Artists

Zerihun Asmamaw (ዘሪሁን አስማማው)

Actor | Director

የኛ ክፍል፣የወንዱች ጉዳይ፣ማህቶት፣ላገባ ነው፣ ዌይተሩ፣ደርቢ፣አልቦ፣መፈንቅለ ሴቶች፣ኮመን ኩርስ፣ ሲቲ ቦይስ፣ማን ልበል፣ጓንታኖሞ፣አየሁሽ፣ፍቅር በአሜሪካ፣እናፋታለን፣የጠፋው ልጅ እና አትውደድ አትውለድ ላይ ተውኖል። ጎሮቤታሞች ሲትኮም ላይም ተውኖል። የአየሁሽ ፊልም ዳይሬክተር ነው። Please send us your contribution to our Facebook page or by email to

Biruk Menase (ብሩክ ምናሴ)

Actor

ትውልድና እድገቱ አዲስ አበባ ልዩ ስሙ ጣልያን ሰፈር በሚባል ሲሆን በመናገሻ ገነት ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ታዳጊ ክፍል ውስጥ ውድቅት ብርሃን የተሰኘ ትያትር ይሰራ ነበር። ከዚያም ዶ/ር ተስፋዬ አበበ ጋር ቴያትር ተምሯል። ከዝያም ፍቅርን ፈርሁ እና ያልተሰበረ የተሰኙ ፊልሞችን ለህዝብ ኣቅርቧል። ባሁን ሰዓት ከመድረክ በስተጀርባ የሚል ትያትር በሐገር ፍቅር ቴያትር ቤት እየሰራ ይገኛል።

Samson Tadesse (ሳምሶን ታደሰ)

Actor | Director | Producer | Writer

Samson Tadesse, best known for the movie Sost Maezen (2013), is passionate since elementary school participating in theatrical clubs. He attended elementary school in Nazret at Hailiye Chefik. Then He attended Assela Atekalay for high school. He is currently married to the sensational Ethiopian Idol finalist Dagmawi... read more

Fitsum Kassahun (ፍጹም ካሳሁን)

Director | Writer

ትወልድ እና እድገቱ መርካቶ ነው። የፊልም ሙያ እና ግጥም የመፃፍ ፍላጉቱ ሳይቁረጥ አሁንም ድረስ አብሮት ዘለቁ እስካሁን እየተደደረበት ነው የድምፃዊ አብነት አጎናፍር ታናሽ ወንድም ስለወነ የግጥም ሰራውን ለወንድሙ ሳይሰስት ሰጥቱል ፍፁምም አንድ ብሎ ፊልም የጀመረው ወንድሙ በፃፈው አላዳንኩሽም ፊልም ነው። በመቀጠል ቤራሚድ፣ስስት፣አንናገርም፣ህይወት እና ፍቅር፣ሰበበኛ እና ስስት ሁለት ፊልም ዳይሬክተር ነው።

Tamiru Berhanu (ታምሩ ብርሃኑ)

Actor | Director | Producer | Writer

ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ጣልያን ሰፈር ነው። ለትወናው ያለው ፍቅሩ አብሮት አድጉል ማለት ይችላል ጥሙን ለመወጣት ከመላኩ አሻጋሪ ቡድን ተቀላቅሎ በርካታ ትያትሮችን ድፍን ኢትዮጲያ ላይ አስይቱል አዲስ አበባ ባሉ ትያትር ቤቶች በተጋባዥነት ተውኖል፣በርካታ የማስታወቂያ ስራዎችን አቅርቦል አሁን ከትወናው በተጨማሪ መድረክ መምራት እና ፕሮግራም ማቅረብን በተጨማሪ ይሰራል።

Michael Million (ሚካኤል ሚልዮን)

Actor

ውልደት እና ዕድገቱ አዲስ አበባ አሜሪካ ግቢ ነው። በልጅነቱ ብዙ ሙያ ይነካካ ነበር ተዋናይ ከመሆኑ በፊት አስተማሪም የጥበብ ፍላጎቱ ከፍ ከፍ ብሎ አዲስ አበባ ዮንቨርስቲ የትያትር ምሩቁ ነው በአርቱ ላይ ከፍ ብሎ መቀጠል ጀምሯል። የፊልም ፅሁፍ በማፃፍ ብዙ ፊልሞች ላይ ሰርቷል ያልታሰበው፣የወንዶች ጉዳይ፣አይገባንም。。。እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።

