Congratulations! to 9th Leza Award winners (ለ፱ኛው የለዛ ሽልማት አሸናፊዎች እንዲሁም እጩዎች እንኳን ደስ አላቹ)

ለ፱ኛው የለዛ ሽልማት አሸናፊዎች እንዲሁም እጩዎች እንኳን ደስ አላቹ
  1. ቁራኛዬ: የዓመቱ ምርጥ ፊልም … በዳኞች 60% ውሳኔ
  2. ዘሪሁን ሙላት: የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ … የዳኞች 60% ውሳኔ አሸናፊ
  3. አበበ ባልቻ: ተከታታይ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይ - የአድማጭ ምርጫ
  4. የምስራች ግርማ: የዓመቱ ምርጥ ተዋናይት … በዳኞች 60% ውሳኔ
  5. ጆቫኒ ሪኮ: የሕይወት ዘመን ተሸላሚ
  6. ጎሳዬ ተስፋዬ: የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ … የአድማጭ ምርጫ
  7. ሀና ይሗንስ: ተከታታይ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናዪት … የአድማጭ ምርጫ አሸናፊ
  8. በሃይሉ ታፈሰ (ዚጊ ዛጋ): የዓመቱ ምርጥ ዘፈን በዳኞች 100% ውሳኔ
  9. ደርሶ መልስ: የዓመቱ ምርጥ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ … በአድማጮች 100% ውሳኔ
  10. ቸሊና: የዓመቱ ምርጥ አልበም … በዳኞች 40% ውሳኔ
  11. ጃምቦ ጆቴ: የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዘፈን አሸናፊ
  12. ተሾመ ሲሳይ: ሙዚቃ የጀመሩት በምድር ጦር ነው፡፡ ወታደር ነበሩ … ከምድር ጦር ወደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንዲዘዋወሩ ከተጠየቁ በኋላ አምና በጡረታ እስኪሰናበቱ ድረስ በቴአትር ቤቱ የሙዚቃ ክፍል ሰንብተዋል፡፡ … ዋናቸውን ፍሉት ቢያደርጉም ፒያኖም ይጫወታሉ … አቀናባሪም ነበሩ … (የትዝታዬ እናት) እና (ትንፋሼ ተቀርፆ) … (ዜማና ግጥሙን ሲራክ ታደሰ የሠራው) … በተለይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይሠሩ በነበሩ የመድረክ ሥራዎች እና ቅንብሮች ላይ ፊታውራሪ ነበሩ …
  13. ኩራባቸው ደነቀ: የቴአትር ባለሞያ ነው፡፡ የአ.አ.ዩ የቴአትር ት/ቤት ምሩቅ፡፡ ሀገር ፍቅር የመጀመሪያ የሙያ ቤቱ፡፡ በኋላማ የቴአትር ቤቱ ሥራ አሲኪያሃጅም ነበር፡፡ የመድረክ ቴአትር፡ ተውኗል፡ ጽፏል፡ አዘጋጅቷል፡፡ በራስ ቴአትር (ትንታግ) በማዘጋጃ (ሶስና) ካዘጋጃቸው መካከል ናቸው፡፡ በቴሌቪዥን ድራማ ደግሞ (ማለዳ)፡፡ በራስ ቴአትር፡ ስቴሪዮ ክለብ ስቱዲዮ አቋቁሟል፡፡
  14. አብርሃም ገዛኸኝ: ዛሬን በተራው ሸላሚ ይኹን እንጂ እርሱም ተሸላሚ ነው፡፡ በጉማ፡ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል፡ በዚሁ በለዛ፡ ከለር ኦቭ ዘ ናይል ፊልም ፌስቲቫል… ምርጥ ፊልም ሠርተሃል፡ ውብ አድርገኽ አዘጋጅተሃል፡ ምርጥ የፊልም ጽሑፍ ጽፈሃል፡ ቆንጆ ምስል አስቀርፀሃል፡ የተዋንያኑን ዐቅም ገልጠሃል፡ በድምፅ በገጽ ቅብ ኹሉ፡ ኹሉ ተሳክቶልሃል፡ በሚል እርሱን ብቻ ሳይኾን አሸልሟል፡፡ ……. ሥራ ብዙ ነው፡፡ (የገበና 1) 52 ክፍል አዘጋጅ ነው፡፡ (ምጋቶች) ም ላይ 36 ክፍል ያህል፡፡ … ዐሳብ በማመንጨት፡ በማፍታታት፡ መልክ በማድመቅ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ሠርቷል፡ ሜጋ ኪነጥበባት፡ ሚፍታሕ ፕሮሞሽን፡ ጆን ሆፕኪንስ፡ ቢቢሲን ጨምሮ፡፡ የዶን ፊልም ውስጥ 12 ያህል፡ በፍሊንት ስቶንም በቆየበት 5 ዓመታት፡ ከገበያው የተዋደደ ከ 30 በላይ የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎችን ሠርቷል፡፡ (የፍቅር ነገር) (ሚዜዎቹ) (የጥረት ፍሬዎች፡ ዶክመንተሪ)፡ (ቅብብሎሽ)፡ በስክሪን ጽሑፍ፡ በዝግጅት እና በፕሮዳክሽን መሪነት ሠርቷል፡፡ … የቀደሙት ተሸላሚ ፊልሞቹ፡ በተለይም (የነገን አልወልድም) በሎንዶን፡ በደርባን፡ በሎስ አንጀለስ እና በላጎስ በተካኼዱ ፊልም ፌስቲቫሎች ተመስጋኝ ነበር፡፡ ሌላኛው እና ኹለተኛው፡ ሽልማት የተገባው (ሎሚ ሽታ) ፊልሙ ነው፡፡ … በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ዐዲስ የተጀመረው ድራማ (የእግር እሳት) … የእርሱ እኮ ነው … ትምህርቱ የቴአትር ጥበብ ነው፡ በአ.አ.ዩ … ኹለተኛ ዲግሪው ደግሞ በጋዜጠኝነት እና ኮሚውኒኬሽን
  15. ኃይሉ መርጊያ: ወደ ሙዚቃ የገቡት ከአርባ ዓመት በፊት፡ በምድር ጦር የሙዚቃ ክፍል ሥልጠናውን ወስደው፡፡ በኋላ ጊዜ ከግል የሙዚቃ ቡድኖች ጋር በመኾን ሠርተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በነበሩበት ጊዜ ከተለያዩ ተጫውተዋል፡፡ በመጨረሻም ከዋልያስ ባንድ ጋር ወደ አሜሪካ በመኼድ በተለያዩ ክፍለግዛቶች በመዘዋወር ትርኢታቸውን አቅርበዋል፡፡ በኢትዮጵያም ኾነ በአሜሪካ ቆይታቸው በርካታ በሙዚቃ መሣሪያ ብቻ የተቀነባበሩ ዜማዎችን በካሴት እና በሲዲ ለአድማጮች አቅርበዋል፡፡ የተመሰገኑ የሙዚቃ ባለሞያ ናቸው፡፡
  16. ተባባሪ ፕሮፌሰር አቦነኽ አሻግሬ: በአ.አ.ዩ በቴአትር ት/ቤት ውስጥ መምህር ናቸው፡፡ ከ30 ዓመት በላይ ቴአትር አስተምረዋል፡፡ ጽፈዋል፡ ተርጉመዋል፡፡ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር አካኺደዋል፡፡ ጽሑፎቻቸውም በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ታትመውላቸዋል፡፡ በቅርብ፡ በዓለም የታወቁ፡ ከእግሊዝኛ ወደ አማርኛ የተመለሱ አስራ አንድ ተውኔቶችን የያዘ (የዓለም ምርጥ ተውኔቶች) በሚል ያሳተሙት መጽሐፍ አለ፡፡ እንዲሁም ሚቺጋን እስቴት ዩኒቨርሲቲ ባሳተመው የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን ቀንድ ሲኒማ ጉዳይ የተመለከቱ የአሥራ ኹለት ምሁራንን ጥናቶች ባካተተው መጽሐፍ ላይ በአርታኢነት (ከሌሎች ጋር በመኾን) ተሳትፈውበታል፡፡ የቴአትር ት/ቤት እና የአ.አ.ዩ ባህል ማዕከል ዳይሬክተር ነበሩ፡፡
  17. ኤልያስ ተባባል: ቀድሞ በራስ ቴአትር ቆይታው ማሲንቆ ተጫዋች ነበር፡፡ በኋላ ደግሞ ድምጻዊ … ኹለት አልበም ሠርቷል፡፡ (ማማዬ፡ ማማዬ)፡ … ከሰው ጆሮ የቀረ… ባለማሲንቆ መሣሪያውን ሲያነሣ ዐብሮ የሚያነሣት ዜማ ናት… (ገንዘብ አላት ብሎ መልከ ጥፉ ማግባት፡ ገንዘቡም ያልቅና ኹለተኛ ጥፋት) … ደሞ ሌላ፡ ከጊዜ በኋላ (የኢትዮጵያ ሴቶች ስም እኒህ ነበሩ) የሚል ጥቅስ መሳይ ሀተታ በዜማ መዝገብ አስቀምጦል፡፡ ከ28 ዓመት በኋላ
