Artists

Emebet Woldegabriel (እመቤት ወልደገብሬል)

Actress

ተወልዳ ያደገችው አዲስ አበበ ለም ሆቴል ነው ነው። በልጅነቷ ጋዜጠኛ መሆን ትፈልግ ነበር ግን የሆነችው ተዋናይ ነው ተስፋዬ ስሜ ጋር ትምህርትን ወስዳ ወደ ትወናው በትያትር ተቀላቀለች የመጀመርያዋን መድረክ ህፃናት ወጣቶች ተቀጥራለች ቀጥላም በብሄራዊ ትያትር ተቀጥራ እየሰራች ነው በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ የትያትር ምሩቅ ናት በረከታ ትያትሮች፣ሬዲዮ ድራማዎች፣የቲቪ ድራማ እና ፊልሞች ሰርታለች።

Henok Mehari (ሄኖክ ማሃሪ)

Actor

ከሙዚቀኛ ቤተሰብ ነው የተገኛው የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ሙሩቅ ነው የራሱ 2ት አለበም አለው አቀናባሪ ነው፣ግጥም እና ዜማ ፀሀፊ ነው፣ ከወንድሞቹ ጋር ማሃሪ ብራዘር ባንድ መስርተው እስካሁን በርካታ ድምፃውያንን በማጀብ እየሰሩ ነው በድምፃዊነቱ ከኢትዮጲያ አልፎ በአፍሪካ አፍሬማ አሸናፊ ነው።

Yonatan Worku (ዮናታን ወርቁ)

Director | Writer

ውልደት እና እድገቱ በሰሜኑ ክፍል ራያ ውስጥ ነው። ፊልም የማየት ፍቅሩ ፊልም ለመስራት ኧነሳስቱታል ወደ አዲስ አበባ መጥቱ ከጓደኛው ጋር ሆኑ የመጀመርያ ፊልሙን ለተመልካች አበቃ ካዛ ቀጥሉ በግሉ ትንሽ ያማይባሉ ፊልሞች ለተመልካች አቅርቦል።

Ermias Tadesse (ኤርማያስ ታደሰ)

Actor | Director | Producer | Writer

ፊልም ለመሰራት ህልሙን ከጓደኞቹ ጋር ግሩፕ መስርቱ ፊልም መስራትን ጀመረ:: ግሩፑ ውስጥ ደራሲ፣ዳይሬክተር እና ተዋናይ ሆኑ በጋራ ይሰራ ነበር ግሩፑም ሲፈርስ ወደ በቁሚነት 123 ሲቲዲዮ መሰራት ጀመረ ከዚህ በፊት ይሰራበት እንደነበረው ይሰራ ቀጠለ።

Birhane Nigussie (ብርሃኔ ንጉሴ)

Director | Writer

ትውልድ እና እድገቱ በሰሜን ኢትዮጲያ ትግራይ ነው። ፊልም ስራን ከልጅነቱ ጀምሩ በጭንቅላቱ ይዞ ነው ያደገው:: ምኞትም ህልም ብቻ ሳይሆን ወደ ስኬት አምርቱል:: ከፊልም ሙያ በፊት ከሰይፉ ፋንታሁን እና ሱራፌል ወንድሙ ጋር በጋራ አዲስ ዜማ የሚል ፕሮግራም በኤፍ አዲስ፣ኢኒፎ ቴም በወር አንዴ የሚወጣ መፅሄት እና በቲቪ ደግሙ አዲስ ዜማ በኢቲቪ ያቀርብ ነበር:: ካዛም አልፎ በርካታ የፊልም ባለሙያዎች የፈለቁበት ሆሊላንድ ትማህርት ቤት ከአላማየው ታደሰ እና ተስፋዬ ገ/ሀና በጋራ ከፍተው በፊልሙ ላይ... read more

Tezera Lemma (ተዘራ ለማ)

Actor

ወደ ትወናው የገባው ዘግይቱ ነው ማለት ይቻላል ለበርካታ ዓመት በሹፍርና ይሰራ ነበር ቢሆንም ግን የትወና እና የጥበብ ፍቅር ከእሱ አልተለየውም ነበር ቁመናውም ለፊልምአመቺ እነደሆነ ያየ ሁሉ ምስክር ነው። የመጀመርያውን ሰራ በኦድሽን አልፎ አንድ ብሉ መሰራት ጀመረ ከዛ በኃላ ለቁጥር የሚከብዱ ፊልሞችን ሰርቱል።

