Artists

Fantu Mandoye (ፋንቱ ማንዶዬ)

Actor

አንጋፋ ብለን ከምንጠራቸው ተዋንያን ወስጥ ከፊት ይገኛል። ውልደት እና እድገቱ መሀል አዲስ አበባ ፒያስ ነው ጡረታ እስከሚወጣ ድረስ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ብዙ ስራዎችን በድምፅም በትወናም ሰርቷል። በይበልጥ የሚታወቁበት ስራ የት ሄደሽ ነበር በሚለው ዘፈን ነው

Biruktawit Shimeles (ብሩክታዊት ሺመልስ)

Actress

ትውልዷ እና እድገቷ ሀዋሳ ነው። ከልጅነቷ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚዘጋጁ ድራማዎች እና ሞዴሊንጎች ላይ ትሳተፍ ነበር። ግጥም እና ድርሰት ትፅፍ ነበር እንደውም ከትወናው ይልቅ ፀሀፊ የምሆን ይመስለኝ ነበር ትላለች። አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በሀዋሳ ሲሆን ያጠናቀቀችው ወደ አዲስ አበባ የመጣችው ለትምህርት ሲሆን ብዙም ሳይቆይ እውነት ሀሰት የተሰኘ ፊልም ላይ እንድትሰራ ካስት ተደርጋ የመጀመሪያ ፊልሟን ሰርታለች ከዛም ደስ ሲል፣ አደረች አራዳ፣ ፍቅሬን በምን ቋንቋ እና ለእይታ ... read more

Abiy Gebremariam (አብይ ገብረማርያም)

Actor | Producer

ተወልዶ ያደገው በሰሜን ኢትዮጲያ ጎንደር ነው። ምንም ተወናን ቢወድም ከትወና በፊት የሞዴሊንግ ሙያን በደንብ አድርጎ ሰርቷል አብይ በርካታ ፊልሞችን ላይ ተውኗል።

Shimeles Abera (ሺመልስ አበራ)

Actor

የአባቱን ሞያ ተከትሎ ነው ወደ ትወናው የተቀላቀለው ሀገራችን ላይ አሉ ብለን ከምንጠራቸው ተዋንያን መሀል አንዱ ነው። ለቁጥር በጣም የሚከብዱ ትያትሮችን ኢትዮጲያ ውስጥ ያሉ ትያትር ቤቶች ተውኖል በቅርብ ጌዜ እንኳን ደመ ነፍስ፣የሚስት ያለህ፣ቅጣጥል ኮከቦች፣የቴዎድሮስ ራዕይ፣እንግዳ፣የእግዜር ጣት፣አብሮ አደግ፣ፍቅር የተራበ በጣም ትንሹ ናቸው በርካታ የሬድዮ ድራማውች፣የቲቪ ድራማውች ላይ ተውኖል። በይበልጥ የታወቀው ኮቴው የቲቪ ድራማ ላይ ማየት የተሳናው ሆኑ ሲሰራ ነው።

Dawit Negash (ዳዊት ነጋሽ)

Director | Writer

ትውልድ እና እድገቱ አዲስ አበባ ነው። በትምህርቱ ሌላ ነገር ቢማርም በተማረበት ሙያ ብዙም ሳያገለግል የፊልም የመስራት ጥበቡ ይበለጥ ገዝፎ ፀሀፊ እና ዳይሬክተር ሆኑ እራሱን ያገኛል በአርቱ ትልቁ ጉዞ ላይ እንደሆን የሚሰማው ዳዊት የሚሰራው ስራ ላይ ማስተላፍ የሚፈልገው ሁሉንም የሚመለከት እናዳለበት ያምናል።

Fenan Hideru (ፋናን ህዳሩ)

Actress

ማሬ ማሬ በሚለው ዘፈን ምንአልባትም ከዘፈኑ እኩል የገነነች ተዋናይ በቅርብ አዲስ ፊልም ከ123 ስትዲዮ ጋር እየሰራች ነው:: ጄ ቲቪ ላይ እየተላለፈው ያለው ዝነኛው የሬድዮ ድራማ የነበረው አሁን በምስል የመጣሁ የማዕበል ዋናተኞች ላይ ከዚህ በፊት በሬድዮ መስታወት አራጋው የወከለቻት ብቻ ሳይሆን የሆነቻትን እፁብ ድንቅን ወክላ በቲቪ እየሰራች ነው Please send us your contributions to our Facebook read more

Rediet Terefe (ረድኤት ተረፈ)

