዳጅ ተዋናይት ማህደር አሰፋ ኤክስኪቲቭ ፕሮዲሰር ሆነው ዘመን እሁድ እና ማክሰኞ በኢቢኤስ ቲቪ ይታያል፡፡
እንደ ሁሉም ስራዎች ጠንካራ እና ደካማ ጎን አለው፤ እንዲስተካካል በማሰብ ማተኮሩ የፈለኩቱ እንደ አኔ ዕይታ ደካማ ጎኑ ላይ ነው ሙሉ ደካማ ማውራት እንዳይሆንብኝ በዝርዝር ባልገልጥም እነዚህ ጠንካራ ጎኖቹ መሆኑን ላስታውስ፡-
  1. አብዛኞቹ ተዋንያን በብቃት ነው የሚተውኑት
  2. ቀረጻው ጥሩ ነው
  3. ብዙ እንደወጣበት መናገር ሳይጠበቅባቸው ስራቸው ይመሰክራል
  4. የቀረጻ ቦታዎቹ ጥሩ ነው
  5. የስደተ ታሪክ እንደ አጠቃላይ የስደተኞቹ ፓርት ብዙ ርቀት ሄደው የሰሩት የሚስደንቅም የሚያስመሰግንም ነው
ወደ ገደለው ስገባ... ከዚህ በፊት እንደተባለው ድብን እና ፍጥጥ ያለ ኮንቲኒቲ ችግር አለ፤ ይህ በተደጋጋሚ ቪዲዮ የተሰራበት ስህተት ከቦታ እስከ ልብስ ሁኔታ በሰከንዳት ውስጥ ጫማ ከመቀየር መነጽር ከማድረግ እስከ ሜካፕ መጠን መጨመር እና ማነስ ሁለሜ ማለት በመያስደፍር ሁኔታ ዘመን ስናይ ኮንቲኒት ያዥ የላቸውም እስክንል የምናየው ችግር ነው፡፡
“የማይመስል ነገር ለሚስት አትንገር” ይባላል እንደእኔ እይታ ብዙ የማይመስል ነገር ውስጥ የተከበበ ድራማ ነው ዘመን፤ አንዳንዴ ሳይ የትነው ያሉት ያስብለኛል የሚጣሉበት፣የሚጫጫውበት ጉዳይ ጡዘቱ ሁሉ ምነው እቴ ያስብለኛል፡፡
ለምሳሌ፡ ናፍቆት(እስክነንድር) ገጸ ባህሪ በየጊዜው የማይመስል ነገር ያደርጋል ለምን እንዴት ብንል እንኮን መልስ የሌላቸው በጥቂቱ ቅርብ ጊዜ አዳነችን ደብድቦል ይሁን ይደብድብ ከዛ በኃላ ነው የሚገርመው እሶን መደብደቡ ሳያንስ ቤት ድረስ ይሄዳል ይህ ብቻ አይደለም እናትየው ታስገባዋለች እሱስ ይሆን ድንገት ይሰለበል ሰው ቤት ገብቱ፤ ሰው ይደበድባል ሲፈልግ ይሰበስባቸዋል... እዚ ጋር እንደውምፖሊስ መጥቶ ተጫጩኦ እየደበደበ እያት ገንዘብ እንደረዳ ሰው ዘና ብሎ ይወጣል፤
ወደ መጀመርያ ክፎሎች ስንመለስ ተመስገን(ኤልያስ) አዳነችን(ሀና) የቀረባት ሳይኮሎጂ ችግር ስላለባት ኢሚንት ፍቅር ሳይኖረው ሊረዳት ነው ወደ በኃላ ሚስጥሮን እንድያቅ ቢያደርጉትም ከጉኖ የሆነው ሊረደግፋት ነው፡፡ እና ይሄው ቶም እሷን ሲደግፍ እሷም ስትደገፍ ምንም ፍቅር የሌለው ሰው የማይሰጠውን ፍጹም ፍቅር እየሰጣት እሷም የሱ ፍቅር ገብቶት በፎንቃው ጠብ ብላ ምን ሆነ ብዙ ብር ከፍላ ያሰራችውን ፎርጂድ ዐይኖ ዕያየ ቀደደ ይቅደድ ይሁን እንደ ወረቀቱ አንገብጋቢ ነት ይተናነቃሉ ብለን ስንጠብቅ ጭራሽ እንደድሮ ሚስጥሮን ትዘርግፍለታለች ታማክርዋለች ስንት ደክማ ያመጣችውን፣ህልሞን ያጨለመውን፣ወንጀል ውስጥ የገባች ደፋር የፈለገችውን ለማድረግ የማትቦዝን ሴት ሁሉንም ትታ እንደድሮ ሆነች፤ እና ያሳምናል፡፡
አብይ(ሰለሞን ቦጋለ) ሚስቱ ካሜራ አስገጥም አለቸው ይሁን እስቲ ትበለው... በጣም የሚገርመው ነገር ካሜራ ይገጠም ሚስቱ ስትለው፣እሱም ይገጠማል የሚለውን ሀሳብ ሲቀበል፣ለአሰሪው ሲነግር፣አሰሪው ሲሰማ፣አሰሪው ለማስገጠም ሲያስብ... ብቻ የካሜራው ጉዳይ ሀገር የመገልበጥ ጉዳይ ነው ያስመሰሉት እንደ አጠቃላይ አብይ ከአሰሪውጋር ያለው ነገር ለአኔ የማይመስል ነው አብረው የምትሰረው ዳይናዊት የምታደርገው የማይመስል ነው፣ከሚስቱ ጋር እንደ ዝሆን አግዝፎ የሚጣሉበት ጉዳይ ድጋሚ ለእኔ ለአቅመ ግጭት የማይደርስ ጉዳይ ነው፡፡
ሌላው ደሞ ገጸ ባህሪ አሳሳል ነው፡፡ በጥቅሉ ለመናገር ሴት ገጸ ባህርያት አውርዶ(ከስደተኞቹ ውጪ ማለት ነው) ጥንካሬ ካላቸው በክፎ መንገድ ብቻ የምናይበትነው ወንዶቹ ደሞ ያሰቡት የሚሳካላቸው፣ ፍጹም ቅን ሆነው የተሳሉት ይበዛሉ፡፡
ጥንካሬ አላት ብለን የምናሰባት ህይወት በራሷ መቆም የማትችል በአባቱ፣በወንድሞ፣በፍቅረኛዋ ጥበቃ የቆሞች በተደጋጋሚ አንተን ካጣው ሰው አልሆንም፣እራሴን አጠፋለው ለናፍቆት የምትል እራሶን ከፎቅ የወረወች ደካማ ገጸ ባህሪ ናት፤
ሳሮን በቅናት የታጠረች ብዙ ወሬ የምትሰማ ባሎን ማሳመን የማትችል ለዕንባ መፍቴዋ የሆነች ሴት ናት፤ ብዙ ነገር የምታማክራት ጠንካራ ናት የምንላት ሉሌ ወርዳ ባለፈ ታሪክ የቆመች አደረጎት ምን አለ እሱን እንኳን እንደ ቶም ወይም አብይ ጠንካራ ሆና ብትቀር ።
ስምረት የምትፈልገውን የማታውቅ በብዙ ደካማ ጉን የተሳለች ሴት አጠገቧ ደሞ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚወዱት ጠንካራ ብቻ የሆነው ወንድ አለ ነፃነት (Faminist ምን ትላላቹ)
ፅዮን እና አዳነች ክፋት የግላቸው የሆኑ ሴቶች ናቸው የፈለገበት ቦታ ላይ ብቁ፣ጠንካራ፣በራስ መተማመን ቢኖራቸው ክፋታቸውን እንጂ ሌላ ምን ማየት አይቻልም