  18. አዜብ ወርቁ ስባኔ: ኹለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ ወደ ቴአትር ገባች፡ በተስፋዬ ሲማ የቴአትር ትምህርት፡፡ በኋላም በአፍለኛው የቴአትር ክበብ ውስጥ ሳለች፡ በፀጋዬ ገ/መድኅን (ሀ ሁ ወይም ፐ ፑ) የበዓሉ ግርማ (ከአድማስ ባሻገር) እና የሰሎሞን ዓለሙ (ከዳንኪራው ባሻገር) ላይ ተጫውታለች፡፡ ከፈረንሳይኛ ቋንቋ የመለሰችው (8ቱ ሴቶች) የመጀመሪያ ቴአትሯ ነው፡ በትርጉም እና በዝግጅት፡፡ (የሚስት ያለኽ)፡ እንዲሁ የፈረንሳይን ዕውቅ ተውኔት (ሲራኖ)፡ (በባሴ ሀብቴ የተተረጎመውን) ተከታዮቹ ሥራዎቿ ናቸው፡፡ በሲዊዲን፡ በኬንያ በቴአትር ጉዳይ ተጉዛለች፡፡ ለአንድ ወር በኒወርክ ሰንብታለች፡፡ (ኮንዶሚኒየሙ) የሚል ፊልምም ሠርታለች፡፡ የ(ገመና 2) የመጨረሻ 20 ክፍሎች ደራሲም ነበረች፡፡ በፊልሞች እና በቴሌቪዥን ድራማ ላይ ተውናለች፡ ትተውናለች፡፡ በፋና ራድዮ ሲተላለፍ የቆየው (የደራው ጨዋታ) ዝግጅት አካልም ነበረች፡፡ በ(ደርሶ መልስ) ድራማ በተዋናይነት አለች፡፡ በሊሴ ገ/ማርያም ት/ቤት ቴአትር ታስተምራለች፡፡ ከ21 ዓመት በላይ ሙያው ውስጥ ናት፡፡ ተውናለች፡ አዘጋጅታለች፡ ደርሳለች፡ ተርጉማለች፡ … ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የአርትስ ቴሌቪዥን ኹነኛ ሰው በመኾን፡ የተለያዩ ቅርፅ እና ይዘት ያላቸውን ዝግጅቶች በመፍጠር፡ በማሳተፍ እና በማስኬድ እየመራች ትገኛለች፡፡ …የትጋት የሥጋ ዘመድ …
  19. ሳሙኤል ይርጋ: ሙዚቃ የጀመረው በ16 ዓመቱ ነው፡፡ ፒያኖ ተጫዋች ነው፡ ሙዚቃ አቀናባሪም፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶችን አቅርቧል፡ ተጠባቂ ከኾኑት ውማድ እና ግላስቶንበሪ ፌስቲቫልን ጨምሮ፡፡ ከቤዚስት ተጫዋቹ ፒተር ገብርኤል ጋር ስምምነት በመፍጠር (ጉዞ) የሚል የመጀመሪያ አልበሙንም በሪል ወርድል ሪከርድስ አማካኝነት ሠርቷል፡፡ ይኸም አልበም ተቀባይነትን አግኝቶ በቢልቦርድ ዎርልድ ሚዉዚክ ቻርት ላይ በአንደኝነት ለሳምንታት ሰንብቷል፡፡ በዓለም፡ የኢትዮጵያ የሙዚቃ አምባሳደር ነው፡፡ በዓለም ኹሉ እየተዘዋወረ ከተለያዩ ባንዶች ጋር በመኾን ፒያኖ ሶሎ ሥራዎችን አቅርቧል፡፡ ፈለቀ ኃይሉ፡ ሚሚ/ስንታየኹ ዘነበ፡ ተራማጅ ወረታው/ማሲንቆ፡ ጸደኒያ ገ/ማርቆስ ኾነው፡ ኒክ ዱብላ የተቋቋመው መቀመጫውን እንግሊዝ አገር ያደረገ የደብ ኮለስስ ባንድ አባል ነበር፡፡ ተሸላሚም ነበር፡፡ ኹለት አልበሞች፡ (The town called Addis) እና (Addis through the looking Glass) ሠርቷል፡፡ እንደ ሙላቱ አስታጥቄ፡ እንደ ግርማ ይፍራሸዋ ኹሉ የዘመናችን መልክ ነው፡፡ Jazz, Soul, Funk, Pop ስልቶችን ውኅድ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ይጫወታል፡፡ በጉዞ አልበም ውስጥ ይገኛሉ፡፡