ከአዲስ አበባ ዮንቨርስት ትያትር ጥበብ በድግሪ ሙሩቅ ናት። ትወና እጅግ ትወዳለች: የነፍሷ ጥሪ እንደሆነም ታምናለች:: ስለዚህ አንድ ብላ በሬድዮ ገራሚ ድምፇን አሰማችን:: በማምሻ ድራማ በሸገር 102.1 ላይ ተወነች። በመቀጠል የተማረችበትን ትምህርት ትያትርን በትወና ተቀላቀለች:: ሲራኖ ትያትር ላይ መሪ ተዋናይ ሆና ተውናለች እየተወነች ነው። ለአንባቢ ከሌሎች ገጣሚያን ጋራ ሆና አንድ የግጥም መድብል አድርሳለች:: ብቻዋን ደግሞ አንድ ሐሙስ የሚል የግጥም መድብል ለአንባብያን አድር... read more

Arsema Worku (አርሴማ ወርቁ)

Actress | Director | Producer | Writer

ፊልም መሰራት የቀን ተሌት ህልሟ ነበር ሆሊላንድ የጥበብ ማዕከል ትምህርት ወስዳለች ወዲያው ወደ ጥበቡ እንዳትገባ በተማረችበት ሙያ ማገልገል እናዳለባት ተሰማት ትንሽ ብትዘገይም ወደ ጥበቡ ለመግባት ባዛው ሳትቀር ፊልም ፕሮዲይስ አድርጋ ተቀላቀለች። በአሁን ሰዓት ፊልም ሰሪዎች ማህበር ፀሀፊ ናት።

Dibekulu Tafesse (ዲበኩሉ ታፈሰ)

Actor

ከልጅነቱ ጀምሮ ከቤተ ክርስትያን አንስቱ ሙዚቃን ይሰራ ነበር ::ድብን ያለ የሙዝቃ ፍቅሩ ብዙ ባንድ ሰርቷል በርካታ ናይት ክለብ ውስጥ ሰርቷል። በአሁን ሰዓት በጃኖ ባንድ ውስጥ ዋና ድምፃዊ ነው። ወደ ትወናው የገባው አስቦበት አይደለም ላካራክተሩ ብቁ ሆኖ የታያት ዘሪቱ ከበደ ካስት አድርጋው እሱም ፊልም የማየት ፍቅሩ ገፍቶት እስካሁን የመጀመርያውን የመጨረሻውን ፊልም ቀሚስ የለበስኩለት ላይ ተውኗል።

Elias Wosenyeleh (ኤልያስ ወሰንየለህ)

Actor

የአርት ጏዙን ሚኒ ሚዲያ ቤተሰብ መምርያ አድርጉ ብዙ አስተማሪ ስራዎችን ሰርቶ ወደ ፊልም የመጣው የልጅነት ህልሙ ነበር:: እራሱን ተዋናይ ሆኖ ማግኝት ይሄው ህልሙ ሜዳ ላይ አልቀረም አሁን የሙሉ ሰዓት ተዋናይ ነው።

Selam Tesfaye (ሰላም ተስፋዬ)

Actress

ውልደቷ በሐረር ነው። በተለያዩ የሃገራችን ከተማዎች ብትኖርም ያደገችው ሁመራ ነው። የትወና መንገዱን ከሁመራ አዲስ አበባ መጥታ አቢስኒያ ተማረች። ከካስቲንክ ኤጀንቱች ፎቱን አይታ ሉና ኩማ የመጀመርያዋን ቢሆንስ ፊልም ሰራች። ቀጥላም ቫላታይን፣ፍቅርበይሉኝታ፣አዲስ ህይወት፣ህይወት በደረጃ፣ሳስት ማዕዘን፣ልክ ነኝ፣ፍሪደም፣ስር ሚዜዋ፣በጭስ ተደብቄ፣እሷን ብዬ፣አልማዜ፣ፍቅሬፍቅረኛ፣ማርትሬዛ፣ወ/ት ድንግል፣ጥለፈኝ፣ ባንዳፍ፣79፣ቤዛ፣ይመችሽ ያአራዳ ልጅ ሁለት፣የልብ ቋንቋ፣ሶስት ማዕዘን ሁለት፣እውነታ፣... read more

Biruk Tamiru (ብሩክ ታምሩ)

Director | Writer

በትምህርት የተመረቀው በህግ ነው ግን የጥበብ ፍቅር አሸነፈው እና ቶም ቮቶ ግራፍ ካሜራ ተምሩ የራሱን ሰራ ከመስራቱ በፊት በተላያዩ ቦታዎች በካሜራ ሙያ ሰርቱእያለ የራሱን ፕሮዳክሽን ከፍቱ (ሻዶ ፊልም ፕሮዳክሽን)የተላያዩ ፊልሞችን ለተመልካች አድርሱል።