Kassahun Fiseha (ካሳሁን ፍሰሃ)
አማርኛ ፊልም በ፫ት ይከፈላል አንደኛው #ካሳሁን(#ማንዴላ) መጀመርያ የሚያፈቅርበት ሁለተኛው #ማንዴላ የሚፈቀርበት ሌላው እና የመጨረሻው በቁጥር የሚያንሰው #ካሳሁን_ፍሰሀ(#ማንዴላ) ጠጠር ያለ ገፀ ባህሪ (እንደ አንድ ጅግና፣ወራጅ አለ... አይነት ) ወክሉ ሲሰራ ነው። ሰሙኑን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ደጋፊሆች ማንዴላ ወይም ማንደላ የቡና ደጋፊ ነው በሚል በጣም ተልካሻ ምክንያት እሱ የሚሰራበትን ፊልም አናይም የሚል አድማ እንደጀመሩ ጆሮ አይሰማው የለም ለወሬ አይከፈል ሰማው፤ ማንዴላ ያለበትን ፊልም አናይም የሚል ዘመቻ በቻይንኛ አማርኛ ፊልም ያለማየት አድማ ነው ምክንያቱም አሁን ከሚወጡት ፊልሙች ከ10 ሳካብደው አስሩም ላይ ካልሆነ ደግሙ 9 ወይም 8ቱ ላይ አለ። ሌላው ደግሞ በዚህ ዋጋ የለሽ ዘመቻ ማነው የሚጎዳው? የቡና ክለብ ወይስ ማንዴላ ማነው... እኔን ብጠየቅ አድማ የመቱት የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊሆች ናቸው የምለው ለምን ካላቹኝ ካሳሁን የመሰለ ተዋናይ ማየት አመለጣቸው፣ቀረባቸው፣አለፋቸው...መቼም በርግጠኝነት ቡና ክለብ አይጎዳም ማንደላ ደግሙ እኛን የመሰለ ወሳኝ አድናቂ እያለ መቼም እሱ መስራቱን ዳይሬክተሮችም እሱን ማሰራት አያቁምም ለምሳሌ እንኳን እኔ በዚህ አመፅ ተነሳስቼ #የት_ነበርሽን ሁለት ጊዜ አይቼዋለሁ ፍቅር ያሸንፋል፣ደስ እንዳለሽ... እሱ ለመተወን አይድከም እንጂ እኔ ከማየት ወደኅላ አልልም። ሌላው ዋናው ነገር በዚው ከቀጠላቹ መንግስት ከፀረ ልማት፣አመጽ በማስፋፋት፣ኮማንድ ፑስቱን በመጣስ... በሚል የቅዱስ ጊዮርጊስን ምድብ ጨዋታ ሳታዮ እስር ቤት ስሙን ስናሳምረው ማረምያ ቤት ልትገቡ ትችላላቹሁ እና ጥቅም አልባ አድማቹውን አቁሙ! ከማንዴላ አድናቂ ከእኔ (Tsion)
Born: July 1980 in Addis Ababa
Nick name: Mandela