  20. ሀመልማል አባተ: የተወለደችው ሀረር፡ ያደገችው አሰበ ተፈሪ፡ የሙዚቃ ዝንባሌዋ የታየው በቤተክርስቲያን፡ ያደገው ቀበሌ ኪነት፡ የጎለበተው ሐረር ፖሊስ፡ የተሻገረው ብሔራዊ ቴአትር፡ … በሂልተን፡ በግዮን የምሽት መዝናኛዎች፡ … ከሮሃ ባንድ ጋር አሜሪካ ድረስ የተሻገረ የሙዚቃ ሕይወት አላት፡፡ የመጀመሪያ አልበሟን ታንጎ ሙዚቃ ቤት ካሳተመ በኋላ እስከ በቀደሙ 2011 ዓ/ም ድረስ 9 አልበሞችን ሠርታ አስደምጣለች፡፡ በሙዚቃ ሥራዋ ዓለምን አካላለች፡፡ ለ10 ዓመት ያህል በአሜሪካ የከረመች ጊዜ በሎስ አንጀለስ ሲቲ ኮሌጅ ለ2 ዓመት ሙዚቃ ተምራለች፡ አልፈጸመችም እንጂ፡፡ በየዓመቱ ከመስከረም ጋር የምትወጣውን አደይ ትመስላለች፡ ዘመን መሻገራችንን ከሚያበስሩን ዜማዎች መካከል አንዱ የርሷ ነውና … (እንኳን አደረሳችኹ)
  21. ሃና ተረፈ: ግጥም ትጽፍ ነበር፡፡ የጋዜጠኝነት ምኞትም ገረፍ አድርጓታል፡፡ በደርግ ጊዜ የቀይ መስቀል ፶ኛ ዓመት ሲከበር በግጥም ተወዳድራ 200 ብር ተሸልማለች፡፡ የዘፈን ግጥምም ደርሳለች፡፡ ለሰሎሞን ደነቀ (እምዬ እማምዬ)ን ጨምሮ 6ያህል፡፡ ሙዚቃ ት/ቤትም ገብታለች፡ ያሬድ፡፡ ለ 3ዓመት ያህል ዋናዋን ቫዮሊን አድርጋ ማሲንቆና ፒያኖን ተምራ ሳታጠናቅቅ ወጥታለች፡፡ ከዚህ ኹሉ በኋላ ከ1971 ዓ/ም ጀምሮ በራስ ቴአትር ተዋናይ ኾናለች፡፡ እስከ አሁን ድረስ … በቴሌቪዥን ድራማ (መንጠቆ) (ከመድረክ የተመለሰ) ይጠቀስላታል፡፡ በመድረክ ቴአትር፡ በራድዮ ድራማ፡ በሲኒማ በርከት ያሉ ሥራዎች ላይ አለች
  22. ኩኩ ሰብስቤ: ሙዚቀኞች ጎረቤት ነበሯት፡፡ የ15 ዓመት ብቃይ ሳለች ሙዚቀኞቹ ወደ ሱዳን ያቀኑ ነበርና ይዘንሽ እንኺድ ይሏታል፡ ስትዘፍን ማርካቸው፡፡ ቤተሰቦቿ እንዴት ተደርጎ አሉ … 12ኛ ክፍል ስትጨርሺ) ተብላ ቀረች፡፡ ከዛም በፊት ከ 9 ዓመቷ ጀምሮ፡ ከኅብረ ትርዒት እና የአድማጮች ምርጫ የወንዱንም የሴቱንም፡ ሙዚቃዎችን እየሰማች በምትማርበት ናዝሬት ት/ቤት ትዘፍን ነበር፡፡ ታዲያ እኩዮቿ ከዝላይ እና ጨዋታ የተረፈ ጊዜ ኖሯቸው ትኩረት ስለማይሰጧት ሰሚዎቿ እና አድናቂዋቿ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ነበሩ፡፡ 12ኛ ክፍል ጨርሰው፡ ምረቃ ዝግጅት ላይ ተጋብዘው ከመጡት ዋልያስ እና አይቤክስ ባንድ ጋራ በተማሪው ፍላጎት እንድትጫወት ኾነ … ጋሽ አቤሴሎም … የአበባ ጉንጉን አደረጉላት፡፡ … እኛ ጋ ተጫወቺ) እኛ ጋ ተጫወቺ) ጥያቄ ቀረበላት … ሮሃ ባንድ በሳምንት 2ቀን በራስ ሆቴል በ150 ብር እና ዋልያስ ባንድ ሳምንቱን በሙሉ በሂልተን ሆቴል በ600 ብር … የራስ ሆቴሉን መረጠች፡፡ ቆይታ ወደ ሂልተን ተሻገረች … ከዓለማየኹ እሸቴ ጋራ (እንግዳዬ ነሽ) ተዘፈነ … (ፍቅር በረታብኝ) (አወይ ቀብራሬ) (ቻልኩበት) … የደጃች ሰብስቤ ልጅ የቀድሞ የመዝገብ ስም እሌኒ ሰብስቤ … ከ12ኛ ክፍል ጀምሮ ደግሞ መዝገብ የሚውቃት
