Artists

Gebrehiwot Gebrecherkos (ገብረህይወት ገብረጨርቆስ)

ትውልድ እና እድገቱ ሰሜኑ የኢትዮጲያ ሰሜን ክፍል ትግራይ አክሱም ነው። እንደ አብዛኛው የፊልም ባለሙያ የፊልም ጥበብ ወስጡ የገባው የሆሊዮድ እና ቦሊዮድ ፊልም በማየት ነበር:: ያ የፊልም ፍላጎቱ አድጎ የራሱን ፊልም ፕሮዳክሽን ከፍቱ ለተመልካች ስራዎችን አቅርቧል። ኤማንዳ፣አይነጋም ወይ?፣ሰርግ ከአሜሪካ፣ፀረ ሚልዮን፣ኮንዶሚንየሙ፣የጎደለኝ፣ፊደላዊት。。。 በፕሮዳክሽን ከተሳተፈባቸው በጥቂቱ ነው። ከደራሲ እና ተዋናይት ባዮሽ ከበድ ጋር በትዳር ተሳስረው ሁለት ልጆች አፍርተዋል።

Welela Assefa (ወለላ አሰፋ)

Actress

አንጋፋ ብለን ከምንጠራቸው ተዋንያን ውስጥ ዋና ናት። በሀገር ፍቅር በአዲስ አበባ ማዘጋጃ እንዲሁም በብሄራዊ ትያትር በርካታ የመድረክ ሰራዎችን ሰርታለች ብዙ ፊልሞች የሬዲዮ ድራማዋች እና ቲቪ ድራማዎች ላይ ተውናለች አሁንም በትወና አለም ውስጥ ናት።

Yayehrad Mamo ( ያይዕራድ ማሞ)

Actor

ትውልድ እና እድገቱ አዲስ አበባ ነው። ተዋናይ የመሆን ህልም ባይኖረውም ፊልም ማየት ግን ሲበዛ ያስደስተዋል በአጋጣሚ ነበር ወደ ትወናው የተቀላቀለው አንድ ፊልም ሰቶር ለጥቂት ጊዜ በእራሱ ስራ ምክንያት ከፊልሙ ጠፍቱ ነበር ምንም ቢዘገይም በቲቪ ድራማ ደጋሚ ወደ ትወናው ተቀላቅሉ ፊልሞችን ሰርቷል።

Sinafikish Tesfaye (ስናፍቅሽ ተስፋዬ)

Actress

ውልደት እና እድገቷ አዲስ አበባ ዑራኤል ነው። የትወና ፍቅሯ ህልሞ ብቻ ሳይሆን ስኬቱማ ጭምር ሆኖላታል ከፊልሞች ይልቅ ትያትር በተለይ ብሄራዊ ትያተር ብዙ ሰርታለች፣የሬዲዮ ድራሞችንም፣የቲቪ ድራማውችንም ላይ ተውናለች ስናፍቅሽ ተስፋዬ። በይበልጥ የምትታወቀው ያልተኬደበት መንገድ ላይ ቢጢቆ ሆና ስትሰራ ነው።

Elias Wosenyeleh (ኤልያስ ወሰንየለህ)

Actor

የአርት ጏዙን ሚኒ ሚዲያ ቤተሰብ መምርያ አድርጉ ብዙ አስተማሪ ስራዎችን ሰርቶ ወደ ፊልም የመጣው የልጅነት ህልሙ ነበር:: እራሱን ተዋናይ ሆኖ ማግኝት ይሄው ህልሙ ሜዳ ላይ አልቀረም አሁን የሙሉ ሰዓት ተዋናይ ነው።

Selam Ashagre (ሰላም አሻግሬ)

Actress

በቅርብ ጊዜ ያሉ ተዋንያን እንደሚቀላቀሉት እሷም መንገድ ላይ ያያት ዳይሬክተር ነበር የመጀመርያዋን ፊልም ያሰራት:: እያለች ሌላ አንድ ፊልም ጨምራ የቲቪ ድራማ መስራት ጀመረች። ዋና ስራዋ ማርኬቲንግ ነው:: ወደ ትወና የተቀላቀለችው በዚህ መንገድ ነው።

Berhane Getachew (ብርሃኑ ጌታቸው )

Director | Writer

የተማረው ከአርት ጋራ በግራም በቀኝም የማይገናኝ ፖለቲካ ነው:: እሱን ትምህርቱን ትቶ ወደ ፊልም ገብቷል አሁን ላይ ወደ ሾው ለመግባት እያሟሟቀ ነው:: ሀርየት የሚል ከአምዕሮ ህመምተኞች ላይ የሚያጠነጥን ሾዉ ቀረፃውን ሰርቷል በአንዱ ቻናል ብቅ ይላል።

Amanuel Habtamu (አማኑኤል ሀብታሙ)

Actor

ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ነው ወደ አርቱ የገባው በአጋጣሚ ቢሆንም ብዙ ስራዎችን ሰርቷል የተማረው ትምህርት ሌላ ቢሆንም በአሁን ሰዓት የሙሉ ሰዓት ተዋናይ ነው። በይበልጥ የታወቀው በረቡኒ ልኡልን ሆኖ ሲተውን ነው።

Feleke Yemarwuha Abebe (ፈለቀ የማርውሃ አበበ)

Actor

ህይወቱን ለትያትር የሰጠ ነው መቀጠሩ የሚታክቱ መድረክ ስራዎችን በ4ቱም ትያትር ቤት አሳይቷል ምንም እንኳን ትንሽ ፊልም ቢሰራም በርካታ የሬድዮ ድራማውችን ሰርቷል ትረካውችን ሰርቷል በተጨማሪም በተለያዮ ዝግጅቶች መድረክ ይመራል። ሙሉ ስሙ ፈለቀ አበበ ሲሆን ማሀል ላይ የከተተው የእናቱን ስም ነው።

Henok Ayele (ሔኖክ አየለ)

Director

ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ነው። ፊልም ስራን ጉዞን ከሆሊላንድ ጥበብ ማዕከል ተምሮ ወደ ፊልሙ አለም በሰፊው ተቀላቅሏል በርካታ ፊልሞችን ሰርቱል አዲስ አይኖችን አሳይቷል ብዙ ተዋንያን አንድ ብለው ከሄኖክ አየለ ጋር ጀምረዋል።

Teshale Worku (ተሻለ ወርቁ)

Actor | Director | Producer

ለረዥም አመት ትያትር ላይ ነው ያሳለፈው ብዙ ትያትሮችን ሰርቷል ሀገር ፍቅር ትያትር ቤት ብዙ ድርሰት ፅፏል የፃፈውንም አዘጋጅቷል። ከቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ፊልሙ አለም በደንብ ገብቷል።

Simon Tsegaye (ስምኦን ፀጋዬ)

Actor

ውልደት እና እድገቱ አዲስ አበባ 4ኪሎ ነው። ወደ ትወናው የተቀላቀለው ቅርጫት ኮስ ሲጫወቱ ታቶይ ነው። ከትወና በፊት የሚዲያ ባለሙያ ነበር እስከ ቅርብ ጊዜ የኢትዮፒካሊንክ አዘጋጅ ነበር የራሱንም ቲቪ ፕሮግራም ናሁ ላይ ጀምሮ ነበር አልቀጠለም እንጂ።