Dereje Haile (ደረጀ ሀይሌ)

Actor

ውልደት እና እድገቱ አዲስ አበባ:: ሙሉ ስሙ ከሚጠራ ይልቅ ደረጀ እና ሀብቴ ቢባል ለሁሉም ይቀላል:: በኮሜዲ ሰራው በኢትዮጲያ ቴሌቪሽን በርካታ ሰራውችን ከሀብቴ ጋር ሰርቱል(ነብሱን ይማረው):: በርካታ የቀልድ ሲዲዮች አውጥቱል በዘፈንም አልበም አውጥተዋል። በኢትዮጲያ ኮሜዲ ትልቅ ስራ እንደሰራ ይታወቀል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከቀልድ ስራው በላይ ፊቱን ወደ ፊልም ያዞረ ይመስላል በፊልሙ ከገባበት ጊዜ አንፃር ትንሽ የማይባሉ ስራዎችን ለተመልካች አድርሶል። በይበልጥ የሚታወቀው በኮሜዲ ስራው ነው።

Tariku Desalegn (ታሪኩ ደሳለኝ)

Cinematographer | Director

ውልደት እና እደገቱ አዲስ አበባ ነው ፊልም ማየት አብዝቱ ስለሚወድ ፊልም ማስራት ፍላጎቱ አድጉ ቶም ቪዲዮ ተምሩ ወደ ስራው ለመግባት ተንደረደረ። ሲኒማቶግራፈር ሆኑ በኢትዮጲያ ፊልም ተቀላቀለ።

Tamiru Berhanu (ታምሩ ብርሃኑ)

Actor | Director | Producer | Writer

ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ጣልያን ሰፈር ነው። ለትወናው ያለው ፍቅሩ አብሮት አድጉል ማለት ይችላል ጥሙን ለመወጣት ከመላኩ አሻጋሪ ቡድን ተቀላቅሎ በርካታ ትያትሮችን ድፍን ኢትዮጲያ ላይ አስይቱል አዲስ አበባ ባሉ ትያትር ቤቶች በተጋባዥነት ተውኖል፣በርካታ የማስታወቂያ ስራዎችን አቅርቦል አሁን ከትወናው በተጨማሪ መድረክ መምራት እና ፕሮግራም ማቅረብን በተጨማሪ ይሰራል።

Biruk Tamiru (ብሩክ ታምሩ)

Director | Writer

በትምህርት የተመረቀው በህግ ነው ግን የጥበብ ፍቅር አሸነፈው እና ቶም ቮቶ ግራፍ ካሜራ ተምሩ የራሱን ሰራ ከመስራቱ በፊት በተላያዩ ቦታዎች በካሜራ ሙያ ሰርቱእያለ የራሱን ፕሮዳክሽን ከፍቱ (ሻዶ ፊልም ፕሮዳክሽን)የተላያዩ ፊልሞችን ለተመልካች አድርሱል።

Fekadu Teklemariam (ፍቃዱ ተክለማርያም)

Actor

ሀገራችን ላይ ካሉ ተዋንያን ከፊት የሚሰለፍ ነው ውልደት እና እድገቱ አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው።ትወና የልጅነት ፍቅሩ ነው ወደ ትወናውም ገብቱ አንቱታ አግኝቱል በርካታ የመድረክ ስራዎችን በይበልጥ ብሄራዊ ትያትር መድረክ ላይ በርካታ ስራዎችን ሰርቱል፤ ትንሽ የማይባል የሬዲዮ ድራማ እና የቲቪ ድራማ ላይ ተውኖል። በይበልጥ የሚታወቀው አፄ ቴዎድሮስ ትያትር ላይ አፄ ቴዎድሮስ ሆኑ ሲተውን ነው።

Kidist Yilma (ቅድስት ይልማ)

Director | Screenplay | Writer

ውልደት አዲስ አበባ ዑራኤል ነው እድገቱ ደግሙ ዑራኤል እና ባሌ ነው። ከሚኒ ሚዲያ አንስታ አሁን ላይ አሉን ብለን ከምንጠራቸው ደራሲ እና አዘጋጁ ውስጥ አንዱ ናት። በዚህ ሙያ የሴት እጥረት አለው አሁን ላይ ብዙ ፊልም ለተመልካች በማቅረብ በሴቶች የሚፎካከራትም የለም።