The chain of Ethiopian Drama (የኢትየጵያ ድራማ ያሰረው ሰንሰለት)

ቲቪ ድራማዎች በዝተዋል፣ከህዝብ ፍላጎት እና ከሚዲያ መብዛት አንፃር ገና ያስፈልጋሉ... በሁለት የተከፈሉ ሀሳቦች ሊነሱ ይችላሉ ከሁሉም ግን ማንንም የሚያስማማው እውነት ከጥቂት አመት በኃላ በርካታ የቲቪ ድራማዎች መቅረብ ጀምሮል ለዚህ አንዱ ምክንያት ብዙ ሚዲያዎች መከፈት ሊጠቀስ ይችላል። በዚ ላይ ሳይነሳ መቅረት የሌለበት በስሜታዊነት ይሁን በችኮላ እንዲሁም ስፖንሰር ማጣት እና ወጪ መሸፈን ከብዶ ትንሽ የማይባሉ ተከታታይ ድራማዎች ተጀምረው ከአንድ ምዕራፍ በላይ መጎዝ አልቻሉም። በርካታ የቲቪ ድራማዎች የሚተላለፍበት ኢቢኤስ ነው ከሚተላለፎት መሀል ደሞ ከሰሜን አሜሪካ ተሰሩቱ የሚቀርበው ሰንሰለት አንዱ ነው የድራማው ደራሲ ተመስገን አፈወርቅ ነው አዘጋጁቹ ደሞ ደራሲው እና ቴድሮዎስ ለገሰ ናቸው፤ ዳይሬክተሮቹን ጨምሮ አይልቅበት ተሾመ፣መስታወት አራጋው፣መለሰ ወልዱ፣ኤርሴማ አባይነህ (የድሮ ዮዲት መንግስቱ)፣አብርአም ማሩ... እና ሌሎችም ለመጀመርያ ጊዜ ሰንሰለት ላይ ያየናቸው በፊት እንውቃቸው የነበሩ አሜሪካ የገቡ ተዋንያን ተሳትፈውበታል ቅዳሜ ቅዳሜ ምሽት 3:30 (በኢትየጵያ ሰዓት) ይታለለፋል ሰንሰለት

ወደ ገደለው ስገባ...ሰንሰለት እንደ እኔ

ይህን ፅሁፍ የፃፍኩት ሰንሰለት በመሰረቱ ነው ይህንን በቅድሚያ ላስቀምጥ ቀጥሉ ሰአታቸውን በአግባብ ይጠቀማሉ ከ45 ደቂቃ ያለነሰ በየሳምንቱ ያስተላልፋሉ በዛ ላይ season break በሚል ረዥም ጊዜ አይወስዱም። ...እና ለእኔ ሰንሰለት በጣም በብዙ ስህተቱች የተሞላ ተከታታይ ድራማ እንደዚህ መሰራት የለበትም ለሚለው ማሳይ ነው ከታሪክ አንስቱ እስከ ኤዲቲንክ በአጭሩ ለምን አንሰራም በሚል ተነሳሽነት በተለይ ኢትዮጵያ ላለነው ተመልካች የማይመጥን ስራ(ምን አልባት እዛ ያለው ኢትዮጵያዊ ኑሮን ያሳየው ይሆናል) ለእኛ እዚ ላለነው ግን ዕቃ ዕቃ ነው።

ታሪኩ:- (የመጀመርያው ዕቃ ዕቃ) አሜሪካ ህግ የለም የሚያስብል ምክንያታዊነት የጎደለው ገና ሲጀመር የታወቀ እንደገና ደሞ የተንዛዛ ከ5ሳንቲም በታች ዋጋ ያለው ነገር ለሶስት ተከታታይ ክፍል የሚቆይ እጅግ አሰልቺ ታሪክ ነው። ኢሚንት በሆነ ምክንያት ሰው ሀገር ላይ ሰው ማስገደል፣ሰው ገድሉ በነፃነት የሚኖርበት እሱ ይሁን ስንል የተገደለባቸውም ቤተሰቧቸ አርፈው የሚቀመጡበት(ለእያንዳንዱ ችግር 911 24/7 በፍጥነት እየደረሰ ያገለግል በሚባልበት ሀገር)፣የሰው ቤት እንደ ልብ ሰብሮ የሚገባበት፣ከዝናብ የማይተናነስ ጥይት ወርዱበት ያለ ምንም ጠባሳ በህክምና መዳን... ፤ በጣም የሚስቀኝ የስደተኞቹ ታሪክ ነው ቆይ ቢቀርስ ባይኖርስ በዛ ላይ ስደተኛ የተባሉት በሙሉ ድሉት ያንገላታቸው ፣ገራሚ ንቅሳት ክንዳቸው ላይ ያሳረፎ፣ወዛቸው ቁልጩ ያለ፣ልብሳቸው ከየት አምጥተውት ነው ይህን የመሰለ ጃከቴ የሚያስብል...እሱስ ይሁን በትወና ይሸፈናል እንዳንል አንዱ እንኳን ትወና የማይችሉ ናቸው ሁሉም መዱ ይይዛሉ እንዴት እኛ ጋር እንደመጡ እግዝኤር ይወቀው እነሱን ማሰራት ለእኛ ተመልካቹች ንቀት ነው። ሌላው ደሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲ ይሄ የፈረደበት የማይዳሰሰውን ለውጥ ለመጠቀም በሚል ፖለቲካ ያለ ምንም ተጨባጭ ነገር እያካተቱ ነው(the same is true for ዘመን ድራማ! ደሞ አውቄ ነው በእንግሊዘኛ የፃፍኩት)

