Artists

Arsema Worku (አርሴማ ወርቁ)

Actress | Director | Producer | Writer

ፊልም መሰራት የቀን ተሌት ህልሟ ነበር ሆሊላንድ የጥበብ ማዕከል ትምህርት ወስዳለች ወዲያው ወደ ጥበቡ እንዳትገባ በተማረችበት ሙያ ማገልገል እናዳለባት ተሰማት ትንሽ ብትዘገይም ወደ ጥበቡ ለመግባት ባዛው ሳትቀር ፊልም ፕሮዲይስ አድርጋ ተቀላቀለች። በአሁን ሰዓት ፊልም ሰሪዎች ማህበር ፀሀፊ ናት።

Dereje Haile (ደረጀ ሀይሌ)

Actor

ውልደት እና እድገቱ አዲስ አበባ:: ሙሉ ስሙ ከሚጠራ ይልቅ ደረጀ እና ሀብቴ ቢባል ለሁሉም ይቀላል:: በኮሜዲ ሰራው በኢትዮጲያ ቴሌቪሽን በርካታ ሰራውችን ከሀብቴ ጋር ሰርቱል(ነብሱን ይማረው):: በርካታ የቀልድ ሲዲዮች አውጥቱል በዘፈንም አልበም አውጥተዋል። በኢትዮጲያ ኮሜዲ ትልቅ ስራ እንደሰራ ይታወቀል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከቀልድ ስራው በላይ ፊቱን ወደ ፊልም ያዞረ ይመስላል በፊልሙ ከገባበት ጊዜ አንፃር ትንሽ የማይባሉ ስራዎችን ለተመልካች አድርሶል። በይበልጥ የሚታወቀው በኮሜዲ ስራው ነው።

Rediet Terefe (ረድኤት ተረፈ)

ከአዲስ አበባ ዮንቨርስት ትያትር ጥበብ በድግሪ ሙሩቅ ናት። ትወና እጅግ ትወዳለች: የነፍሷ ጥሪ እንደሆነም ታምናለች:: ስለዚህ አንድ ብላ በሬድዮ ገራሚ ድምፇን አሰማችን:: በማምሻ ድራማ በሸገር 102.1 ላይ ተወነች። በመቀጠል የተማረችበትን ትምህርት ትያትርን በትወና ተቀላቀለች:: ሲራኖ ትያትር ላይ መሪ ተዋናይ ሆና ተውናለች እየተወነች ነው። ለአንባቢ ከሌሎች ገጣሚያን ጋራ ሆና አንድ የግጥም መድብል አድርሳለች:: ብቻዋን ደግሞ አንድ ሐሙስ የሚል የግጥም መድብል ለአንባብያን አድር... read more

Dereje Gashaw (ደረጄ ጋሻው)

Director

ፊልም ጥበብ ውስጥ መግባት ፊልም መስራት ከልጅነቱ ጀምሮ በሚያየው የውጪ ፊልም ልክፍት ውስጡ ከገባ ቆይቱል ምንም ነገር እናዳሰቡት ባይሆንም ወደ ኢትዮጵዮ ፊልም ጥበብ በጓደኞቹ ፊልሙች ፕሮዳክሽን ውስጥ እየሰራ ቀስ በቀስ የራሱን ፊልም ከጓደኞቹ ጋር መሰራት ጀመረ። በአሁን ሰአት የሙሉ ሰአት ፊልም ሰሪ ነው ማለት ያስደፍራል። በአሁን ሰዓት አል ሶፊ ፊልም ፕሮዳክሽን ከጓደኞች ጋር በመክፈት ስራውችን እየሰራ ነው።

Yetnayet Tamrat (የትናየት ታምራት)

Actress | Producer

ወርቅበወርቅ፣ፍቅር ሲመነዘር፣ሼፋ 2፣ያነገስከኝ እና 50 ሎሚ ላይ ተውናለች፤ ዳና የቲቪ ድራማ ላይ ተውናለች እየተወነች ነው። ያነገስከ'ኝ እና ሃምሳ ሎሚ ፕሮዲሰር ናት የትናየት ታምራት ሚሚ

Bahrain Keder (ባህሬን ከድር)

Actor | Producer

ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ሰባተኛ ነው። ወደ ትወናው የገባው በአጋጣሚ በሞዴሊንግ ነው ወደ ፊልም ተመርጦ የገባው ከተዋናይነት ከሞዴሊንግ በተጨማሪ የራሱ ፕሮዲውስ ያደረጋቸው ስራዉች አሉ።

Fenan Hideru (ፋናን ህዳሩ)

Actress

ማሬ ማሬ በሚለው ዘፈን ምንአልባትም ከዘፈኑ እኩል የገነነች ተዋናይ በቅርብ አዲስ ፊልም ከ123 ስትዲዮ ጋር እየሰራች ነው:: ጄ ቲቪ ላይ እየተላለፈው ያለው ዝነኛው የሬድዮ ድራማ የነበረው አሁን በምስል የመጣሁ የማዕበል ዋናተኞች ላይ ከዚህ በፊት በሬድዮ መስታወት አራጋው የወከለቻት ብቻ ሳይሆን የሆነቻትን እፁብ ድንቅን ወክላ በቲቪ እየሰራች ነው Please send us your contributions to our Facebook read more

Robel Solomon (ሮቤል ሰለሞን)

Director

ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ነው ትወና ቢወድም እንኳን ሳያስብ ወደ እዚህ እንደገባ ይናገረል የቅርጫት ኳስ ተጨጫዋች ነው በዛ አጋጣሚ ነበር የመጀመርያ ፊልሙን መስራት የቻለው በአሁን ሰዓት በሌላ ዘርፍ ትምዕርት ላይ ይገኛል።

Tewodros Sifraye (ቴድሮስ ስፍራዬ)

Actor

ስላ አንቺ፣ቬራ፣ያ ልጅ፣ከበሮ፣ቢሆንስ፣ኒሻን፣እሱን ብዬ፣የፍቅሬ ፍቅረኛ፣ጊዜ ሚዛን እና አርፋጅ ላይ ተውኖል።

Mekdes Tsegaye (መቅደስ ፀጋዬ)

Actress | Assistant-Director | Producer

Mekdes Tsegaye is a Film Actress, Director, Writer, producer and Talk show host who is responsible for Tisisir , Yeadam Gemena , Zeraf, Yekereme, Mogachoch and Mekdi show. ትስስር፣የአዳም ገበና፣ዘራፍ፣የከረመ ላይ ትተውናለች። የትስስር ደራሲ፣የአዳም ገመና ደራሲ እና ዳይሬክተር ናት፤ትስስር፣የአዳም ገመና፣ዘራፍ፣ዲፕሎማት እና የከረመ ፊልሞች ፕሮዲሰር ናት። ኢቢኤስ ላይ የሚተላለፈው ሞጋቾች ተከታታይ የ... read more

Robel Girma (ሮቤል ግርማ)

Actor | Director | Writer

ተወዶል ያደገው ደቡብ ክልል ውስጥ አርባ ምንጭ ከተማ ነው ሁሌም ፊልምባየ ቁጥር ፊልም የመስራት ፍላጎቱ ይጨምር ነበረበፍላጎት ብቻ አልቀረም ምንም እንኳን ብሌላ ዘርፍ ቢመረቅም ወደ ፊልም ለመግባት ምንም አላገደውም በመጣበት ጥቂት ጊዜ ወደ ፊልሙ ገብቷል።