Artist Biruktawit Shimeles Picture
4 0 0

Actress

ትውልዷ እና እድገቷ ሀዋሳ ነው። ከልጅነቷ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚዘጋጁ ድራማዎች እና ሞዴሊንጎች ላይ ትሳተፍ ነበር። ግጥም እና ድርሰት ትፅፍ ነበር እንደውም ከትወናው ይልቅ ፀሀፊ የምሆን ይመስለኝ ነበር ትላለች። አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በሀዋሳ ሲሆን ያጠናቀቀችው ወደ አዲስ አበባ የመጣችው ለትምህርት ሲሆን ብዙም ሳይቆይ እውነት ሀሰት የተሰኘ ፊልም ላይ እንድትሰራ ካስት ተደርጋ የመጀመሪያ ፊልሟን ሰርታለች ከዛም ደስ ሲል፣ አደረች አራዳ፣ ፍቅሬን በምን ቋንቋ እና ለእይታ ያልበቃው ያቺ ነገር ፊልሞች ላይ ተውናለች። የተቀበረው እና ትርታ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማዎች ላይ ተውናለች። በተለያዩ የቴሌቭዥን ማስታወቂያዎች ፣ በሶስት የሙዚቃ ክሊፖች ፣ የማስተር ሼፍ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ በፕሮግራም መሪነት እና በተለያዩ የፎቶ ሞዴሊንግ ስራዎች ላይ ተሳትፍለች።

Nick name: Birkti

Recommended Artists