ኮንቲንቲ ስህተት ያስጠላካል ከማለው ቃል ውጪ ምንም አይገልፀውም ከአቀማመጥ እስከ አለባበስ በቃ በሽ ነው እሱን ልከታተል ከተባለ አንድም ነገር ማየት አትችልም (ይሄ አብዛኛው ተከታታይ ድራማዎች ላይ የተለመደ ሊስተካከል የሚገባው ቢሆንም ሰንሰለት ግን እየበሳበት ነው ሲጀምር ከነበረው አሁን ላይ ያለው ኮንቲኒት ስህተት ይበልጣል)

ትወና:- ቅድም አንስቼዋለሁ ስደተኞች ላይ ግን አሁንም አነሰዋለው ምክንያቱም ሰንሰለት ላይ የሚተውኑት ከ60% በላይ አይችሉም ከየት እንደተመለመሉ እንጃ ብቻ ባዶ ከሚሆን የመጡ ነው የሚመስለው ከለመቻለቸው የተነሳ፤... አንዳንዴ እንዲ እላለው በጣም ብዙ የሚችሉ የምንወዳቸው ተዋንያን አሜሪካ እንደገቡ ኑሮቸውን እዛ እንዳደረጉ በአካል ሄደን ባነይም ቲቪ ላይ ቀርቧ ወይ በInstagram post አውቀናል እና እነሱ ለማን ማሰተፈ ከበዳቸው እልልና ደሞ እንኳንም አልገብ የሚለው ሀሳብ ይገዝፍብኛል ምክንያቱም ጭራሽ ድራማው አይመጥናቸው ስራው የወረደ ነው ጠፍታቹ ጠፍታቹ በእንዲህ በወረደ ስራ እኔ በግሌ ላያቹ ጭራሽ አልፈልግም (ዮዲት መንግስቱ ምክንያትሽ ምን ይሁን ምን ከዚህ ድራማ መውጣትሽ በጣም ጥሩ ውሳኔ ነው ለእኔ)

ኑሮአቸው፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዘመድ አለው ያቺ ሰው የማይቀርበት ሀገር ላይ እና ሲነግሩን መቀመጭያ ሰአት እንኳን ገንዘብ የሆነበት ሀገር ነው እና ሰንሰለት በተደጋጋሚ የሆነ ቦታ ቁጭ ብለው ረዥም ሰአት ሲያጠፎ፣ተሰብስበው ሰው እየቧጨቁ ጥሬ ስጋ ሲበሉ ነው የምናየው ከስንት አንዴ ነው ስራ ላይ የምናያቸው እና ምን ለማለት አሜሪካ እንዲህ ናት እረፍት በሽ የሆነበት ሀገር ናት እኛ ድንገት ከመጣን እናንተ የምታሳዮንን ህይወት መኖር እንችላለን

የሰልጣኔ ሀገር የቴክኖሎጂ መሪ በሆነች ሀገር ላይ ተቀምጦ በቀረፃ በኤዲቲንግ ተሽሎ አለመገኝት ይቅር እና ተወዳዳሪ አለመሆን ሲደረስ ይደብርአል፤ እንደ ኢትዮጵያ በቂ የሰው ሀይል ባይኖርም ዳሩ መሰረት ያለበት ነገር ግድ ለተመልካች መመጠን አለበት

ይህን ዕይታዬን ስፅፍ የሙሉ ጊዜ ስራቹ እንዳልሆነ ባላቹ ጠባብ ጊዜ ነገራቹን አጠባቹ ለተመልካች ለማድረስ ተግታቹ እንደምትሰሩ (ለዚህ ማሳያ ሁለት አመት መቆየታቹ አንድ ነው) ግምት ውስጥ ለመክተት ሞክሬ ነበር...ግን... አንድን ነገር አድምቶ መስራት የማይቻል ከሆነ፣ባላቹም ጊዜ ተሽሉ ቀረቱ ተወዳዳሪ መሆን የማይቻል ከሆነ ከሰሜን አሜሪካ የሚተላለፍ ለመባል ያህል ወይ በቁጥር ለመጨር ከልሆነ እንደው አልተገደዳቹ ቢቀርስ አሰኘኝ...


Comments

or to write a comment

Latest News and Articles

Ethiopian movie news and article - Asansiro
read more