  23. ማንያዘዋል እንዳሻው: በፊልም እና በቴአትር ዝግጅት ከ World Intellectual Property Organization (WIPO) Creativity Award አሸናፊ፡ በቴአትር ዝግጅት የ Dr. Karl Award ተሸላሚ፡ በደቡብ አፍሪካ ፊልም ካምፓኒ በተሠራው “The Father” በተሰኘው እ.ኤ.አ ከ2ሺ ጀምሮ፡ በአፍሪካ፡ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ በተዘጋጁ ፊልም ፌስቲቫሎች እና በዓለም ዙሪያ በተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በተሠራጨው አጭር ፊልም፡ የፊልሙን ጽሑፍ (ከ7 የአፍሪካ ሀገሮች መካከል) ውድድር አሸናፊ፡ በ 2000 እና በ2002 በኪዳን ኢትዮጵያ፡ (የዓመቱ ምርጥ አዘጋጅ)፡ በ 4ኛው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል በዴዝዴሞና ፊልም በ (የዓመቱ ምርጥ አዘጋጅ) ዘርፍ ተሸላሚ ነው፡፡ …. በትርጉም ያቀረባቸው ቴአትሮች አሉት፡፡ Andorra, በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፡ (አማጭ) በራስ ቴአትር፡ The Little Brave Tailor, በሕፃናት እና ወጣቶች ቴአትር… ከ20 በላይ የመድረክ ቴአትሮችን አዘጋጅቷል፡፡ በሜጋ ኪነጥበባት፡ The Visit, የብሩክታዊት ሥጦታ …በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፡ (ንጉሥ አርማህ) (ኀምሌት)፡ … በራስ ቴአትር፡ የፀጋዬ ገ/መድኅን ትርጉም (ማክቤዝ) በዐዲስ አበባ ቴአትር እና ባህል አዳራሽ(ማዘጋጃ)፡ (ዩሊየስ ቄሳር) (ዳና)፡ (እንግዳ) The Lover and The Zoo Story, (double bill) … በአ.አ.ዩ Woyzeck, Six Characters in Search of an Author፡ (ዳንዴው ጨቡዴ) (የመንግሥቱ ለማ) …… በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተሠራጩት ድራማዎች ደግሞ Conscience, The Portrait, The Vengeful Student ልደት፡ (የአንገት ጌጡ), ተርጓሚው አውግቸው ተረፈ ታዲያ ይኽ ኹሉ ከመኾኑ በፊት በቴአትር ጥበብ ኹለተኛ ዲግሪውን ፡ከጀርመን Humboldt University አግኝቷል፡፡ ይኽ ኵሉ ከመኾኑ በፊት በ1977ዓም በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴአትር ተምሯል፡፡ ይኽ ኵሉ ከመኾኑ በፊት በምኒልክ ት/ቤት አንደኛ እና ኹለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ፈጽሟል፡፡ በተለያየ ጊዜ በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አለቅነት፡ ሠርቷል የአሁኑን ጨምሮ፡፡ በቅርብ፡ (የፍቅር ማዕበል) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፡ (እንግዳ) እና (የመስቀል ወፍ) በማዘጋጃ፡ አሁን ደግሞ (እምዬ ብረቷ) በሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሚታይለት ቴአትሩ ነው፡፡ ምናልባትም በቀደመዉ ጊዜ የቀረውን የቴአትር ቤት አስተዳዳሪ ኾኖ ቴአትር ሠርቶ ለትርኢት የማብቃት ልምድን በስማ በለው ብቻ እንዳይቀር የመለሰ በርግጥም የቴአትር ባለሞያ ነው፡፡


Comments

or to write a comment

Latest News and Articles

Ethiopian movie news and article - Asansiro
read more