Artists

Berhane Getachew (ብርሃኑ ጌታቸው )

Director | Writer

የተማረው ከአርት ጋራ በግራም በቀኝም የማይገናኝ ፖለቲካ ነው:: እሱን ትምህርቱን ትቶ ወደ ፊልም ገብቷል አሁን ላይ ወደ ሾው ለመግባት እያሟሟቀ ነው:: ሀርየት የሚል ከአምዕሮ ህመምተኞች ላይ የሚያጠነጥን ሾዉ ቀረፃውን ሰርቷል በአንዱ ቻናል ብቅ ይላል።

Fikirte Desalegne (ፍቅርተ ደሳለኝ)

Actress

ተዋናይ እና ድምፃዊ ፍቅርተ ደሳለኝ(ማሚ) በጡረታ እስክትለቅ ድረስ በሀገር ፍቅር በተዋናይ፣ድምፃዊ እና በተወዛዋዥነት አገልግላች። በጣም በርካታ ፊልሞች ላይ የእናት ገፀ ባህሪ ወክላ ሰርታለች ጠቅሰን መጨረስ አይደለም ማጋመስ አንችልም ለምሳሌ ያህል እነዚን መጥራት ወደናል፦ ያ ልጅ፣ማንነት፣ሰርፕራያዝ፣ ጓንታናሞ፣ ዱካ፣በልደቴ ቀን፣ህይወቴ፣ስሌት፣ በመንገዴ ላይ፣400 ፍቅር፣ያነገስከኝ፣ አይራቅ፣አስረሽ ፍቺው፣የሴም ወርቅ፣ ኤደን፣ብላቲናው፣ላብጡስ፣ ፊደላዊት፣ታዛ፣... እጅግ በጣም ብዙ ፊልሞች... read more

Yohannes Tefera (ዮሃንስ ተፈራ)

Actor | Writer

ፈንጂ ወረዳ፣ጭወኃት፣ስስት፣መፈንቅለ ሴቶች፣ ያለ ሴት፣300ሺ፣ኮመን ኩርስ፣ቫላታይን፣ጆከር፣ተስፈኞቹ፣ ሄሎ ኢትዮጲያ፣ሰውረኝ፣ቁልፎን ስጪኝ፣አማረኝ፣ሰበበኛ ፣ፍቅር በሬዲዮ፣ካህኔ፣ሚስቴን ቀሙኝ፣ተሸውደናል፣ ኤደን፣የህዝብ ነኝ፣ሌላው መንገድ እና እንደ ቀልድ ላይ ተውኖል። ገመና 2 እና ዳና የቲቪ ድራማ ላይ ተውኖል ዳና ላይ አሁንም እየተወነ ነው
Please send us your contribution to our Facebook ... read more

Chirotaw Kelkay (ችሮታው ከልካይ)

Actor

አንጋፋ ተዋንያን ተርታ ውስጥ ይመደባል ውልደቱ እና እድገቱ አዲስ አበባ ከፍተኛ 10 ነው። በርካታ የመድረክ ስራዎች በተለይ ሁኔታ ሀገር ፍቅር ትያትር ቤት በጥሩታ እስከተለየበት ጊዜ ድረስ ለቁጥር የሚከብዱ ትያትሮችን ተውኑል፣በርካታ የሬዲዮ ድራማዎችን በትወና ተሳትፎል እንዲሁም የቲቪ ድራማዎችም ላይ በትወና አይተነዋል።

Melkam Yideg (መልካም ይደግ)

መልካም ይደግ: ያለ-ሴት፣የመጨረሻው ቀሚስ፣ባንቺ ጊዜ፣ወደው አይሰርቁ፣የእኔስ አዳም እና ታሽጓል ላይ ተውናለች። ብላቲናው እና ፍሬ ፊልም ፕሮዲሰር ናት በየመጨረሻው ቀሚስ በመጀመርያው ጎማ አዋርድ የአመቱ ምርጥ ረዳት ተዋናይት አሸናፊ ሞዴል፣ተዋናይ እና ፕሮዲሰር መልካም ይደግ

Michael Million (ሚካኤል ሚልዮን)