.....

እዚ ጋር እነደ ግራ ግብት ያለ ገጸ ባህሪ ማስታወስ እፈልጋለው አዳነች፤ በሳይኮሎጂ የተጎዳች ለእህቷ ጥላቻ የነበራት አልነበረችም ይህንን ደግሞ በተደጋጋሚ በምሬት ትናገራለች ካራክተሮም የተሳለችው ተወዳጅነት ከፍ ያለ ብዙ ሰው ለፍቅር የሚመኛት የት ትደርሳለች የተባለች ሴት ዕድሜዋ እየገፋ ያለ ትዳር እስካሁን ካደገችበት ቤት ያለወጣች መሆኖ በዚህም አጋጣሚ እራሱን ለመለወጥ ሌላ አማራጭ ስለሌላት እህቷን የምትጠቀም ሴት ነበረች፤ ግን እያየናት እህቷን ከራሱ ለውጥ ይልቅ ለእህቱ መሰበር የምትደክም ሴት ሆነች በምክንያት የከፋችን ሴት ክፎት አብሮት የተወለደ ሴት ሆነች፡፡
የናፍቆትንም ከልክ ያለፈ ድርጊት ሃይ ባይ የሌለው ሰው፣ሁሉም በእጁ ሁሉ በደጁ የሆነ ገጸ ባህሪ ገደብ መስጠትም ተገቢ ነው፡፡
የነፃነት ሰው የማይመስል ለመላዕክ የቀረበ ፍፁም ሰው ገፀ ባህሪም ይታሰብበት
አላስፈላጊ ነገሮች ፡ የቲቪ ድራማ ከቤተሰብ ጋር ነው የሚታየው ጭራሽ ልናያቸው የማይገቡ ነገሮች እንዴት ይባላል የምንላቸው ቃለ ተውኔቶች አንዴ ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ይጠራሉ፡፡ መጀመርያ ክፍል አከባቢ የበዙ የፍቅር ሲኖች እና ደስ የማይሉ የሹገር ማሚ ሁኔታ ብልግና ከምንላቸው ወሬዎች ጋር እናይ ነበር መሀል ላይ ትቶ ነበር አሁን ግን ተነስቶባቸዋል ተመልሰው እነዛ ነገሮች እያሳዩን ነው የቲቪ ድራማ ከቤተሰብ ጋር ነው የሚታየው በፊልሞቻችን የምንሳቀቀው ይበቃል አንዳንድ ነገሮችን ኢትዮጲያ ላይ የምንኖር ኢትዮጲያዊ ነን እና ይቅሩብን፡፡
እዚ ጋር ሌላ አቅል የሚያስተው ጉዳይ በተደጋጋሚ የእግዝሐብሄር ስም የሚጠራ ሁሉንም አውቃለው፣ገንዘብ አባዛለው የሚለው በመላዕኩ ሚካሄል ስም የሚጠራ ዕቃ ዕቃ ታሪክ የሚነግሩበት ምንም ምቾት የማይሰጥ ታሪክ ይዞብን መጥተዋል፡
በተረፈ እንደ አጠቃላይ አሰልቺነት አለው ድራማው ለዚ ምክንያት ከእኛ የራቁ ገፀ ባህርያት አሳሳል እና ግጭቶቹ እንዳለ ሆኖ ቃለ ተውኔቶቹ በጣም አሰልቺ ናቸው።
ዋናው ግን ዘመን ባይኖር ይህን አልፅፍም፣በርካታ ተዋንያንን አናይም እና ይበል። ጺዮን ታምራት


Comments

or to write a comment

Latest News and Articles

Ethiopian movie news and article - Asansiro
read more