Mubarak Yusuf (ሙባረክ ዩሱፍ)

Director | Producer

We do not have full information about this artist, Please send us your contribution to our Facebook page or by email to info@etmdb.com

Yonatan Worku (ዮናታን ወርቁ)

Director | Writer

ውልደት እና እድገቱ በሰሜኑ ክፍል ራያ ውስጥ ነው። ፊልም የማየት ፍቅሩ ፊልም ለመስራት ኧነሳስቱታል ወደ አዲስ አበባ መጥቱ ከጓደኛው ጋር ሆኑ የመጀመርያ ፊልሙን ለተመልካች አበቃ ካዛ ቀጥሉ በግሉ ትንሽ ያማይባሉ ፊልሞች ለተመልካች አቅርቦል።

Kidist Siyum (ቅድስት ስዩም)

Actress

ተዋናይት ቅድስት ስዩም የሐገራችንን ስም በፊልሙ ዘርፍ ባስጠራው በላምብ ፊልም ትወናን ጀመረች። በፊልሙ ላይም ባሳየችው የትወና ብቃት በሞሮኮ የፊልም ፈስቲቫል በምርጥ ረዳት ተዋናይት ዘርፍ አሸናፊ ልቶን ችላለች። ከዛም በመቀጠል በሰራችው ፍርቱና ፊልም በሩስያ ፊልም ፈስቲቫል ላይ የምርጥ ተዋናይትነትን ሽልማት ልታገኝ ችላለች።

Etsehiwot Abebe (እጸሂወት አበበ)

Actress | Producer

ተዋናይት እና ሞዴል እፀህይወት አበበ ተወልዳ ያደገችው አዲስ አበባ ልዩ ስሙ ጣልያን ሰፈር ነው፡፡ የመጀመሪያ ጀረጃ ትምህርቷን በአፍሪካ አንድነት እና እድገት ፋና ትምህርት ቤት የተማረች ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ደግሞ መድሀኒዓለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምራለች፡: በ16 አመቷ ነበር ወደ ሞዴሊግ ሙያ የገባችው :: የሞዴሊግ ትምህርትን የተማረችው በ ሚስ ስኩል ኦፍ ሞዴሊግ 2 ባች ሆና ትምህርቷን ያጠናቀቀችው፡፡ መጀመሪያ የስራችው የ ኤርምያስ ምን ተክቼ ልርሳሽ የሚለውን ሙዚቃ ቪዲዮ... read more

Solomon Muhe (ሰለሞን ሙሄ)

Actor | Director | Writer

ደራሲ፣ዳይሬክተር፣ተዋናይ እና ፕሮዲሰር ሰለሞን ሙሄ ውልደቱም እድገቱም አዲስ አበባ ነው። በጣም በወጣትነቱ ነው ወደ ትወና አልያም ወደ ጥበብ የገበው፤ እንደ እኔ አገለላለፅ ሰለሙን በተለይ በፊልማችን ላይ በጥሩ ሆነ በመጥፎ ብቻ አሁን ላለበት ደረጃ የራሱን ነገር ያበረከተ ባለሙያ ነው።
በ1994 ማግስት የተባለ ፊልም በድርሰት፣ በዝግጅት፣ ትወና፣ ፕሮዲሰር አልፎም ተርፎ ማጀብያ ሙዚቃ በመስራት ለህዝብ አቅርቦል ከዛም በፊት በአጃቢነት ትንሽ የማይባሉ ስራዎችን ሰርቷል።
መ... read more

Melat Nebiyu (ሜላት ነብዩ)

Actress | Producer | Writer

ውልደት እና ዕድገቷ አዲስ አበባ ሲሆን ወደ ትወና የገባችው በአጋጣሚ ቢሆንም ከገባች በኋላ ብዙ ስራዎችን ሰርተላች።