Actor

ውልደት እና ዕድገቱ አዲስ አበባ አሜሪካ ግቢ ነው። በልጅነቱ ብዙ ሙያ ይነካካ ነበር ተዋናይ ከመሆኑ በፊት አስተማሪም የጥበብ ፍላጎቱ ከፍ ከፍ ብሎ አዲስ አበባ ዮንቨርስቲ የትያትር ምሩቁ ነው በአርቱ ላይ ከፍ ብሎ መቀጠል ጀምሯል። የፊልም ፅሁፍ በማፃፍ ብዙ ፊልሞች ላይ ሰርቷል ያልታሰበው፣የወንዶች ጉዳይ፣አይገባንም。。。እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።

Leulseged Kassa (ልዑልሰገድ ካሳ)

በትወና ዲፕሎማና cocያለው የተቀበረው ተከታታይ ድራማ ላይ በትወና ብሌን አቻዬ እኔና ቤቴ ፊልም ላይ በትወና የተሳተፈ ሲሆን በፕሮዳክሽን ማናጀርነትም ይሰራል

Ayu Girma (አዩ ግርማ)

Actress

ውልደቷም እድገቷ አዲስ አበባ ነው፤ የትወና ፍቅሩ እና ብቃቱ ከክበባት አልፎ ወደ የማለዳ ኮከቦች ውድድር አምጥቶታል። የመጀመርያው የማለዳ ኮከቦች ከተወዳደሩት እስከ መጨረሻው ከተጓዙ አንዷ ናት አዮ፤ ሁለተኛ በመውጣት አጠናቃለች። ከዛም በመቀጠል የማለዳ ኮከቦች ተዋንያን የተወኑበት አጭር ተከታታይ ድራማ እዛው ቲቪ ላይ የተለለፈ ድራማ ፅፋለች፤ በመቀጠል በርካታ አድናቂዎችን ያተረፈችበት ዘመን ድራማ ላይ ሶፍያን ገፀ ባህሪ መተወን ጀመረች። ሼማንደፈር የተሰኘ ፊልም ደሞ ዳይሬክት አድር... read more

Behailu Wase (በሀይሉ ዋሴ )

Director | Producer | Writer

የተማረው ትምህርት ኮምፒተር ሳይንስ ነው:: የነፍሱ ጥሪ ተከትሎ ብዙ ፊልሞችን መፃፍ ጀምሯል የሚፅፈውን ፅሁፍ ወደ ስክሪን ለማውረድ ብዙ ጊዜ አልወሰደበትም:: የፊልም ጥበብን ለማወቅ አላቲንዮስ ቡድን በመቀላቀል ቀጠለ:: ብዙ ውይይቱችን መታደም በመወያየት ቀጠሎ አሁን የደረሰበት ደርሷል።

Alemtsehay Eshetu (አለምጸሃይ እሸቱ)

Actress

አለም በተለያዩ ክሊፖችና ማስታወቂያዎች ላይ ትታወቃለች። በአዲስ አበባ ቦሌ አከባቢ ተወለደች። ከፍሎ ሟች የሚለው ፊልም ላይ ተውናለች። የሰላም ተስፋዬና የማህደር አሰፋ አድናቂ ናት። ባሁኑ ሰዓት የቢዝነስ ማኔጅመንት ተማሪ ስቶን፤ ወደፊት በፊልሙ ዘርፍ ሰፊ ተሳትፎ የማድረግ እቅድ አላት።

Admasu Kebede (አድማሱ ከበደ)

Actor | Director | Writer

ውልደት እና እድገቱ አዲስ አበባ ልደታ ነው። የአርት ጉዞን ፋዘር ቤት ሄዶ አጠንክሮታል ብሉ ናይል ፊልም አካዳሚም ተምሯል። ትወናንም አጠንክሮ መስራቱን ቀጥሎል ከጀመረበት ጊዜ እስካ አሁን ትንሽ የማይባል ፊልም ሰርቷል:: በይበልጥ የሚታወቀው በየወንዱች ጉዳይ አምዕሮ ሆኖ ሲተውን ነው።